Return to BahaiPrayers.net
Facebook
በፆም ወይም በሌሎች የማለዳ ጊዜያት የሚደረግ
አምላኬ ጌታዬ ሆይ! እኔ አገልጋይህ የአገልጋይህም ልጅ ነኝ፡፡ የአንድነትህ የቀኑ ኮከብ ከፈቃድህ ጎሕ በበራበትና በትዕዛዝህ መፃሕፍት ውስጥ በተደነገገው መሠረት ጮራውን በመላው ዓለም ላይ በፈነጠቀበት በዚህ ማለዳ ከመደቤ ነቅቻለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ ወደ ዕውቀትህ ብርሃን ውበት ለመንቃት በመቻላችን ለአንተ ምስጋና ይድረስህ፡፡ ጌታዬ ሆይ አንተን በስተቀር ሌላውን ሁሉ ለመተው የሚያስችለንንና ከአንተ በስተቀር ከማንኛውም ቁራኛነት የሚያነፃንን ላክልን፡፡ በተጨማሪም ለእኔ ለእኔ ውድ ለሆኑትና ለዘመዶቼ፤ ለወንዱም ለሴቱም የዚህኛውንና የመጪውን ዓለም መልካም ነገር ሁሉ እዘዝልን፡፡ አቤቱ አንተ የመላው ፍጥረት ተወዳጅና የጠቅላላው ሁለንተን ዓለም ምኞት የሆንክ ሆይ፣ የእርኩሱ አንሾኳሻኪ መገለጫዎች ከአደረግሃቸው ከእነዚያ በሰዎች ልቦናዎች ከሚያንሾኳሹኩት፤ በማይቋረጠው ጠባቂነትህ ጠብቀን፡፡ አንተ የፈቀድከውን ለማድረግ የማይሳንህ ነህና፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ኃያሉ፤ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ በገዛ ራሱም ነዋሪው ነህና ፡፡
ጌታ አምላኬ ሆይ ፤ እርሱን ከሁሉም በላቁት ስያሜዎችህ ላይ የሰየምከውን በእርሱም ፃድቃንን ከኃጢአን የለየህበትን ባርከው፣ እኛም አንተ የምትፈቅደውንና የምትወደውን እንድንሠራ በፀጋህ እርዳን፣ በተጨማሪም አምላኬ ሆይ የአንተ ቃላትና ፊደላት የሆኑትን ፊታቸውን ወደአንተ ያቀኑትን ወደአንተም ገጽታ የዞሩትን ጥሪህንም ያዳመጡትን ሁሉ ባርካቸው፤
በእውነቱ አንተ የሰዎች ሁሉ ጌታና ንጉሥ በሁሉም ነገሮች ላይየበላይ ነህ፡፡
- Bahá'u'lláh