Return to BahaiPrayers.net   Facebook

በሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አንዱ የሚደገረግ፣ ይህን ፀሎት ለመድገም የሚሻ ይቁምና ልቦናውን ወደ እግዚአብሔየር ያቅና፣ በሥፍራውም እንደቆመ የሩኅሩኁን የይቅር -ባዩን አምላክ ምሕረት እንደሚጠባበቅ ሁሉ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ይመልከት፤ ከዚያም እንዲህ ይበል፤

አቤቱ አንተ የስሞች ሁሉ ጌታና የሰማያት ፈጣሪ የሆንከው ሆይ! ፀሎቴ፣ ውበትህን እንዳላይ የጋረደኝን ግርዶሽ የሚያነድ እሳትና፣ ወደ ሕልውናህም ውቅያኖስ የሚመራኝ ብርሃን እንዲሆን፣ በእነዚያ ፣ ፍጹም የተከበረው የንዑዱና ሊታይ የማይቻለው አንተ ሕልውና ጎሕ በሆኑት እማፀንሃለሁ፤

ቀጥሎም እግዚአብሔር የተባረከና የተከበረ ይሁንና፣ እጆቹን ወደ እርሱ በልመና በማንሳት እንዲህ ይበል፤

አቤቱ አንተ የዓለም እሾትና የብሔሮች ሁሉ ተወዳጅ የሆንከው ሆይ! ወደ አንተ ዞሬ፣ ከአንተ በቀር ከማንኛውም ቁራኛነት ሁሉ ተላቅቄ በእንቅስቃሴው መላው ፍጥረት በተቀሰቀሰበት ገመድህ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ ጌታዬ ሆይ እኔ አገልጋይህ የአገልጋይህም ልጅ ነኝ፡፡ ፈቃድንህና ፍላጎትህን ለመፈፀም ዝግጁ ሆኜ መቆሜንና ከበጎ ፈቃድህም በስቀር ሌላ እንደማልሻ ተመልከተኝ፤ አገልጋይህን እንደፈቀድከውና እንደሻህ እንድታደርገው በምሕረትህ ውቅያኖስና በጸጋህ የቀኑ ኮከብ (የዘመኑ ፀሐይ) እማጠንሃለሁ፡፡ ከመነገርና ከመወደስ በላይ በጣም ከፍ ባለው ኃያልነትህ! በአንተ የተገለፀ ማንኛውም ነገር የልቤ ፍላጎትና የነፍሴ ተወዳጅ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ሰማያትንና ምድርን የከበበውን ፈቃድህን ተመልከት እንጂ ምኖቶቼንና አድራጎቶቼን አትመልከት፣ በፍጹም ታላቁ ስምህ አቤቱ አንተ የብሔሮች ሁሉ ጌታ ሆይ አንተ የፈለግኽውን ብቻ ፈልጌአለሁ፤ የምታፈቅረውንም ብቻ አፈቅራለሁ፡፡

ከዚያም በኋላ ተንበርክኮ ግንባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይበል፡፡

ከራስህ ገለፃ በቀር ከማንም ገለፃ፣ ከአንተም የመረዳት ችሎታ በቀር ከማንም የመረዳት ችሎታ በላይ የላቅህ ነህ፡፡

ቀጥሎም ይቁምና እንዲህ ይበል፤

ጌታዬ ሆይ ፀሎቴን ሉዓላዊነትህ እስካለ ድረስ ለመኖርና በዓለማትህም እያንዳንዱ ዓለም ስምህን ላወሳበት የምችልበት፣ የህይወት ውሃዎች ምንጭ አደርግልኝ፤

እንደገና በመማፀን እጆቹን ወደላይ በማንሳት እንዲህ ይበል፤

አቤቱ ከአንተ ሲለቀዩ ልቦችና ነፍሶች የቀለጡ በፍቅርህም እሳት መላው ዓለም የተቀጣጠለው ሆይ! አቤቱ አንተ በሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ የሆንከው ሆይ! በአንተ ዘንድ የሚገኘውን እንዳትነፍገኝ፣ መላውን ፍጥረት ባንበረከክህበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ይህ ባይተዋር በግርማህ ከለላ ሥር በምህረትህ ክልል ውስጥ ወዳለው፣ እጅግ በጣም ወደ ተከበረው ቤቱ ሲገሰግስ፣ ይህ ኃጢአተኛ የይቅር ባይነትህን ውቅያኖስ ይህ ዝቅተኛ የክብርህን መንበር፣ ይህ ምስኪን ፍጡር የሀብትህን ምንች ሲሻ ትመለከታለህ፤ የፈቀድከውን ማንኛውንም ነገር የማዘዝ ስልጣን ያንተ ነው፡፡ በሥራዎችህ መመስገን፣ ለትዕዛዞችህም ታዛዥነትን ማግኘት፣ ትዕዛዝ በመስጠጥም ገደብ የሌለብህ ሆነህ ፀንተህ የምትኖር መሆንህን እመሰክራለሁ፡፡

ቀጥሎም እጆቹን ወደላይ በማንሳት ከሁሉ በላይ ታላቁን ስም፣ ማለትም አላህ ኡ አብሃ (አምላ ፍጹም ክቡር) የሚለውን ሶስት ጊዜ ይደጋግም፡፡ አምላክ ይክበር ይመስገንና በእርሱ ፊት አንጎብሶ እጆቹን ጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤

አምላኬ ሆይ ፣ አንተን ለማምለክ በመናፈቁ አንተን ለማስታወስና ለማሞገስ በጣም በመመኘቱ መንፈሴ በመላው አካላቴ ውስጥ እንዴት እንደተንቀሳቀሰ ለዚያ በቃልህ መንግስትና በዕውቀትህ ሰማይ ትዕዛዝህ ልሳን ለመሠከረለትም መንፈሴ እንዴት እንደሚመሠክር ታያለህ፡፡ አቤቱ ጌታዬ በዚህ ሁኔታ የእኔን ምስኪንነት እንዳሳይና የአንተን በረከቶችና ፀጋዎች እንዳወሳ፣ የእኔን ደካማነት እንድመሠክርና የአንተን ሥልጣንና ኃያልነት እንድገልጽ፣ ከአንተ ጋር ያለውን ሁሉ ከአንተ መለመን እወዳለሁ፡፡

ቀጥሎም ይቁም፣ በመማፀንም እጆቹን ሁለቱ ወደ ላይ ያንሳና እንዲህ ይበል፤

ከአንተ ከፍጹም ኃያሉ፣ ከፍጹም ለጋሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ በመጀመሪያም ሆነ በመጨረሻ ሁሉን ደንጋጊ ከሆንከው፤ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ በመጀመሪያም ሆነ በመቸረሻ ሁሉን ደንጋጊ ከሆንከው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ቅርታህ ድፍረትን ሰጥቶኛል፣ ምሕረትህ አጠንክሮኛል፣ ጥሪህ ቀስቅሶኛል ፀጋህም አስነስቶ ወደ አንተ መርቶኛል፡፡ እንግዲያውማ በቅርበትህ ከተማ በር ላይ ልቆም ከፈቃድህ ሰማይ ወደሚያበሩት ብርሃኖች ፊቴን ለመመለስ የምደፍር እኔ ማን ነኝ? ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ጎስቋላ ፍጡር የፀጋህን በር ሲያንኳኳ ይህ ኢምንት ነፍስ ከበረከትህ እጆች ዘለዓለማዊውን የሕይወት ጅረት ሲሻ ትመለከታለህ፡፡ አቤቱ አንተ የስሞች ሁሉ ጌታ ሆይ፣ ትዕዛዝ ምንጊዜም ያንተው ነው፣ አቤቱ የሰማያት ፈጣሪ ሆይ የእኔ ግን ሁሉንም መተውና ለፈቃድህ በውዴታ መገዛት ነው፡፡

ቀጥሎም እጆቹን ሶስቱ ወደ ላይ በማንሣት እንዲህ ይበል፤

እግዚአብሔር ከታላቅ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ነው፡፡

ቀጥሎም ተምበርክኮ ግምባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይበል፤

ወደ አንተ የቀረቡት የሚያቀርቡት ምስጋና ወደ ቅርበትህ ሰማይ ከመውጣት ወይም የእነዚያ ለአንተ ያደሩት ሰዎች ልቦች አፅዋፋት ወደ መንበርህ በር ከመድረስ በጣም ከፍ ያልክ ነህ፤ አንተ ከባህርያት ሁሉ የነፃህ ከስሞችም ሁሉ በላይ ቅዱስ መሆንህን እመሠክራለሁ:: ከአንተ ፍጹም ከላቀው ከንዑዱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

ቀጥሎም ይቀመጥና እንዲህ ይበል፡-

የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ፣ የሰማይ ሰራዊት የገነት አርያም ነዋዎች ከእነዚህም በላይ ከፍጹም ደማቁ አድማስ የታላቁ አንደበት ራሱም የሚመሠክሩልህ፣ አንተ አምላክ መሆንህንና ከአንተም በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ፣ እርሱም ያ የተከሰተው በእርሱም አማካይነት ሁ እና ን (ሁን) ፊደላት የተገናኙበትና የተጣመሩበት፣ ሥውሩ ምስጢር፣ ብርቁ ምልክት መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ ስሙ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ በሆነው ብዕር የሠፈረው፣ በአምላክ መፃሕፍትም ውስጥ የተጠቀሰው፣ የሰማይና የምድር ዙፋን ጌታ እርሱ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡

ቀጥሎም ቀጥ ብሎ ይቁምና እንዲህ ይበል፤

አቤቱ የፍጡራን ሁሉ ጌታና የሚታዩትም የማይታዩትም ነገሮች ሁሉ ባለቤት ሆይ! አንተ እምባዬንና የማሰማውን ሲቃ እነሆ ታስታውላለህ፤ የማቃሰቴን ድምፅ፣ ዋይታዬን የልቤንም ሰቆቃ ትሰማለህ፡፡ በኃያልነትህ ሕግ ተላላፊነቴ ወደ አንተ ከመቅረብ አግዶኛል፡፡ ኃጢአቴም ከቅድስናህ መንበር አግልሎኛል፤ አቤቱ ጌታዬ ፍቅርህ አበልጽጎኛል፤ ከአንተም መለየት አጥፍቶኛል፤ ከአንተ መራቅም ጨርሶኛል፡፡ በውበትህ ላይ ለማተኮርና በመጽሐፍህ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለማክበር እንድችል እንድትወስንልኝ በዚህ ምድረበዳ ባሉት ዱካዎችህ በዳር አልባ ስፋት ውስጥ እዚህ ነኝ፡፡ እዚህ ነኝ በሚሉት የሕሩያንህ ቃላት፣በግልፀትህ እስትንፋስናበክስተትህ የንጋት ልዝብ ነፋስ እማጠንሃለሁ፡፡

ቀጥሎም ከሁሉም በላይ ታላቁን ስም ሶስት ጊዜ ይድገምና አጎንብሶ እጆቹን በጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤

አምላኬ ሆይ፣ አንተን እንዳስታውስና እንዳወድስህ ስለረዳኽኝ፣ እርሱን የምልክቶችህ ጎሕ የሆነውን ስላሳወቅኽኝ፣ በጌታነትህም ፊት እንድሰግድ ስለአደረግኽኝ፣ በአምላክነትህም ፊት ራሴን ዝቅ እንዳደርግና በታላቅነትህም አንደበት የተነገረውን ለመቀበል ስለአበቃኽኝ ምስጋና ለአንተ ይሁን፤

ከዚያም ይቁምና እንዲህ ይበል፤

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ጀርባዬ በኃጢአቴ ክብደት ጎብጧል፣ ግዴለሽነቴም አውድሞኛል፡፡ የእኔን ርኩስ ድርጊቶችና የአንተን ደግነት ባሰላሰልኩ ቁጥር ልቤ በውስጤ ይቀልጣል፣ ደሜም በስሮቼ ውስጥ ይፈላል፡፡ በውበትህም አቤቱ አንተ የዓለም እሾት ሆይ! ፊቴን ወደ አንተ ለማቅናት እፍረት ይሰማኛል፣ ናፋቂ እጆቼም ወደ ቸርነትህ ሰማይ ለመዘርጋት ያፍራሉ፤ አቤቱ አንተ የሰማዩና የምድሩ ዙፋን ጌታ የሆንክ አምላክ ሆይ! እንባዎቼ አንተን ከማስታወስና የአንተንም ባህርያት ከማወደስ እንዴት እንዳገዱኝ እነሆ ታያለህ! አቤቱ አንተ የፍጡራን ሁሉ ጌታ፣ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮች ሁሉ ንጉሥ የሆንከው ሆይ! ለተወዳጆችህ እንደልግስናህና እንደፀጋህ መጠን እንድታደርግላቸው በመንግስትህ ምልክቶችና በመግዛትህ ምሥጢራት እማጠንሃለሁ፡፡

ቀጥሎም ከሁሉም በላይ ታላቁን ስም ሶስቱ ይደገምና ተንበርክኮ ግንባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይላል፡፡

አምላካችን ሆይ ወደ አንተ የሚያቀርበንንና በመፃሕፍትህና በቅዱሳት ጽሁፎችህ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች የሚያድለንን ስለላክህልን ምስጋና ለአንተ ይሁን፣ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ከዋጋ ቢስ ሃሳብና ከከንቱ አስተሳሰብ አጀቦች እንድትጠብቀን እንማፀንሃለን፡፡ በእውነቱ አንተ ኃያሉ ሁሉን አዋቂው ነህና፡፡

ቀጥሎም ራሱን ቀና አድርጎ ይቀመጥና እንዲህ ይበል፤

አምላኬ ሆይ፣ ሕሩያንህ የመሠከሩትን እመሠክራለሁ፣ የገነት አርያም ነዋሪዎችም በኃያሉ ዙፋንህ ዙሪያ የከበቡት ሁሉ ያረጋገጡትንም አረጋግጣለሁ፡፡ አቤቱ የዓለማት ጌታ ሆይ የሰማይና የምድር መንግስታት የአንተ ናቸው፡፡

በየዕለቱ በሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አንዴ 95 ጊዜ የሚደገም፤

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac