Return to BahaiPrayers.net
Facebook
አቤቱ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የእውነተኛ አፍቃሪዎችህን ግንባር አብራላቸው፣ የተረጋገጠ ድል በሚያስገኙ መልአካዊ ሠራዊትም ደግፋቸው የእምነትህን ደህንነት በመጠበቅ፣ እምነታቸውን በአንተ ትዝታ ላይ በማድረግ ልቦቻቸውን ለአንተ ፍቅር በመስጠት፣ ውበትህን በማወደስና አንተን የሚያስደስቱበትን መንገድ በመፈለግ ለሀብታቸው ሳይሳሱ የለገስካቸውን ሁሉ በጎዳናህ በማዋላቸው፣ እግሮቻቸውን በቀጥተኛው መንገድህ ላይ አበርታላቸው ከጥንታዊው ቸርነትህም የቡራኬዎችህን በሮች ክፈትላቸው፤
ጌታዬ ሆይ! የተትረፈረፈ ድርሻ፣ የተመደበ ካሣና የተረጋገጠ ሽልማት እዘዝላቸው፤
በእውነቱ አንተ ደጋፊው ረዳቱ ለጋሱ በረከት የተመላው፣ዘለዓለም ሰጪው ነህና፤
- Bahá'u'lláh