Return to BahaiPrayers.net
Facebook
(በነፍሰ ጡር የሚደረግ)
ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! በእውነቱ ወደ ግልጹ መንግስትህ ስለመራሃት፣ በአላፊ ጠፊውም ዓለም የአንተን ጥሪ እንድትሰማና በሁሉም ነገሮች ውስጥ የአንተን ድል አድራጊ ንግስና መከሰት የሚያረጋግጡትን ምልክቶችህን ለማየት እንድችል ስላደረግሃት ለምትለምንህና ለምትማፀንህ ባሪያህ ለትሑቷ ሴት አገልጋይህ ለለገስካት ችሮታ አወድስሃለሁ፣ ደግሜም አመሰግንሃለሁ፡፡
ጌታዬ ሆይ ይህን በማኅፀኔ ውስጥ ያለውን ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁ፡፡ ስለዚህ በአንተ ችሮታና ቸርነት በመንግስትህ ውስጥ ተመስጋኝ ህፃንና የታደለ ነፍስ ይሆን ዘንድ፣ በአንተ ትምህርት ጥበቃ ሥር እንዲያድግና እንዲዳብር አድርገው፤ በእውነቱ አንተ ፀጋ የተመላው ነህ! በእርግጥ አንተ የታላቅ ችሮታ ጌታ ነህ!
- Bahá'u'lláh