Return to BahaiPrayers.net   Facebook

ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ የተከበርክ ነህ! ለእኔና የአንተን ገጽ ለማየት ለፈለጉት ሁሉ ከቸርነትህና በረከት ከተመላበት ፀጋህ መስጠቱ የሚጠበቀውን ከስጦታዎችህና ከችሮታዎችህ መለገሱም ተገቢ የሆነውን እንድትልክልን በኃይል በሚነፍሱት የፀጋህ ነፋሶች በእነዚያም በዓላማህ ንጋቶችና በመንፈሳዊ የእውቀት ብልጭታህ የንጋት ሥፍራዎች በሆኑት እማፀንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ÷ እኔ ምስኪንና ጉስቁል ነኝ! በሀብትህ ውቅያኖስ ውስጥ አስጥመኝ፣ የተጠማሁ ነኝ ከፍቅራዊ ደግነትህ የህይወት ውሃዎች እንድጠጣ አድርገኝ፤

አገልጋችህን ፀጋ በተመላበት አምላካዊ ጥበቃህ ዛፍ ጥላ ሥር በአንድ ላይ እንድትሰበስባቸው÷ በአንተው በራስህና በእርሱ የአንተ የራስህ ህልውና ክስተትና በሰማይና በምድር ለሚገኙት ሁሉ ክፉውን ከበጎ የሚለይ ቃልህ አድርገህ በሰየምከው እማፀንሃለሁ፡፡ ከፍሬዎቹ እንዲሳተፉ ÷ወደቅጠሎቹ መንኮሻኮሽ÷ከቅርንጫፎቹ ላይ ወደሚያዜመውም ወፍ ድምጽ ጣፋጭነት ጆሮዎቻቸውን እንዲያቀኑ እርዳቸው፡፡ በእውነቱ÷ አንተ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ÷ የማይደረስበቱ÷ ፍጹም ኃያሉ÷ ከሁሉም በላይ ፀጋ የተመላው ነህና፤

አቤቱ አንተ መሐሪው አምላክ ሆይ! አቤቱ አንተ ኃያልና ሃይል የተመላው ሆይ! አቤቱ አንተ ከሁሉም በላይ ለጋስ አባት ሆይ! እነዚህ አገልጋዮች ወደ አንተ ተመልሰው በአንተ ደጀሰላም ለመማፀን÷ ከአንተ ታላቅ መተማመኛ የአንተን የማያልቁ በረከቶች ለመለመን በአንድ ላይ ተሰባስበዋል፡፡ እነርሱ ከአንተ መልካም ደስታ በስተቀር ሌላ ዓላማ የላቸውም፡፡ የሰውን ዘር ዓለም ከማገልገል በስተቀር ሌላ ዕቅድ የላቸውም፡፡

አምላክ ሆይ! ይህን ስብሰባ ብሩህ አድርገው ልቦችን መሐሪዎች አድርጋቸው፡፡ የቅዱስ መንፈስን በረከቶች አውርድላቸው፤ የመንግስተ ሰማይ ኃይል አጎናጽፋቸው፣የመንግስተ ሰማይ አእምሮዎች በመስጠት ባርካቸው፤ በሙሉ ትሕትናና ፀፀት በተመላበት ልብ ወደ አንተ መንግስት በመመለስና ለሰው ዘር ዓለም አገልግሎት በመስጠት ሥራ እንዲጠመዱ ቅንነታቸውን አብዛ፡፡ እያንዳንዱ ብሩህ ሻማ ይሁን፡፡ እያንዳንዱ አንፀባራቂ ኮከብ ይሁን፡፡ እያንዳንዱ በአምላክ መንግስት ውስጥ ውበት የተመላ ቀለምና አስደሳች መዓዛ ያለው ይሁን፡፡

አቤቱ አንተ ለጋስ አባት ሆይ !ቡራኬዎችህን አጎናጽፈን፣ ጉድለቶቻችንን አትመልከት፡፡ በጥበቃህ መጠለያ ሥር ጠልለን፡፡ ኃጢአቶቻችንን አትመልከት፡፡ በምሕረትህ ፈውሰን እኛ ደካሞች ነን አንተ ግን ኃያል ነህ፡፡ እኛ ምስኪኖች ነንሀ አንተ ግን ሀብታም ነህ፡፡ እኛ ሕሙማን ነን፤አንተ ደግሞ ሐኪም ነህ፡፡ እኛ ችግረኞች ነን አንተ ግን ከሁሉ በላይ ቸር ነህ፡፡

አምላክ ሆይ! ሀብትህን አጎናጽፈን፡፡ አንተ ኃይል የተመላው ነህ፡፡ አንተ ሰጪው ነህ አንተ ለጋሱ ነህ፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac