Return to BahaiPrayers.net   Facebook

እርሱ ለጋሱ ፡ ጸጋ የተመላው ነው፤

በእውነቱ እርሱ አንዱ፡ አንድዬው የማይታው የተከበረው መሆኑን በገዛ ራሱ ሕያውነት ለመሠከረው፣ለጥንታዊው ፣ ለዘላለም ነዋሪው ለማይለወጠው፣ ለዘላለማዊው አምላክ ምስጋና ይሁን! በእውነቱ የእርሱን አንድነት በማረጋገጥ የእርሱን አንድዬነት በመቀበል ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እንመሰክራለን፡፡ እርሱ ከእርሱ ከራሱ በስተቀር ከሌላ ከማንም ገለፃ ነፃ ሆኖ፣ ወደ አቅራቢያቸው ለመድረስ በማይቻሉ ከፍታዎች፣ በላቀ ደረጃው የላቁ ከፍታዎች ላይ ለዘለዓለም ኖሮአል፡፡

እርሱ ፀጋንና በጎ ፈቃድን ለሰዎች ለመግለፅ፣ ያለምንም ሥርዓት ለማስያዝ ስለፈለገ፣ ትዕዛዛትን ገለፀ፣ ሕግጋትንም ደነገገ፣ በእነዚህም ሕግጋት መካከል የጋብቻን ሕግ መሠረተ፣ የደህንነትና የዳንም ምሽግ አደረገው፣ ከቅድስና መንግሥተ ሰማይም በተላከው በእርሱ ከሁሉም በላይ ቅዱስ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ እንድናከብረው አዘዘን፡፡ የእርሱ ክብር ታላቅ ነው! እንዲህ ይላል፣ ሰዎች ሆይ፣ በአገልጋዮቼ መካከል እኔን የሚያስታውስ ከእናንተ ይገኝ ዘንድ ተጋቡ፣ ይህ ለእናንተ ከትዕዛዞቼ መካከል አንዱ ነው፤ ለእናንተ ለራሳችሁ እንዲራዳችሁ ታዘዙት፡፡

አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን! በእውነቱ ይህ አገልጋይህና ይህች አገልጋይህ በምሕረትህ ጥላ ሥር ተሰባስበው÷ በአንተ ደግነትና ቸርነት በጋብቻ ተጣምረዋል፡፡ ጌታ ሆይ ! በዚህ ዓለምህና በመንግስትህ ውስጥ እርጃቸው በቸርነትህና በፀጋህ እያንዳንዱን መልካም ነገር አድላቸው፡፡ ጌታ ሆይ! ለአንተ በአገልጋይነታቸው ተግባር ላይ አበርታቸው፤ ለአንተ እንዲያገለግሉ፤ በዓለምህም የስምህ ምልክቶች እንዲሆኑ አድርጋቸው፤ በዚህ ዓለምና በሚቀጥለውም ዓለም በማያልቁ ችሮታዎችህ ጠብቃቸው፡፡ ጌታ ሆይ! የመሀሪነትህን መንግስት እየተማፀኑ፣ የአንድነትህንም ዓለም እርዳታ እየጠየቁ ናቸው፡፡ በእውነቱ የአንተን ትዕዛዝ በማክበር ተጋብተዋል፡፡ እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ የስምምነትና የአንድነት ምልክቶች እንዲሆኑ አድርጋቸው፣ በእውነቱ አንተ ምንም የማይሳነው፣ በሁሉ ሥፍራ የሚገኘውና ፍጹም ኃያሉ ነህና፤

የፈውስ

አምላኬ ሆይ፣ ስምህ መፈወሻ ነው፣ አንተንም ማስታወስ መድኃኒቴ ነው፡፡ ወደ አንተ መቅረብ ተስፋዬ ነው፣ ለአንተም ያለኝ ፍቅር ባልደረባዬ ነው፡፡ የአንተ ምሕረት በዚህና በሚቀጥለው ዓለም መፈወሻዬና እርዳታዬ ነው፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ለጋሱ፣ ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህና፤

በፈዋሹ በአርኪው በረዳቴ በእግዚአብሔር ስም! አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይሁን!

