Return to BahaiPrayers.net   Facebook

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ÷ በፀጋህና በቸርነትህ ኃዘኔን አጥፋ በሉዓላዊነትህና በኃይልነትህ ሥቃዬን አስወግድ፣ አምላኬ ሆይ÷ ኃዘን ከየአቅጣጫው በከበበኝ ጊዜ ፊቴን ወደ አንተ ሳቀና ትመለከተኛለህ፡፡ አቤቱ አንተ የፍጡራን ሁሉ ጌታ፣ ለሚታዩና ለማይታዩት ነገሮች ሁሉ ጥላና ከለላ የሆንከው ሆይ! ከእነዚያ ፎቶቻችውን ወደ አንተ ከመመለስ ከቶ ምንም ከማያግዳቸው ጋር ትቆጥረኝ ዘንድ÷ የሰዎችን ልቦችና ነፍሶች በገዛው ስምህ÷ በምሕረትህ ውቅያኖስ ማዕበልና በፀጋህ የቀኑ ኮከብ ድምቀት እማጠንሃለሁ፡፡

ጌታዬ ሆይ÷ በቀናትህ የደረሰብኝን አንተ ትመለከታለህ፡፡ አንተን ለማገልገል ለመነሣትና ባህርያትህን ለማሞገስ የሚያስችለኝ ታዝልኝ ዘንድ በእርሱ የስሞችህ ጎሕና የባህርያትም የንጋት ሥፍራ በሆነው እማጠንሃለሁ፡፡ አንተ በእውነቱ ፍጹም ኃያሉ÷ ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው፣የሰዎችን ሁሉ ፀሎት ሰሚው ነህና፡፡

በመጨረሻም ተግባሬን ሁሉ ትባርክልኝ ከኃጢአቴም ታነፃኝ ፍላጎቴንም ታሟላልኝ ዘንድ በገጽህ ብርሃን እለምንሃለሁ፡፡ አንተ ለስልጣንህና ለገዥነትህ እያንዳንዱ አንደበት የመሰከረልህ እያንዳንዱ የሚገነዘብ ልብ ስለ ግርማህና ስለ ሉዓላዊነትህ ያወቀልህ ነህና፡፡ የጠየቁህን ከምትሰማው መልስም ለመስጠት ከማትቆጠበው ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

ከእግዚአብሔር በስተቀር ችግርን የሚያስወግድ አለ ወይ? በል፡- ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው! እርሱ አምላክ ነው! ሁሉም አገልጋዮቹ ናቸው፡ ሁሉም በትዕዛዙ ይኖራሉ፤

አቤቱ አንተ በመከራዬ ጊዜ ማረፊያዬ! በጭንቀቴም ጊዜ ጋሻዬና መከታዬ፣ በችግር ጊዜ መጠጊያዬና መሸሻዬ! በብቸኝነቴም ጊዜ ባልደረባዬ! በኃዘኔ ጊዜ መጽናኛዬ! በጓደኛ -ቢነቴም ጊዜ አፍቃሪ ጓደኛዬ! የኃዘኔን ሥቃይ የምርቃት ኃጢአቴንም ይቅር የምትል ጌታ አምላኬ ሆይ!

በዚህ በመለኮታዊ አንድነትህ ዘመን የአንተን ፈቃድ ከሚቃወም ነገር ሁሉ እንድትከልለኝ እንከን የሌለብኝና ያልተበከልኩ ሆኜ ፀጋህን ዛፍ ጥላ እንዳልፈልግ እንቅፋት ከሚሆንብኝ ርኩሰት ሁሉ እንድታነፃኝ፣ ሙሉ በሙሉ ወደ አንተ በመዞር በሙሉ ልቤ አዕምሮዬና አንደበቴ በጋለ ስሜት እማፀንሃለሁ፡፡

ጌታ ሆይ በደካማው ላይ ምሕረት ይኑርህ፤ በሽተኛውንም ፈውስ፣ የሚያቃጥለውንም ጥም አርካ፡፡ የፍቅርህ እሳት የሚጋጋበትን ልብ ደስ አሰኘው፣በመንግስተ ሰማያዊ ፍቅርህና መንፈስህ ነበልባል አንድደው፡፡

የመለኮታዊ አንድነት መቅደሶችን በቅድስና ካባ አጎናጽፋቸው ፣የቸርነትህንም ዘውድ በራሴ ላይ ድፋልኝ፡፡

ፊቴን በፀጋህ ሉል ብርሃን አብራልኝ፣ በቅድስናህም ደጀሰላም አገልግሎት ዘንድ በቸርነትህ እርዳኝ፡፡

ልቤ ለፍጡራንህ በሚኖረው ፍቅር እንዲጥለቀለቅ አድርገው፣የምህረትህ ምልክት፣ የፀጋህ መታወቂያ፣በተወዳጆችህ መካከል ስምምነት አስፋፊ፣ ለአንተ ያደርኩ፣ ያንተን ትዝታ የማወሳ፣ ራሴንም ረስቼ ያንተ የሆነውን ሁሉ የማስታወስ እንድሆን ፈቃድህ ይሁን፡፡

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ የይቅርታህንና የፀጋህን ልዝብ ነፋስ አታርቅብኝ፣ ከረዳትነትህና ከፍቅርህ ምንጭ አትንሳኝ፤ በጠባቂ ክንፎችህ ጥላ ሥራ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፣ የፍጹም ጠባቂ አይንህን እይታ አሳርፍብኝ፡፡

ስምህን በሕዝብህ መካከል እንዳወድስ፣ ድምጼም በታላላቅ ጉባኤዎች ላይ ከፍ እንዲል፣ ከከናፍሮቼም የአንተ ምስጋና ጎርፍ እንዲፈስ ምላሴን አፍታታ፡፡ አንተ በእውነቱ፣ ፀጋ-የተመላው የተመሰገነው፣ ኃያሉ፣ ምንም የማይሳነው ነህና!

ጌታዬ ተወዳጄ፣ ፍላጎቴ ሆይ! በብቸኝነቴ ጊዜ ተጎዳኘኝ በግዞቴም ጊዜ አብረኽት ሁን፤ ኃዘኔን አስወግድልኝ፣ ለውበትህም ያደርኩ አድርገኝ፣ ከአንተ በስተቀር ከሌላው ነገር ሁሉ አግልለኝ፣ በቅድስናህም መዓዛ ወደ አንተ ሳበኝ፡፡ በመንግስትህም ውስጥ ውሎዬን ከእነዚያ ከአንተ በስተቀር ከሌላው ነገር ሁሉ ከተላቀቁት፤ የአንተንም ቅዱስ ደጀሰላም ለማገልገል ከሚናፍቁትና በእምነትህ ከፀኑት ጋር እንድጎዳኝ አድርገኝ፤ ለመልካም ፈቃድህ ከበቁት ሴት አገልጋዮችህ አንዷ ለመሆን አስችለኝ፡፡ በእውነቱ አንተ ፀጋ የተመላው ለጋሱ ነህና፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac