Return to BahaiPrayers.net   Facebook

Infants

ጌታ አምላኬ ሆይ፡ ምስጋና ለአንተ ይሁን ይህ ህፃን በፀጋህ የፍቅራዊ ምሕረትህንና ርኅራኁ የተመላበት የአምላካዊ ጥበቃህን ጡት እንዲጠባ የመንግስተ ሰማያዊ ዛፎችህንም ፍሬዎች እንዲመገብ ፈቃድህ ይሁን፡፡ አንተ ራስህ በላቀው ፈቃድህና ሥልጣንህ ኃይል ስለፈጠርከውና ወደ መኖር ስለጠራኽው ለአንተ እንጂ ለሌላ ለማንም እንክብካቤ እንዲተው አታድርገው ከአንተ ከፍፁም ኃያሉ ከሁሉን አዋቂው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

አቤቱ አንተ ከሁሉም በላይ ተወዳጄ ሆይ፤ የተወደስክ ነህ ከሁሉ የላቀ በረከትህን ጣፋጭ ሽታና የቅዱስ ስጦታዎችህን መዓዛዎች በላዩ አርብብበት፡፡ ከዚያም አቤቱ አንተ ስሞችና የባህርያት መንግስትን በመዳፈህ ውስጥ ይዘህ ያለኽው ሆይ ከሁሉም በላይ በተከበረው ስምህ ጥላ ሥር መጠለያ ለመፈለግ አስችለው፤ በእውነቱ አንተ የፈቀድከውን ለማድረግ የማይሳንህ ነህ፤ በእርግጥም አንተ ኃያሉ የተከበረው ዘለዓለም ይቅር ባዩ ፀጋ የተመላው ለጋሱ መሐሪው ነህና፤

ጌታ አምላኬ ሆይ ይህ አንተ በማይሻረው ትዕዛዝህ መልእክቶችና በፈቃድህ መፃሕፍት ውስጥ የተከበረ ደረጃ እንዲኖራቸው ከፈቀድህላቸው አገልጋዮችህ መካከል ከአንዱ አብራክ የተገኘ ልጅ ነው፡፡

ይህ ልጅ በአገልጋዮችህ መካከል በሳል ነፍስ እንዲሆን ፈቃድህ ይሆን ዘንድ፣ እያንዳንዱን ሰው ወደ ፍላጎቱ ዓላማ ለመድረስ በአስቻልክበት ስምህ እማፀንሃለሁ፣ በስምህ ኃይል አማካይነት እንዲያበራ አድርገው፣የአንተን ምስጋና ለመናገር ፊቱን ወደ አንተ ለመመለስና ወደ አንተ ለመቅረብ አስችለው በእውነቱ ከእምቅድመ ዓለም ጀምሮ እንደፈቃድህ ለማድረግ ኃይል የነበረህ፣እስከ ዘለዓለምም የፈቀድኽውን ለማድረግ የማይሳንህ ሆነህ የምትኖረው አንተ ነህ፤ ከአንተ ከተከበረው ግርማ ሞገስ ከተመላው ከድል አድራጊው ከኃያሉ፣ ከሁሉን አስገዳጁ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

ጌታዬ ሆይ ጌታዬ ሆይ በለጋነት ዕድሜ ያለሁ ሕፃን ነኝ፡፡ ከምሕረትህ ጡት ወተት መግበኝ፣ በፍቅርህ እቅፍ ውስጥ አሰልጥነኝ፣ በአንተ መርሖ ትምህርት ቤት አስተምረኝ፣ በበረከትህ ጥላ ሥር አጎልምሰኝ፤ ከጨለማ አውጣኝ ደማቅ ብርሃን አድርገኝ ከደስታ ማጣት አድነኝ፣የጽጌረዳ አትክልት ሥፍራ አበባ አድርገኝ የደጀሰላምህ አገልጋይ እንድሆን አድርገኝ የፃድቃንንም ዝንባሌና ጠባይ አጎናጽፈኝ ፣ለሰው ዘር ዓለም የበረከት መንስኤ አድርገኝ፣ በራሴም ላይ የዘለዓለም ህይወት አክሊል ድፋልኝ!

በእውነቱ አንተ ኃይል የተመላው ኃያሉ፣ ሁሉን የሚያው ሰሚው ነህና፤

አምላኬ ሆይ ምራኝ፣ ጠብቀኝ ብሩህ መብራትና አንፀባራቂ ኮከብ አድርገኝ፣ አንተ ኃያሉና ኃይል የተመላው ነህና፤

አምላክ ሆይ እነዚህን ህፃናት አስተምራቸው እነዚህ ህፃናት የአትክልት ሥፍራህ ተክሎች የመስክህ አበባዎች አትክልት ቦታህ ፅጌረዳዎች ናቸው፡፡ ዝናብህ እንዲዘንብላቸው የአውነት ፀሐይ ከፍቅርህ ጋር እንዲበራላቸው አድርግ፣ ይሠለጥኑ ያድጉና ይዳብሩ፣ በከፍተኛ ውበትም ይታዩ ዘንድ፣

የአንተ ልዝብ ነፋስ እንዲያድሳቸው ፈቃድህ ይሁን አንተ ሰጪው ነህ፡፡ አንተ ሩኅሩኁ ነህ፡፡

አምላክ ሆይ ይህን ጨቅላ ህፃን በፍቅርህ ጉያ ተንከባከበው ከመለኮታዊ ጠባቂነትህም ጡት ወተት ለግሰው፡፡ ይህን ለጋ ቡቃያ በፍቅርህ የጽጌረዳ አትክልት ሥፍራ ውስጥ ኮትኩተህ አሳድገው፤ ከፀጋህም በሚወርደው ዝናብ እንዲያድግ እርዳው፡፡ የመንግስተ ሰማይ ልጅ አድርገው ወደ መንግስተ ሰማያዊው ዓለምህም ምራው ፡፡ አንተ ኃይል የተመላህና ደግ ነህ፣ አንተ ሰጪው ቸሩ፣የተትረፈረፈ በረከት ባለቤት ነህና፤

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac