Return to BahaiPrayers.net   Facebook

Assemblies

ፍጹም ኃይል የተመላው በፀጋው የላቀ ድል ለማግኘት እንድትችሉ ይረዳችሁ ዘንድ ወደ መንፈሳዊ ጉባኤው ክፍል በምትገቡበት ጊዜ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር በሚርገበገብ ልብና እርሱን ከማስታወስ በቀር ከሌላ ነገር ሁሉ በነፃ አንደበት ይሁን ፀሎት አድርጉ፡፡

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ! እኛ በዚህ ታላቅ ቀን ከአንተ በቀር ከሁሉም ተላቅቀን ወደ ቅዱስ ገጽህ በፍቅር የተመለስን አገልጋዮችህ ነን፡፡ በሰው ዘር መካከል ቃልህን ከፍ ለማድረግ ባለን የዓላማ ስምምነት በአመለካከታችንና በአስተሳሰባችን ተዋሕደን በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሰብስበናል፡፡ ጌታ አምላካችን ሆይ! የአንተ መለኮታዊ መርሖ ምልክቶች፣ በሰዎችም መካከል የላቀው እምነትህ ሰንደቅ ዓላማዎች፣ ለኃይሉ ቃል ኪዳንህም አገልጋዮች እንድንሆን አንተ ከሁሉም የላቅህ ጌታችን ሆይ በአብሀ መንግስትህን የመለኮታዊ አንድነትህ መገለጫዎች፣ በሁሉም አካባቢዎች ላይ የሚያበሩ አንፀባራቂ ከዋክብትም አድርገን፡፡ ጌታ ሆይ! በአስገራሚው ፀጋህ ሞገድ የሚንቀሳቀሱ ባሕሮች ፍፁም ክብር ከተመሉት ከፍታዎች የሚጎርፉ ጅረቶች፣ በመንግስጠ ሰማያዊው እምነት ዛፍ ላይ ያሉ መልካም ፍሬዎችና በመለኮታዊ የወይን እርሻህ ውስጥ በፀጋህ ልዝብ ነፋሶች የሚወዛወዙ ዛፎች እንድንሆን እርዳን፤ አምላክ ሆይ! አስተሳሰቦቻችን አመለካከቶቻችንና ስሜቶቻችን ልክ የአንድነት መንፈስ ይገልፁ ዘንድ ልክ እንደ አንድ ባህር ሰንበሮች አንድ እንድንሆንና እንደ አንፀባራቂው ብርሃንህ ጨረሮች በአንድነት እንድንጣመር፣ ነፍሶቻችን ለመለኮታዊ አንድነትህ ጥቅሶች እንዲገዙ ልቦቻችንም በጸጋህ ጎርፎች እንዲደሰቱ አድርጋቸው፡፡ አንተ ፀጋ የተመላው ለጋሱ ሰጪው ፍጹም ኃያሉ መሐሪው ሩኅሩህ ነህና፡፡

አቤቱ አንተ ሩኅሩህ አምላክ ሆይ! በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ በታላቅ ትሕትና በአንድ ላይ ተሰባስበናል፡፡ አንድ እንድንሆንና እንድንስማማ፣ እርስ በርሳችንም እንድማርና ወተት በጣፈጠ ግንኙነት እንድንቀራረብ፣ ለሰውም ዘር አንድነት መንግስት ምጹዓት ምክንያት እንድንሆን ፊቶቻችንን ወደ አንተ መንግስት በመመለስ ማረጋገጫህንና እርዳታህን እንለምናለን፡፡ ምኖታችን እንዲፈፀምልን በንፁህ ልብና በብሩህ መንፈስ ወደ አንተ እንድንፀልይና እንድንለምንህ እርዳን፡፡

ፍጹም ኃያሉ ሆይ! በፀጋህና በቸርነትህ ተመልክተን እንጂ ኃጢአታችንን አትመልከት፡፡ ጉድለቶቻችንን ይቅር በለን፡፡ በረከትህን አውርድልን፡፡ የፍቅርህን እሳት አቀጣጥለህ የአጉል ምልኮን የስሜትንና የምኖትንን ግርዶሽ አቃጥለህ አጥፋቸው ከእኔነት ድክመት ተከላክለህ ጠብቀን በመሐሪነትህ ዛፍ ጥላ ሥር ከልለን፣ የመንፈስንም ፀጥታና ዕረፍት ስጠን፡፡

በእውነቱ አንተ ኃይል የተመላው ፣ኃያሉ ነህና፡፡

በመንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ መዝጊያ ላይ የሚደረግ ፀሎት

አምላክ ሆይ! አምላክ ሆይ! እኛ በአንተ አምነን፣ኪዳንህና በአዲሱ ሥርዓትህ ፀንተን፣ ወደ አንተ ተስበን፣ በፍቅርህ እሳት ተቀጣጥለን፣ የእምነትህም ቅን እማኖች ሆነን በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ተሰባስበን መገኘታችንን ከማይታየው የአንድነትህ መንግስት ተመልከተን፤ እና በአንተ የወይን እርሻ ውስጥ በማገልገል ላይ የምንገኝ፣ ሃይማኖትህን አስፋፊዎች ራሳችንን ለአንተ አገልግሎት የሰጠን የአንተ ገጽታ አምላኪዎች ለተወዳጆችህ ትሁታን፣ በበርህም ፊት ታዛዦች የሆንን፣ ሕሩያንህን በማገልገል ተግባራችንም ተቀባይነት ማግኘታችንን እንድታረጋግጥልን በማይታዩት ሠራዊቶችህም እንድትደግፈን ለአንተ ለምናበረክተውም አገልግሎት ሽንጦቻችንን እንድታጠናክርልን ለትዕዛዝህ ትሑታን ተገዥዎችና ከአንተም ጋር የምንቋረብ አምላኪ አገልጋዮች እንድታደርገን አንተን በመማፀን ላይ የምንገኝ አገልጋዮችህ ነን፡፡

አቤቱ አንተ ጌታችን ሆይ! እኛ ደካሞች ነን፣ አንተ ደግሞ ኃያሉ፣ ኃይል የተመላው ነህ እኛ ሕይወት አልባዎች ነን፡፡ አንተ ደግሞ ታላቁ ሕይወት ሰጪ መንፈስ ነህ፡፡ እኛ ችግረኞች ነን፡፡ አንተ ደግሞ በሕይወት አኗሪው ኃይል የተመላው ነህ፡፡

አቤቱ አንተ ጌታችን ሆይ! ፊቶቻችንን ምሕረት ወደተመላው ገጽታህ መልስልን፣ ከመንግስተ-ሰማያው የአንተ ገበታ የተትረፈረፈውን የአንተን ፀጋ መግበን በላቁት የአንተ መላእክት ሠራዊት እርዳን፣ በአብሃ መንግስትም ቅዱሳን አማካይነት አጠንክረን፡፡

በእውነቱ አንተ ቸሩ መሐሪው ነህ፡፡ አንተ የታላቅ በረከት ባለቤት ነህ በእርግጥም አንተ ሩኅሩኁና ጸጋ-የተመላው ነህና፣ጸጋ-የተመላው ነህና፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac