Return to BahaiPrayers.net   Facebook

Mankind

የማመልክህና የማወድስህ አምላክ ሆይ ! ስለአንድነትህና ስለ አንድዬነትህ እመሠክራለሁ፡፡ በፊት ለሰጠኽኝና አሁንም ለምትሰጠኝ ስጦታህ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ የምህረቱ የሚያጥለቀልቁ ዶፎች በታላላቆቹም በታናናሾቹም ላይ ያለልዩነት የዘነቡት የፀጋውም ደመቅ ብርሃኖች በታዛዦችም በአመፀኞችም ላይ ያበሩት ፍጹም ቸር ጌታ ነህ፡፡

አቤቱ አንተ የምህረት ህልውና በእርሱ በር ደጃፍ ፊት የሰገደው፣ በእርሱም እምነት መንበር ዙሪያ፣ ፍቅራዊ ደግነት ከሁሉ በላቀ ውስጣዊ መንፈሱ የከበበው የምህረት አምላክ ሆይ፤ የሰው-ዘር ዓለም መገለጫዎች በሆኑት ሁሉ ላይ ምህረት እንዲኖርህ፣ በቀናትህም ከፀጋህ ህዝቦች እንዳትነፍጋቸው፣ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ፀጋህን እየተማለድን፣ የአሁንም ጊዜ ችሮታህን እየለመንን እንማፀንሃለን፡፡

ሁሉም ድሆችና ችግሮች ናቸው፤ አንተ ግን በእውነቱ ሁሉ ያለው ሁሉ አስገባሪው ፍጹም ኃያል የተመላው ነህ፡፡ ጌታ ሆይ! ማንም የተፈጠረ ህያው ከመልካም ፈቃድህ ክልሎች ውጪ እንዳይቀር፣ ሁሉንም የምድር ህዝች ወደ እምነትህ ገነት የመግባትን ፀጋ ለማግኘት አስችላቸው፡፡ አንተ ሊታወስ ከማይቻል ጊዜ ጀምሮ የሚያስደስትህን ለማድረግ ችሎታ ያለህ ከምትሻው ከማንኛውም ነገር በላይ ሆነህ ኖረሃል፡፡

አቤቱ አንተ ሩኅሩኅ አምላክ ሆይ! የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ምንጭ ፈጠርኩ ሁሉም አንድ ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ አዘዝህ፡፡ በቅዱስ ቅርበትህ ሁሉ በመንበርክ ሥር ይጠለላሉ፤ ሁሉም በበረከትህ ማዕደ ዙሪያ ተሰብስበዋል፡፡ ሁሉም በአምላካዊ ጥበቃህ ብርሃን አንፀባርቀዋል፡፡

አምላክ ሆይ፣ አንተ ለሁሉም ደግ ነህ፤ ለሁሉም ህይወት ትሰጣለህ፣ ለእያንዳንዱም ተሰጥአንና ችሎታን ሰጥተዋል፣ ሁሉም በምሕረትህ ውቅያኖስ ውስጥ ሰጥመዋል፡፡ አቤቱ ቸር አምላክ ሆይ! ሁሉን አስተባብር፡፡ የሰው ልጆች አንድ ቤተሰብ እንዲሆኑና መላዋን ምድር እንደ አንድ መኖሪያቸው እንዲያደርጉአት፣ ሃይማኖቶች እንዲስማሙ አድርግ፣ ሀገሮችንም አንድ አድርጋቸው፡፡ ሁሉም በፍጹም አንድነትና ስምምነት እንዲኖሩ ፈቃድህ ይሁን፡፡

አምላክ ሆይ! የሰውን ዘር አንድነት ሰንደቅ ከፍ ብሎ እንዲታይ አድርገው፡፡ አምላክ ሆይ! ታላቁን ሰላም መስርት አምላኬ ሆይ! ልቦችን በጽኑ አስተባብር፡፡ አቤቱ ቸር አባት የሆንክ አምላክ ሆይ! በፍቅርህ መዓዛ ልቦቻችንን ደስ አሰኝልን፡፡ በመርሖህም ፋና አይኖቻችንን አብራልን በቃልህ ዜማ ጆሮዎቻችንን አስደስትልን በአምላካዊ ጥበቃ ከምሽግ ውስጥ ሁላችንን ጠልለን፡

አንተ ኃይልና ብርቱው ነህ አንተ ይቅር ባዩ ነህ፣ አንተ ሰውን ልጆች ጥፋት የማይከታተለው ነህና፡፡ አቤቱ አንተ ሩኅሩኅ ቸርና ሁሉን የምትችል ጌታ ሆይ! እኛ በአምላካዊ ጥበቃህ ሥር ተጠልለን የምንገኝ አገልጋዮችህ ነን፡፡ የፍቅር አንፃርህን አሳርፍብን፡፡ ለአይኖቻችን ብርሃንን፣ለጆሮቻችን መስማትን፣ ለልቦቻችን ማስተዋልንና ፍቅርን ስጥልን በምስራች ዜናህ ነፍሶቻችንን አስደስትልን፡፡ ጌታ ሆይ! የመንግስትህን መንገድ አሳየን፣ በመንፈስ ቅዱስህም እስትንፋስ በሁላችን ነፍስ ዝራብን፡፡ ዘለዓለማዊ ህይወትን ስጠን፤ የማይሻረውንም ክብር አጎናጽፈን፡፡ የሰውን ልጆች አንድ አድርጋቸው፣ የሰውንም ዘር ዓለም አብራ፡፡ መንገድህን እንድንከተል፣ ፈቃድህን እንድንናፍቅ፣ የመንግስትህንም ምስቲር እንድንሻ አድርገን፡፡ አምላክ ሆይ! አስተባብረን ልቦቻችንንም ከቶ ከማይፈርሰው ኅብረትህ ጋር አስተሳስርልን፡፡ በእውነቱ አንተ ሰጪው ነህ፣ አንተ ሩኅሩኁ ነህ፣ አንተ ፍጹም ኃያሉ ነህና፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac