Return to BahaiPrayers.net
Facebook
ጌታ ሆይ ! ይህን ወጣት ብሩህ አድርገው፤ በዚህ ምስኪን ፍጡር ላይ በረከትህን አውርድ፤ ዕውቀትን ለግሰው በየዕለቱም ጥዋት ተጨማሪ ጉልበት ስጠው፤ ክስሕተት ነፃ ይሆን ዘንድ፣ ለእምነትህ አገልግሎት ራሱን ይሰጥ ዘንድ የተሳሳቱትን እንዲመልስ ዕድለ ቢሶቹንም እንዲመራ ምርኮኞቹን ነፃ እንዲያወጣ ግዴለሾቹንም እንዲያነቃቃና ሁሉም አንተን በማስታወስና በማወደስ ይባረኩ ዘንድ በጥበቃህ መጠለያ ውስጥ ጠብቀው፡፡ አንተ ኃያሉና በሁሉ ላይ ስልጣን ያለው ነህና፡፡
አቤቱ አንተ ሩኅሩህ ጌታ ሆይ! ለዚህች የመንግስተ ሰማይ ልጅ መለኮታዊ ማረጋገጫን ለማግሳት በእምነትህ ጠንካራና ፅኑ ሆና ትኖር ዘንድ፣ ልክ በምስሥጢራት የጽጌረዳ አትክልት ሥፍራ እንደምትገኝም ዘማሪ ወፍ፣ በአብሃ መንግስት በእጅግ በጣም ድንቅ ድምጽ ዜማዎችን ታዜም ዘንድ፣ በዚህም ለእያንዳንዱ ሰው ደስታን ታመጣ ዘንድ፣ በፀጋህ እርዳታ በመንግስተ ሰማይ ሴት ልጆች መካከል ከፍ አድርጋት፣ ለዘለዓለማዊው ሕይወትም አብቃት፤
አንተ ለጋዙ ሁሉን አፍቃሪው ነህና፣
አቤቱ አንተ ከሁሉም በላይ ክብር የተመላህ ጌታ ሆይ ይህችን የአንተን ትንሽ ሴት አገልጋይ ብሩክና ደስተኛ አድርጋት፣በታላቅ ደስታና በከፍተኛ ሐሴት የተመላች በመሆን ጣፋጭ ሽታ ያለው መዓዛ ታሰራጭ ዘንድ በአንድነትህ ደጀሰላም የተወደደች እንድትሆንና ከፍቅርህ ጽዋ እስትረካ እንድትጠጣ አድርጋት፣ አንተ ኃያሉና ኃይል የተመላው ነህና፣ አንተ ሁሉን አዋቂው፣ ሁሉን የሚያየው ነህና፤
ጌታ ሆይ! ይህቺን የእግዚአብሔር መንግስት ልጅ በሁለቱም ዓለማት የተከበረች እንድትሆን እርዳት፣ ከዚህ ከጠፊ የትቢያ ዓለምና ልቦቻቸውን በዚያ ላይ ከአሳረፉት ፊቷን እንድታዞር አድርጋት ከሞት አልባ ዓለም ጋር ግንኙነትና ጥብቅ ትስስር ያላት ለመሆን አስችላት፤ አንተን ለማገልገል ትነሣ ዘንድ መንግስተ ሰማያዊ ኃይል ስጣት፣ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋሶችም አጠንክራት፤
አንተ ኃያሉ ነህ፤
- Bahá'u'lláh