አምላኬና ተወዳጄ ሆይ! አቤቱ አንተ የመጨረሻ ዕድል መንግስትና ተፈፃሚ የማድረግ ሥልጣን በመዳፍህ ውስጥ ያለው ሆይ፤ በዚህ ሕመመተኛ ላይ ከእያንዳንዱ በሽታ ድክመትና ፈተና የሚያነፃውን ከምህረትህ ደመናዎች እንድታዘንብበት በመፈወሻህም ውቅያኖስ ውስጥ እንድታሰጥመው፤ ምሕረትህ ሁሉን ነገር በቀደመበት ስምህ፣ ከገጽታህ አድማስ ባበራውና ፀጋህ በእነዚያ በምድርና በሰማይ በሚገኙት ሁሉ ላይ ፍፁም በሆነበት በህቡዕ ስምህ ውበት ፀሐይ እለምንሃለሁ፡፡

በእውነቱ፣ አንተ የፈቀደውን ሁሉ አድራጊው ነህና በእርግጥም አንተ ይቅር ባዩና አዛኜ ነህና፡፡

ጌታ አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን ይህቺን ለመጠጊያ ወደ አንተ የሸሸችውን የእርሱን አንተ ራስህን በእርሱ ላይ የከሰትከውን ተገን የፈለገችውን መላ እምነተንና ተስፋዋንም በአንተ ላይ የጣለችውን ሴት አገልጋይ እንድትጠብቅ እርሱ የአንተ ውበት የሆነው በእምነትህ ዙፋን ላይ በተሰየበት ስምህ አንተም ሁሉንም ነገሮች በምትለውጥበት ሁሉንም ነገሮች አንድ ላይ በምትሰበስብበት፣ ሁሉንም ነገሮች ስለሥራቸው ልትጠይቃቸው በምትጠራበት፣ ለሁሉም ነገሮች ወሮቻቸውን በምትሰጥበት ሁሉንም ነገሮች ጠብቀህ በምታቆይበት ሁሉንም ነገሮች በሕይወት በምታኖርበት ስምህ እለምንሃለሁ፡፡

አምላኬ ሆይ እርሷ ታማ በመፈወሻህ ዛፍ ጥላ ሥር ገብታለች፡፡ ተሰቃይታ ወደ ጥበቃህ ከተማ ሸሽታለች፤ በሽተኛ ሆና የችሮታህን ምንጭ መነሻ ፈልጋለች፤ ክፉኛ ተበሳጭታ ወደ ማረጋጋትህ ምንጭ ለመድረስ በፍጥነት ገስግሳለች፤ በኃጢአት ሸክም ተጨንቃ ፊቷን ወደ ይቅር ባይነትህ መንበር መልሳለች፡፡

አምላኬና ተወዳጄ ሆይ በሥልጣንህና በፍቅራዊ ደግነትህ፣ በአዳኝ ቅባትህና በመፈወሻህ ልብስ አልብሳት፣ ከምሕረትህና ከችሮታህ ጽዋ እስክትረካ እንድትጠጣ አድርጋት፡፡ በተጨማሪም፣ ከእያንዳንዱ መከራና ሕመም፣ ከሁሉም ስቃይና በሽታ ለአንተ ከሚያስጠይፈቅ ከማንኛውም ነገር ጠብቃት፡፡

አንተ በእውነቱ ከአንተ ከራስህ በስተቀር ከሌላው ሁሉ በላይ በጣም የላቅህና የተከበርክ ነህ፡፡ በእውነቱ አንተ ፈዋሹ ፍጹም አርኪው ጠብቆ አኑዋሪው፣ ዘላለም ይቅር ባዩ፤ ከሁሉ በላይ መሐሪው ነህና፡፡

አምላኬ ሆይ አንተ በስሞቹ ሕመምተኞች የሚፈወሱት በሽተኞችም የሚድኑት፣ የተጠቀሙትም የሚረኩት ክፉኛ የተበሳጩትም የሚረጋጉት መንገድ የሳቱትም የሚመሩት የተዋረዱትም የሚከበሩት ድሆችም የሚበለጽጉት አላዋቂዎችም ዕውቀት የሚያገኙት፣ የተከዙትም የሚደሰቱት ኃዘንተኞችም የሚጽናኑት፣የቀዘቀዙትም የሚሞቁት የተረገጡትም ከፍ የሚደረጉት ነህ፡፡ አምላኬ ሆይ በስምህ አማካይነት የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ተቀሰቀሱ፣ሰማያትም ተዘረጉ ምድርም ተመሠረተች፤ ደመናዎቹም እንዲንሳፈፉና በምድር ላይ እንዲያዘንቡ ተደረጉ፡፡ ይህም በእውነቱ ለፍሮችህ ሁሉ የአንተ ፀጋ ምልክት ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ ሌሊት በዚህ አንተ በፍጥረትህ መንግስት ከአንተ ፍፁም ክብር የተመላ ህልውና ጋር በአዛመድኽው ሕፃን ላይ ከምሕረትህ ደመናዎች የመፈወሻህን ዝናቦች እንድታዘንብበት አንተ አምላክነትህን በከሰትህበት እምነትህንም ከፍጥረት ሁሉ በላይ ከፍ በአደረግህበት ስምህ፣ የአንተ ከሁሉ የላቁ ስያሜዎችና ከሁሉም በላይ የተከበሩ ባህርያት የአንተ ከሁሉ የላቀውና ከሁሉም በላይ የተከበረው ሕያውነት በሚወደስባቸው ባህርያት ሁሉ እማፀንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ በአንተ ፀጋ በደህንነትና በጤና ልብስ አልብሰው አቤቱ አንተ ተወዳጄ ሆይ ከእያንዳንዱም ስቃይና ሕመም ለአንተም ከሚያስጠላው ከማንኛውም ነገር ጠብቀው በእውነቱ የአንተ ኃያልነት ለሁሉም ነገሮች ብቁ ነው፡፡ በእውነቱ አንተ ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው በገዛ ራሱም ነዋው ነህ፡፡ ከዚህም በላይ አምላኬ ሆይ የዚህንና የሚቀጥለውን ዓለም መልካም ነገሮች የቀድሞዎችንም የኋለኞችንም ትውልዶች መልካም ነገሮች ሁሉ ላክለት፡፡ በእውነቱ የአንተ ኃይልነትና የአንተ ጥበብ ለዚህ ሁሉ ብቁ ናቸውና፡፡

ጌታ አምላኬ ሆይ፤ ክብር ለአንተ ይሁን ተማጽኜሃለሁ እርሱን አንተን በጽናት በመያዝ ወደ አንተ የተመለሰውን በምሕረትህም ላይ የተንጠላጠለውን የፍቅራዊ መለኮታዊ ጥበቃህንም ዘርፍ አጥብቆ የያዘውን ከማንኛውም አደጋ እንድትጠብቀው በእርሱ አማካይነት የአንተን መርሐ ግርማዎች ከፍ በአደረግህበት፣ የፍቅራዊ ደግነትህንም ብርሃን በአበራህበት፣ የጌታነትህንም ሥልጣን በገለጽህበት፣ የስሞችህም ፋኖስ በባህርያትህ መቅረዝ ላይ በተከሰተበት እርሱም የአንድነትህ መቅደስና የመላቀቅ ክስተት የሆነው በአበራበት፣ የአንተ መርሐ ጎዳናዎችም በታወቁበት የበጎ ፈቃድህም መንገዶች በተቀየሱበት የስህተት መሠረቶች እንዲንቀጠቀጡ የክፋት ምልክቶችም እንዲጠፉ በተደረጉበት የጥበብ ምንጮችም በፈለቁበት መንግስተ ሰማያውያም ገበታ ከላይ በተላከበት፣ አገልጋችህንም ጠብቀህ በአኖርክበትና ፈውስህንም በለገስክበት ፣ ለአገልጋችህ ርህራሄ የተመላበት ምሕረትህን በአሳየህበትና በፍጡራንም መካከል ይቅር ባይነትህን በገለፅክበት ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡ እንግዲህ ፈውስህን ላክለት፣ የተሟላም አድርገው በአንተ የተለገሰ ጽናት በከፍተኛነትህም የተበረከተ መረጋጋት አጎናጽፈው፣

በእውነቱ አንተ ፈዋሹ አኑዋሪው ረዳቱ ፍጹም ኃያሉ ኃይል የተሞላው፣ ንዑዱ ሁሉን አዋቂው ነህና፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! በበረከትህ ውሀዎች አማካይነት ከእያንዳንዱ ስቃይና የጤና መቃወስ፣ ከማናቸውም ድክመትና አቅመ ቢስነት ሁሉ እንድታነፃኝ፣ በመፈወሻህ ውቅያኖስም በፀጋህ የቀኑ ኮከብ ብርሃን ውበትም÷ አገልጋዮችህን በአስገበርክበት ስምህም÷ ከሁሉ በላይ በተከበረው ቃልህ ሁሉን የሚናኝ ኃይልም÷ ከሁሉ በላይ ግርማ በተመላው ብዕርህ ሁሉን ቻይነትም፣ በሰማይና በምድር ከሚገኙት ሁሉ መፈጠር በቀደመው ምሕረትህም እለምንሃለሁ፡፡

ጌታዬ ሆይ ተማፀኝህ በበረከትህ በር ላይ ሲጠባበቅ፣ እርሱ ተስፋውን በአንተ ላይ ያደረገውም በቸርነትህ ገመድ ላይ ተንጠላጥሎ ታየዋለህ፤ እር ከፀጋህ ውቅያኖስና ከፍቅራዊ ደግነትህ የቀኑ ኮከብ የሚፈልጋቸውን ነገሮች እንዳትነፍገው እማፀንሃለሁ፡፡

አንተ የሚያስደስትህን ለማድረግ ኃይል አለህ፡፡ ከአንተ ከምንጊዜም ይቅር ባዩ ከፍፁም ቸሩ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac