Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Pioneers
አምላኬ ሆይ የአንተን መልካም ደስታ ከመቀዳጀት ለአንተ አገልጋይ ለመሆን ተቀባይነት ስለማግኘቴ ማረጋገጫን ከማግኘት፣ ለአንተ አገልግሎት ለማበርከት ዓላማ ራሴን ከመስጠት፣ በአንተ ታላቅ የወይን እርሻ ውስጥ ከመሥራትና ሁሉንም ነገር በአንተ መንገድ መስዋዕት ከማድረግ በስተቀር በልቤ ውስጥ ምንም አይነት ሌላ ፍላጎት እንደሌለ አንተ የምታውቀውና ምስክሬም ነህ፡፡ አንተ ሁሉን አዋቂው፤ ሁሉን የሚያየው ነህና ለአንተ ካለኝ ፍቅር፤ እርምጃዎቼን ወደ ተራሮችና ወደ በረሃዎች በማቅናት አንተ መንግስት ስለመምጣቱ ክፍለ ባለ ድምጽ ከማወጅ በሰዎችም ሁሉ መካከል ጥሪህን ከማሰማት በስተቀር ሌላ ምኞት የለኝም፡፡ አምላክ ሆይ! ለዚህ ረዳት ለሌለው መንገዱን ክፈትለት፣ ለዚህ ህመምተኛ መድኃኒት ፈቀድለት፣ ለዚህም ለሚሰቃየው ፈውስህን አውርድለት ፡፡ ልቤ እየነደደ ፣ ከአይኖቼም እንባ እየጎረፈ በአንተ ደጀሰላም ላይ ሆኜ እማፀንሃለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ በመንገድህ ማንኛውንም መከራ ለመቻል ዝግጁ ነኝ፣ በሙሉ ልቤና ነፍሴም ማንኛውንም ችግር ለመቋቋም እመኛለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ! ከፈተናዎች ጠብቀኝ፤ እኔ ከሁሉም ነገሮች ፊቴን ማዞሬንና ረሴን ከሁሉም ሃሳቦች ነፃ ማድረግን አንተ ደህና አድርገህ ታውቃለህ፡፡ አንተን ከማንሳት በስተቀር ምንም ሥራ፣ አንተን ከማገልገልም በቀር ሌላ ምንም ምኖት የለኝም፡፡
- Bahá'u'lláh