Return to BahaiPrayers.net   Facebook

አምላኬ ሆይ! አምላኬ ሆይ! የአገልጋዮችህን ልብ አስተባብር፤ ታላቁን ዓላማህንም ግለጽላቸው፤ ትዕዛዝህን ይከተሉ፣ በሕግህም ይኖሩ ዘንድ፣ አምላክ ሆይ በጥረታቸው እርዳታቸው ለአንተም እንዲያገለግሉ ኃይልን ስጣቸው፣ አምላክ ሆይ! ራሳቸውን ለራሳቸው አትተው፤ እርምጃቸውን ሁሉ በዕውቀት ብርሃን ምራው፣ በፍቅርህም ልቦቻቸው አስደስት፡፡ በእውነቱ አንተ ረዳታቸውና ጌታቸው ነህና፡፡

የአንድነት ብርሃን መላዋን ዓለም እንዲያለብሱና “መንግስት የአምላክ ናት ” የሚለውም ማኅተም በሕዝቦቿ ሁሉ ግንባር ላይ እንዲታተም የአምላክ ፈቃድ ይሁን፡፡

አምላክ ሆይ! አምላኬ ሆይ! በእውነቱ ምህረቶችህ ሁሉ በእነዚህ ነፍሶች ላይ እንዲወርዱ አንተን በመጠየቅ እለምንሃለሁ፡፡ በደጀ ሰላምህ ፊት ሆኜ እማፀንሃለሁ፣ ለችሮታህና ለእውነትህ ምረጣቸው፡

ጌታ ሆይ! ልቦችን በማስተባበር አስተሳስራቸው፣ ነፍሶችን ሁሉ በስምምነት አጣምራቸው፣ መንፈሶችንም በቅዱስነትህና በአንድነትህ ምልክቶች አስደስታቸው፤ ጌታ ሆይ! እነዚህን ፊቶች በአንድነት ብርሃን አማካይነት ብሩህ አድርጋቸው፡፡ ለመንግስትህ እንዲያገለግሉ የአገልጋዮችህን ሽንጦች አጠንክርላቸው፡፡

አቤቱ አንተ ወሰን የሌለው ምሕረት ባለቤት የሆንከው ጌታ ሆይ! አቤቱ የኃጢአት ስርየትና የይቅርታ ጌታ ሆይ! ኃጢአቶቻችንን አስተሰርይልን ስለጉድለቶቻችንም ይቅርታ አድርግልን፣ ወደ ኃያልነትና ወደ ሥልጣን መንግስት በመፀለይ በመንበርህ ቅርበት ትሑታን፣ በማስረጃዎችህም ክብር ፊት ታዛዦች በመሆን ወደ ምህረትህ መንግሥት ፊቶቻችንን እንድንመልስ አድርገን፡፡

አቤቱ ጌታ አምላክ ሆይ! በፍቅርህ በረከት እንደ ባህር ማዕበሎች እንደ አትክልት ሥፍራ አበቦች የተባበርንና የተስማማን እንድንሆን አድርገን፡፡ ጌታ ሆይ! በአንድነትህ ምልክቶች አማካይነት ልቦችን አስፋቸው፣ የሰው ዘርንም ሁሉ ከአንድ አይነት የክብር ከፍታ እንደሚያበሩ ከዋክብት፣ በሕይወት ዛፍህ ላይ እንደሚያድጉ ፍጹማን ፍሬዎች አድርጋቸው፡፡

በእውነቱ፣ አንተ ፍጹም ኃይሉ፣ በገዛ ራሱ ነዋሪ፣ ሰጪው ይቅር ባዩ መሐሪው ሁሉን አዋቂው አንድዬው ፈጣሪ ነህና፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac