Return to BahaiPrayers.net
Facebook
(በሴት የሚደረግ)
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ከሁሉ ነገሮች የማላቀቅንጽዋ ሙላልኝ፣ በአንተ ውበቶችና ስጦታዎች ጉባኤም ውስጥ አንተን በማፍቀር ወይን ጠጅ አስደስተኝ፤ ከክፉ ስሜትና ፍላጎት ወረራዎች ነፃ አውጣኝ፤ የዚህ የሙታን ዓለምን ሰንሰለቶች ከላዬ በጣጥስልኝ፣ በላቀ ሐሴት ወደ ላቀው መንፈሳዊ ዓለም ሳበኝ፣ በሴት አገልጋዮችም መካከል በቅዱስነትህ እስትንፋሶች አድሰኝ፡፡
ጌታ ሆይ ፊቴን በስጦታዎችህ ብርሃኖች አብራልኝ፣ አይኖቼን ፍጹም ድል አድራጊ የሆነውን ኃያልነትህን ምልክቶች ብርሃን በማየት እንዲበሩ አድርግልኝ፤ አቤቱ አንተ የዚህ ዓለምና የላይኛው መንግስት ንጉሴ ሆይ አቤቱ፣አንተ የስልጣንና የኃይል ጌታ ሆይ የአንተን ምልክቶችና ስጦታዎች በሰፊው ለማሰራጨት እምነትህን ለማወጅ፣ ትምህርቶችህን ለማስፋፋት ሕግህን ለማገልገል ቃልህንም ከፍ ከፍ ለማድረግ እችል ዘንድ፣ ልቤን ሁሉን ነገሮች በሚያቅፈው ዕውቀትህ ክብር አስደስትልኝ፣ ነፍሴም በነፍስ ላይ አዲስ ሕይወት በሚዘሩት የታላቅ ሐሴት አስደሳች ዜናዎች እንድትደሰት አድርጋት፤
አንተ በእውነቱ ኃይል የተመላው፣ ዘላለም ሰጪው ሁሉን ቻዩ፣ ምን የማይሳነው ነህ፡፡
- Bahá'u'lláh