Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Help
አቤቱ አምላኬ፣ ተወዳጄ ንጉሴ ፍላጎቴ ሆይ! ለአንተ የማቀርባቸውን ምስጋናዎቼን ምን አንደበት ሊያወሳቸው ይችላል. ደንታ-ቢስ ነበርኩ፣ ቀሰቀስከኝ፡፡ ከአንተ ዞሬ ነበርኩ፤ ወደ አንተ እንድመልስ በፀጋህ ረዳኽኝ፡፡ እንደሞተ ሰው ነበርኩ፤ በሕይወት ውሃ ነፍስ ዘራህብኝ፡፡
መለኮታዊው ጠባቂ ሆይ መላው ኑባሬ በፀጋህ የተገኘ ነው፤ ከቸርነትህ ውሃዎች አትንፈገው ከምህረትህም ውቅያኖስ አትከልክለው፡፡ በሁሉ ጊዜያትና በሁሉ ሁኔታዎች እንድትረዳኝና እንድትደግፈኝ ጥንታዊ ቸርነትህንም ከፀጋህ መንግስተ -ሰማይ እንድፈልግ እንድታደርገኝ እማፀንሃለሁ፡፡ በእውነቱ አንተ የጸጋ ጌታ፣ የዘለዓለማዊ መንግስት ንጉሥ ነህና፡፡
ጌታ ሆይ አንተ የተከበርክ፣ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ! ጠልቆ የመረዳት ችሎታ ያለው እያንዳንዱ ሰው አንተን አውቆ ለመቀበል በሚያደርገው ሙከራው በጣም መንገድ ስቷል፡፡ እያንዳንዱም የበቃ የዕውቀት ሰው ስለ አንተ በሚያደርገው ምርመራ ክፉኛ ግራ ተጋብቷል፡፡ እያንዳንዱ ማስረጃ ሊታወቅ ወደማይቻለው የአንተ ሕላዌ ለመድረስ አይችልም፡፡ እያንዳንዱም ብርሃን ከኃያልነትህ የሚያፈዝ ነፀብራቅ ውስጥ ከጭላንጭሉ ብቻ ጋር እንኳ ቢወዳደር ወደኋላ ያፈገፍግና ከአድማስ በታች ይጠልቃል፡፡
ጌታ ሆይ ፀጋ የተመላበት በረከትህንና በጎ ስጦታዎችህን አጎናጽፈኝ፣ ከክብርህ ከፍተኝነት ተገቢ የሆነውንም ፍቀድልኝ፤ ጌታዬ ሆይ ልዩ ድል ለማግኘት እንድችል እርዳኝ፡፡ የማይቀር የዓላማ ስኬት በር በፊቴ ክፈትልኝ አንተ ቃል የገባሃቸው ነገሮች በቅርብ ጊዜ እንዲደርሱ ፈቃድህ ይሁን፤ አንተ በእውነቱ በሁሉ ነገሮች ላይ ኃይል አለህ፤ አምላኬ ሆይ ልቤን በፍቅርህ የህይወት ውሃዎች አድስልኝ፤ ጌታዬ ሆይ ከለጋም ምህረትህ ጽዋ አርኪ መጠጥ ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ በክብርህ መኖሪያ ውስጥ እንድኖር ፍቀድልኝ፣ አምላኬ ሆይ መለኮታዊ ሥውርነትህ ከተሸፈነበት ጨለማ ውስጥ እንድወጣ አድርገኝ፡፡ ለእርሱ ነቁጥ ለሆነውና ለእነዚያ እምነት ደጋፊዎች ለሆኑት ከሰጠኽው ከእያንዳንዱ መልካም ነገር ለመካፈል አስችለኝ፡፡ ከአንተ መስጠቱ የሚጠበቀውንና ለደረጃህ የሚገባውን እዘዝልኝ፤ በቅዱስ ቅርበትህ ለፈፀምኳቸው ክፉ ነገሮች በፀጋህ ይቅር በለኝ በፀጋህ አድነኝ እንጂ በፍትሕ እይታ አትመልከተኝ፤ ለክብርህ በሚገባው ሁኔታ በምህረትህ አያያዝ ያዘኝ፤ በረከት ለተመላባቸው ችሮታዎችህም የሚመጥነውን ለግሰኝ፡፡
አንተ ዘለዓለም ይቅርባዩ ንዑዱ ችሮታዎችንና ሥጦታዎችን አጎናጽፈው፣ ወሰን የሌለው ፀጋ ጌታ ነህና፡፡ በእውነቱ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንተ ሁሉ ያለው፣ ከሁሉም በላይ ከፍተኛው ነህ፡፡
እግዚአብሔር ጌታችን ሆይ ! ለአንተ ከሚያስፀይፈው ከማንኛውም ነገር በፀጋህ ጠብቀን ከአንተ መሰጠቱ ተገቢ የሆነውን ስጠን፡፡ ከሰፊ ቸርነትህ ጨምርልን፣ እንዲሁም ባርከን ለፈፀምናቸው በደሎች ይቅርታ አድርግልን፤ ኃጢአቶቻችንንም ካላያችን እጠብልን፣ ፀጋ በተመላበት ይቅር ባይነትህም ቅር በለን፡፡ በእውነቱአንተ ከሁሉም በላይ የተከበርከው፣ በጋዛ ራሱም ነዋው ነህና፡፡
ፍቅር የተመላበት አምላካዊ ጠባቂነትህ፤ በሰማያትና በምድር የተፈጠሩትን ነገሮች ሁሉ አቅፏል፡፡ ይቅር ባይነትህም ከመላው ፍጥረት አልፎ ተርፏል፡፡ ