Return to BahaiPrayers.net   Facebook

….. ኃጢአትንና በደልን በሰዎች ፊት መናዘዝ….. አይፈቀድም፡፡ ኃጢአተኛው በራሱና በአምላክ መካከል እንዲህ በማለት ከምሕረት ውቅያኖስ ምህረትን መማፀን ከቸርነትህም ሰማይ ይቅርታን መለመን አለበት፡፡

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ለእኔም ለአባቴም ለእናቴም ይቅርባ ባይነትህን ትፈቅድልን ዘንድ በጣፋጭ ቃላትህ በጣም በመመሰጣቸው የክብር ከፍታ ቁንጮ ወደሆነው ፣ ወደ እጅግ በጣም ታላቅ ሰማዕትነት ስፍራ በፍጥነት በገሠገሡት በእውነተኞች አፍቃሪዎችህ ደም እማለድሃለሁ፤ በዕውቀትህ ውስጥ ተሸፍነው በሚገኙት ምስጢራትና በበረከትህ ውቅያኖስ ውስጥ በተቀመጡት ዕንቁዎችም እማፀንሃለሁ፡፡ ከእነዚያ ምሕረትን ከሚያሳዩት አንተ በእውነቱ ከሁሉም በላይ መሀሪው ነህ፡፡ ከአንተ ከዘለዓለም ይቅር ባዩ ፍጹም በረከት ከተመላው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

ጌታ ሆይ! ይህ የኃጢአተኛነት ሕልውና ወደ ልግስናህ ውቅያኖስ ፊቱን ሲመልስ፣ ይህም ደካማው የመለኮታዊ ኃይልህን መንግስት ሲመልስ ይህም ደካማው የመለኮታዊ ኃይልህን መንግስት ሲሻ ይህም ድሀው ፍጡር ራሱን ወደ ሀብትህ ቀኑ ኮከብ ሲያዘነብል ታየዋለህ፡፡ ጌታ ሆይ በምሕረትህና በፀጋህ እርሱ የለመነህን አትንሳው ከበረከትህም ግልፀቶች አትከልክለው፣ በሰማይህ ውስጥና በምድርህ ላይ ለሚኖሩት ሁሉ በሰፊው ከከፈትከው በርህም አታብርረው፡፡

እግዚኦ! እግዚኦ ኃጢአቶቼ ወደ ቅድስናህ መንበር ከመቅረብ ከልክለውኛል፤ በደሎቼም ከግርማ ሞገስህ ድንኳን በጣም ርቄ እንድጠጋ አድርገውኛል፡፡ አንተ እንዳላደርግ የከለከልከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድፈጽመው ያዘዝከኝን አልፈፀምኩም፡፡

ወደ አንተ ለመቅረብ የሚያስችለኝን በበረከትህ ብዕር ትጽፍልኝ ዘንድ በኔና በይቅርባይነትህ በይቅርታህም መካከል ከተጋረጡት በደሎቼም ታነፃኝ ዘንድ፣ በእርሱ የስሞች ሉዓላዊ ጌታ በሆነው እለምንሃለሁ፡፡ በእውነቱ አንተ ምንም የማይሳነው በረከት የተመላው ነህና፡፡ ከአንተ ከኃያሉ፣ ፀጋ ከተመላው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

ጌታ አምላኬ ሆይ ፣ አንተ የተከበርክ ነህ ስለ አንተ ለማውሳት በሞከርኩ ቁጥር በከባድ ኃጢአቶቼና በአንተ ላይ በፈፀምኩአቸው አሳዛኝ በደሎቼ እገታለሁ፣ ከፀጋህም ሙሉ በሙሉ ተነፍ ጌ፣ የአንተን ምስጋና ለማወደስም ፍጹም ኃይል፣ አልባ ሆኜ እገኛለሁ፡፡ ሆኖም በፀጋህ ላይ ያለኝ ታላቅ እምነት፣ በአንተ ላይ ያለኝን ተስፋ ያድስልኛል፣ አንተ ቸርነት በተመላበት ሁኔታ እንደምትለግሰኝ ያለኝ እርግጠኝነትም እንዳወድስህና አንተ ያለህን ነገሮች ሁሉ ከአንተ እንድለምን ያደፋፍረኛል፡፡

አምላኬ ሆይ ልቤ ለክፋት የተጋለጠ ስለሆነ፣ ለራሴ እዳትተወኝ፣ በስሞችህ ውቅያኖሶች የሰጠሙት ሁሉ በሚመሠክሩለት፣ ከተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ብዛት አልፎ በሚገኘው ምሕረትህ እማፀንሃለሁ፡፡ ስለዚህ በመከላከያህ ምሽግና በእንክብካቤህ መጠለያ ውስጥ ጠብቀኝ፣ አምላኬ ሆይ፣ እኔ ብቸኛ ፍላጎቱ አንተ በኃያልነትህ ስልጣን የወሰንከው የሆነው ነኝ፤ እኔ ለራሴ የመረጥኩት ፀጋ በተመላበት ትዕዛዝህና በፈቃድህ ውሳኔ ለመደገፍ፣ በድንጌጌህና በፍርድህ ምልክቶችም እንድታገዝ ብቻ ነው፡፡

አቤቱ አንተ የእነዚያ አንተን የሚናፍቁት ልቦች ተወዳጅ የሆንከው ሆይ፣ ወደ አንተ ቅዱስ መንበር፣ ወደ አንተ ደጀሰላምና ወደ አንተ ቤተ-መቅደስ ከመቅረብ እንዳትነፍገኝ፣ በእምነትህ ክስተቶ በዕውቀት-ብልጭታህም ንጋቶች በግርማህም መገለጫዎች ፣በዕውቀትህም ግምጃ ቤቶች እማፀንሃለሁ፤ ጌታዬ ሆይ ወደ እርሱ ቅዱስ መንበር እንድደርስ፣ በእርሱም ስብዕና ዙሪያ እንድዞር፣ በእርሱም ደጃፍ ፊት በትህትና እንድቆም እርዳኝ፡፡

አንተ ስልጣኑ ከእምቅድመ-ዓለም እስከ ዘለዓለም የሚኖረው ነህ፡፡ ምንም ነገር ከዕውቀትህ አያመልጥም፡፡ አንተ በእውነቱ የስልጣን አምላክ የክብርና የጥበብ አምላክ ነህ፡፡

የዓለማት ሁሉ ጌታ የሆነው፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡

አቤቱ አንተ አምላኬና የሁሉ ነገሮች አምላክ፣ ክብሬና የሁሉ ነገሮች ክብር፣ ፍላጎቴና የሁሉ ነገሮች ፍላጎት ብርታቴና የሁሉ ነገሮች ብርታት፣ ንጉሴና የሁሉ ነገሮች ንጉስ-ጌታዬና የሁሉ ነገሮች ባለቤት ዓላማዬና የሁሉ ነገሮች ዓላማ፣ አንቀሳቃሼና የሁሉ ነገሮች አንቀሳቃሽ የሆንከው ጌታ ሆይ፣ ስምህ የተወደሰ ይሁን! ከፍቅራዊ ምሕረቶችህ ውቅያኖስ እንድከለከል፣ ከቅርበትህ ዳርቻዎችም እንድርቅ እንዳታደርገኝ እማጠንሃለሁ፡፡

ጌታዬ ሆይ፣ ከአንተ በቀር ሌላ ማንኛውም ነገር አይጠቅመኝም፣ ወደ አንተ በቀር ወደ ማንም መቅረቡም ምንም አይረዳኝም፣ ከእነዚያ ፊቶቻቸውን ወደ አንተ አቅጣጫ ከአቀኑትና፣ አንተን ለማገልገል ከተነሱት ጋር እንድትቆጥረኝ፣ ከአንተ ከራስህ በስተቀር ማንኛውም ነገር እንዳያስፈልግህ በአደረግህባቸው ሀብቶቻችህ ብዛት እማጠንሃለሁ፡፡

እንግዲህ ጌታዬ ሆይ አገልጋዮችህንና ሴት አገልጋዮችህን ይቅር በላቸው፡፡ በእውነቱ አንተ ምንጊዜም ይቅር ባዩ ከሁሉም በላይ ሩኅሩኁ ነህና፡፡

ጌታ ሆይ፤ ምስጋና ለአንተ ይሁን ኃጢአታችንን ቅር በለን፣ በእኛ ላይ ምሕረት ይኑርህ፡፡ ወደ አንተም ለመመለስ አስቸለን፡፡ በአንተ ላይ በቀር በሌላ በምንም ላይ እንዳንተማመን አድርገን በፀጋህ አማካይነት፣ ያንን አንተ የምትወደውንና የምትሻውን ከአንት በጣም የሚጠበቀውን ስጠን፡፡ የእነዚያን በእውነት ያመኑትን ደረጃ ከፍ አድርግ ፀጋ በተመላበት ይቅር ባይነትህም ይቅር በላቸው በእውነቱ አንተ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ በገዛ ራሱም ነዋሪው ነህና፤

ጌታዬ ሆይ አቤቱ አንተ የጌቶች ጌታ እርሱ ተፈላጊውን የሚሰጠውና በሮቹን ሁሉ የሚከፍተው የሆንከው ሆይ የአንተን ስም ለማንሳት በቀር ለእያንዳንዱ ሌላ ስም ማንሳት ለአንተ ውዳሴም በቀር ለእያንዳንዱ ሌላ ውዳሴ በቅርበትህ ምክንያት ከተደሰትኩት ደስታም በቀር ለእያንዳንዱ ሌላ ደስታ፣ ከአንተ ጋር በመቋረብ ምክንያት ለአገኘሁት እርካታም በቀር ለእያንዳንዱ ሌላ እርካታ ለፍቅርህና ለመልካም ደስታህም ሐሴት በቀር ለእያንዳንዱ ሌላ ሐሴት ከአንተ ጋር ምንም ግንኙነት ለሌላቸው ከእኔ ጋር ግንኙነት ለነበራቸው ነገሮች ሁሉ ቅርታ እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ፡፡

አቤቱ አንተ ፍጹም ኃያል አምላክ ሆይ ! እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፣ አንተ ግን ይቅርባይ ነህ! እኔ ጥፋቴ የበዛ ነው፣ አንተ ግን ሩኅሩህ ነህ፣ እኔ በስሕተት ጨለማ ውስጥ ነኝ፣ አንተ ግን የምህረት ብርሃን ነህ!

አቤቱ አንተ ለጋሥ አምላክ ሆይ! ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፣ በረከትህን አውርድልኝ፣ ስሕተቴን አትመልከት፣ መጠለያ ስጠኝ በትዕግስትህ ምንጭ ውስጥ አስጥመኝ፣ ከማናቸውም ደቄና በሽታም ፈውሰኝ፡፡

አንፃኝ ቀድሰኝ፣ ኃዘንና ትካዜ እንዲጠፉ፣ ፍስሐና ሐሴት እንዲወርዱ፣ ከሚጎርፈው ቅድስናህ አካፍለኝ፡፡ ጭንቀትና ተስፋ ማጣት በደስታና በታማኝነት እንዲለወጡ አድርግልኝ፣ በፍርሐትም ፈንታ ልበ ሙሉነት እንዳገኝ ፈቃድህ ይሁን፡፡

በእውነቱ አንተ ይቅር-ባዩ- ሩኅሩኁ ለጋሱና ተወዳጁ ነህና፡፡

አምላኬ ሆይ! በጭካኔያቸው፣ በተሳሳተ ስራቸውና በሚያደርጉት ተንኮል ሁሉ የዋሃን በመሆናቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር ትላቸው ዘንድ በአፌም በልቤም እለምንሃለሁ፡፡ ክፉውን ከደጉ፣ ስሕተቱን ከትክክለኛው፣ፍትሕን ከፍርድ ማጓደል ለይተው ሳያውቁ የራሳቸውን ፍላጎት ያደርጋሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል በጣም የተሳሳተውን ሰው ይከተላሉ፤ አምላክ ሆይ ምህረትን አውርድላቸው፣ በዚህ በችግር ዘመን ከመከራ ሁሉ ጠብቃቸው፡፡ ይህ ሁሉ መከራና ችግር ለዚህ በጨለማ ጉድጓድ ለተጣለው አገልጋይህ ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፡፡ ማናቸውንም ኃዘን ሁሉ ለእኔ አድርገው፡፡ ለተወዳጆችህም ሁሉ መስዋዕት ለመሆን እብቃኝ ለታላቅነትህ ወሰን የሌለው አምላክ ሆይ፣ ነፍሴ ህይወቴ መላው ሰውነቴ፣ መንፈሴም ስለ እነርሱ መስዋዕት ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ አምላኬ ሆይ የበደሉኝን፣ ያደሙብኝንና ፍርድንም ያጓደሉብኝን ሁሉ ይቅር እንድትላቸው፣ እኔ ዝቅተኛው አገልጋይህ በግንባሬ ተደፍቼ እለምንሃለሁ፡፡ መልካም ችሮታህን ናቸው፣ ደስታን ስጣቸው ከኃዘን አድነህ ሰላምንና ብልጽግናን አድላች፣ ታላቅ ደስታን ስጣቸው፤ በረከትህንም አውርድላቸው፤ አንተ ራሱን ችሎ ነዋሪው ኃያሉ፣ በአደጋ ጊዜም ረዳቱ ነህና፤

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac