Return to BahaiPrayers.net
Facebook
For the Dead
እርሱ አምላክ ነው፤ እርሱ የፍቅራዊ ደግነትና የቸርነት ጌታ የሆነው የተከበረ ነው፤ አንተ ምንም የማይሳንህ ጌታ የሆንክ አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን፣ ምንም የማይሳንህ ስለመሆንህና ስለኃያልነትህ ስለሉዓላዊነትህና ስለፍቅራዊ ደግነትህ፣ ስለፀጋህና ስለሥልጣንህ፣ ስለሕያውነትህ አንድዬነትና ስለህላዌህ አንድነት፣ከፍጥረት ዓለምና በዚያም ከሚገኙት ሁሉ የተቀደስክና የተከበርክ ስለመሆንህ እመሠክራለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ! ከአንተ በቀር ከሁሉም ተላቅቄ አንተን አጥብቄ መያዜንና ወደ ቸርነትህ ውቅያኖስ፣ ወደ ልግስናህ ሰማይና ወደ ፀጋህ ቀኑ ኮከብ ዛሬ ታየኛለህ፡፡
ጌታ ሆይ! በአገልጋይህ ውስጥ አደራህን እንዳስቀምጥክና ይህም ለዓለም ህይወት የሰጠህበት መንፈስ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ በቀናትህ የፈፀመውን ሥራ ምሕረት በተመላበት ሁኔታ እንድትቀበለው በግልፀትህ ሉል ብርሃን እለምንሃለሁ፡፡ በመልካም ፈቃድህ ክብር እንዲጎናፀፍና በአንተ ተቀባይነት እንዲያጌጥ ፈቃድህ ይሁን፡፡
ጌታዬ ሆይ! አቤቱ አንተ የሰዎች ሁሉ ጌታ ሆይ! እኔ ራሴና የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ስለ ኃያልነትህ እንመሰክራለን፤ ይህን ወደ አንተ ወደ መንግስተ ሰማያዊ ስፍራህ፣ ወደ ላቀው ገነትህና ወደ ቅርበትህ ማረፊያ ያረገውን መንፈስ ከአንተ ከራስህ እንዳታገልለው እለምንሃለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ አገልጋይህ ብዕር ሊገልፃቸው አንደበትም ሊያወሳቸው በማይችል መንግስተ ሰማያዊ ሥፍራዎች ውስጥ ከሕሩያንህ፣ ከቅዱሳንህና ከመልእክተኞችህ ጋር እንዲወዳጅ ፈቃድህ ይሁን፤
ጌታዬ ሆይ፤ በእውነቱ ምስኪኑ ወደ ሀብትህ መንግስት ባይተዋሩ በክልሎችህ ውስጥ ወዳለው መኖሪያ ቤቱ እርሱ በጣም የተጠማው ወደ በረከትህ መንግስተ ሰማያዊ ወንዝ ገሥግሷል፡፡ ጌታ ሆይ ከፀጋህ ማዕድና ከበረከትህ ችሮታ ድርሻውን አትንፈገው፤ አንተ በእውነቱ ፍጹም ኃያሉ፤ ፀጋ የተመላው ፍጹም በረከት የተመላው ነህና!
አምላኬ ሆይ፣ አደራህ ወደ አንተ ተመልሷል፡፡ አሁን አቀባበል ላደረግህለት እንግዳህ ስጦታዎችህንና ችሮታዎችህን ከፀጋህም ዛፍ ፍሬዎች መለገሱ በምድርና በሰማይ የሚገኙ ግዛቶችህን ከከበበው ፀጋህና በረከትህ የሚጠበቅ ነው፤ አንተ የፈቀድከውን ለማድረግ ሥልጣን አለህ፤ ከአንተ ፀጋ ከተመላው ከሁሉም በላይ በረከት ከተመላው ከሩኅሩኁ ከለጋሱ ከይቅር ባዩ ከክቡሩ ከሁሉን አዋቂው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡
ጌታዬ ሆይ ሰዎች እንግዳቸውን እንዲያከብሩ እንዳዘዝካቸው እርሱ ወደ አንተ ያረገውም በእውነቱ አንተ ዘንድ እንደደረሰና ቅርበትህን እንደተቀዳጀ እመሠክራለሁ፤ እንደፀጋህና እንደቸርነትህ ተቀበለው፣ በክብርህ አገልጋዮችህን ካዘዝካቸው ተግባር ራስህም ወደ ኋላ እንደማትል፣ እርሱን በበረከትህ ገመድ ላይ የተንጠላጠለውንና ወደ ሀብትህ ጎሕ ያረገውን እንደማትነፍገው በእርግጥ አውቃለሁ፡፡
ከአንተ ከአንዱ ከአንደዬው ኃይል ከተመላው፣ ከሁሉን አዋቂው በረከት ከተመላው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጌታ አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን! እርሱን በዘላለማዊ ሉዓላዊነትህ ኃይል ያከበርከውን አታዋርደው ወደ ዘለዓለማዊ መቅደስህ እንዲገባ ያደረግኽውንም ከአንተ እንዲርቅ አታድርገው፤ አምላኬ ሆይ፣ እርሱን አንተ በጌትነትህ ጥላ ሥር የከለልከውን ከአንተ መሸሻው የነበርከውን ከአንተ ዘንድ ታባርረዋለህና እርሱን አንተ ከፍ ያደረግኽውን ታዋርደዋለህን. ወይም እርሱን አንተን ለማሰታወስ ያስቻልከውን ትረሳዋለህን?
አንተ የተከበርክ፣ እጅግ በጣም የተከበርክ ነህ! አንተ ከእምቅድመ ዓለም ጀምረህ የመላው ፍጥረት ንጉሥና ዋና አንቀሳቃሹ የነበርከው ነህ፣ ለዘላለምም የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ጌታና ወሳኛቸው ሆነህ መኖርህን ትቀጥላለህ፤ አምላኬ ሆይ አንተ የተከበርክ ነህ ለአገልጋዮችህ ምሕረት መለገስን ብታቋርጥ ሌላ ማን ምሕረት ያደርግላቸዋል፡፡ አንተ ተወዳጆችህን ካልደረህ ፤ ሌላ ማን ሊራዳቸው ይችላል?
አንተ የተከበርክ፣ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ! አንተ ለእውነተኝነትህ የተወደስክ ነህ፤ በአርግጥም እኛ ሁላችንም አንተን እናመልካለን፤ አንተ በፍርድህ ግልጽ ነህ፣በእውነትም እኛ ሁላችንም ለአንተ እንመሠክራለን አንተ በእርግጥ ለፀጋህ የተወደድህ ነህ፤ ከአንተ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ፣ በገዛ ራሱ ነዋሪ ከሆንከው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡
አምላኬ ሆይ! አቤቱ አንተ ኃጢአትን ይቅር ባዩ ስጦታዎች ሰጪው ጭንቅንም አትፊው ሆይ! በእውነቱ ሥጋዊ ልብስን ጥለው ወደ መንፈሳዊው ዓለም ያረጉትን ሁሉ ኃጢአት ይቅር ትልላቸው ዘንድ እማፀንሃለሁ፡፡
ጌታዬ ሆይ ከኃጢአት ሁሉ አንፃቸው ኃዘናቸውን አስወግድላቸው፣ ጨለማውንም ወደ ብርሃን ለውጥላቸው፤ ወደ ተድላ ገነት እንዲገቡ አድርጋቸው ፍጹም ንጹህ በሆነው ውሃ እጠባቸው፤ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ በሆነው ተራራ ላይ ያለውን ግርማህንም እንዲያዩ አድርጋቸው፤
- Bahá'u'lláh