Return to BahaiPrayers.net
Facebook
በየዕለቱ ጧት እኩለ ቀንና ማታ የሚደረግ፣ ለመፀለይ የሚሻ ሁሉ እጁን ይታጠብ በመታጠብም ላይ ሳለ እንዲህ ይበል፡፡
አምላኬ ሆይ፤ መጽሐፍህን አጥብቆ እንዲይዝና የዓለምም አጀቦች በላዩ ላይ ኃይል እንዳይኖራቸው፣ እጄን አበርታ፡፡ የእርሱም ባልሆነው በማንኛውም ነገር ውስጥ እንዳይገባ ጠብቀው፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ኃያሉ፣ ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው ነህና፡፡
ቀጥሎ ፊቱን በመታጠብ ላይ እያለ እንዲህ ይበል፡፡
ጌታዬ ሆይ ፊቴን ወደ አንተ መልሻለሁ! በገጽህ ብርሃን አብራው፡፡ ወደ አንተም በቀር ወደ ማንም እንዳይዞር ጠብቀው፡፡
ከዚያም ይቁም፣ ፊቱን ወደ ቂብሊሀ የውዳሴ ማዕከል ማለትም ወደ ባህጂ አቶር በመመለስ እንዲህ ይበል፤
ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ራሱ ይመሰክራል፡፡ የግልጽነትና የፍጥረት መንግስታት የእርሱ ናቸው፡፡ እርሱ በእውነቱ የግልፀት ጎህ የሆነውን በሲና ላይ የተነጋገረውን በእርሱም አማካይነት የላቀው አድማስ እንዲያበራ የተደረገውን፣ በእርሱም ሊታለፍ የማይቻለው የለውጥ ዛፍ የተናገረውን በእርሱም አማኝነት በሰማይና በምድር ላሉት ሁሉ፣ እነሆ የሁሉ ባለቤት የሆነው መጥቷል፡፡ ምድርና ሰማይ፣ ክብርና ግዛት የሰዎች ሁሉ ጌታ የላይኛውና የምድር ዙፋን ባለቤት የሆነው የአምላክ ናቸው፡፡ የሚለው ጥሪ የታወጀበትን ከስቶታል፡፡
ከዚያም ያጎንብስና እጆቹን በጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤
አንተ ከእኔ ሙገሣና ከማንም ሰው ሙገሣ በላይ ከእኔ ገለፃና በሰማይና በምድር ካሉት ሁሉ ገለፃ በላይ የተከበርክ ነህ፡፡
ከዚያም ቆሞ እጆቹን በመዘርጋት መዳፎቹንም ወደላይና ወደፊት በማቅናት እንዲህ ይበል፤
አምላኬ ሆይ፣ እርሱን በተማፃኘ ጣቶቹ በምሕረትህና በፀጋህ ዘርፍ ላይ የተንጠላጠለውን ቅር አታሰኘው፣ አቤቱ አንተ ምሕረትን ከሚያሳዩ ሁሉ ፍጹም መሐሪው ነህና!
ከዚያም ይቀመጥና እንዲህ ይበል፤
አንድነትህህና አንድዬነትህን አንተ አምላክ መሆንህን፣ ከአንተም በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ በእውነቱ አንተ እምነትህን ገልፀሃል፣ ቃል-ኪዳንህንም አሟልተሃል፣ በሰማይ ውስጥና በምድር ላይ ለሚኖሩትም ሁሉ የፀጋህን በር በሰፊው ከፍተሃል፤ የዓለም ለውጦችና አጋጣሚዎች ወደ አንተ ከመመለስ ሊያደናቅፋአቸው ያልቻሉ፣ እና በአንተ ዘንድ ያለውን ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ያላቸውን ሁሉ በሰውት በተወዳጆችህ ላይ ቡራኬና ሰላም፣ ሰላምታና ክብር ይረፍ፤ በእውነቱ አንተ ምንጊዜም ይቅር-ባዩ ፍጹም ፀጋ የተመላው ነህና፤
- Bahá'u'lláh