Return to BahaiPrayers.net
Facebook
አምላኬ፣ ጌታዬ ፣የልቤ ዓላማ ሆይ! ይህ አገልጋይህ እንክብካቤህንና ጥበቃህን በመማፀን በምሕረትህ ጥላ ሥር ሊተኛ በፀጋህም ከለላ ሥር ሊያርፍ ይፈልጋል፡፡
ጌታዬ ሆይ አንተን ብቻ እንጂ ሌላውን ነገር ሁሉ እንዳያዩ አይኖቼን እንቅልፍ ከቶ በማያታልለው አይንህ እንድትጠብቅልኝ እለምንሃለሁ፡፡ አይኖቼ ያንተን ምልክቶች ለማየትና የግልፀትህን አድማስ ለመመልከት እንዲችሉ የማየት ኃይላቸውን አበርታ.. አንተ በእርሱ ሁሉን ቻይነት መገለፅ ፊት የሥልጣን ሕልውና የተንቀጠቀጠለት ነህና፡፡
ከአንተ ከፍፁም ኃያሉ ከሁሉን አስገባሪው ከማይገታው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡
እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ አንተን የሚናፍቁት ከአንተ በመለየታቸው ምክንያት አይኖቻቸው ሳያንቀላፉ እኔ እንዴት መተኛትን መምረጥ እችላለሁ፤ የተወዳጆችህም ነፍሶች ከአጠገብህ በጣም በመራቃቸው ክፉኛ አዝነው እያሉ እንዴት ለማረፍ እጋደማለሁ.
ጌታዬ ሆይ ፣ መንፈሴንና መላውን ህያውነቴን ለቀኙ እጅህ ኃይልና ጥበቃ አደራ ሰጥቻለሁ፡፡ እራሴን በአንተ ኃይል ትራሴ ላይ አሳርፋለሁ፡፡ በአንተ ፍላጎትና መልካም ፈቃድ አቀናዋለሁ፡፡ በእውነቱ አንተ አኑዋሪው ጠባቂው ፍፁም ኃያሉና ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው ነህ፡፡
በኃያልነትህ ! ተኝቼም ሆነ ነቅቼ አንተ ከምትፈልገው በስተቀር ሌላ አልጠይቅም፡፡ እኔ አገልጋይህና በመዳፎችህ ውስጥ ያለሁ ነኝ፡፡ የመልካም ፈቃድህን መዓዛ ለማወድ የሚችል ተግባር ለመፈፀም እንድንችል በፀጋህ እርዳኝ፡፡ በእውነቱ የእኔና የእነዚያ ወደ አንተ የመቅረቤ ዕድል የተሰጣቸው ምኖት ይህ ነውና፡፡ የዓለማት ጌታ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይሁን!
አንተ አውነትን ፈላጊ ሆይ እግዚአብሔር አይንህን እንዲከፍትልህ ከፈለግህ በእኩለ ሌሊት እግዚአብሔር መማፀን እንዲህ በማለት ወደ እርሱ መፀለይና ከእርሱ ጋር መቋረብ አለብህ፡፡
ጌታ ሆይ ÷ ፊቴን ወደ አንድነትህ መንግስት በመመለስ በምሕረትህ ባህር ውስጥ ሰጥሜአለሁ ፡፡ ጌታ ሆይ በዚህ ጨለማ ሌሊት እይታዬ የአንተን ብርሃኖች በማየት እንዲበራ አድርግልኝ በዚህም ድንቅ ዘመን በፍቅርህ ወይን ጠጅ አስደስተኝ ፡፡ ጌታ ሆይ የክብርህን ብርሃን እንዳይና ወደ ውበትህ እንድሳብ፣ ጥሪህን እንድሰማ አድርገኝ የመንግስተ ሰማይህንም በሮች በፊት ለፊቴ ክፈትልኝ፡፡
በእውነቱ አንተ ሰጪው ለጋሱ መሐሪው ይቅር ባዩ ነህና፡፡
- Bahá'u'lláh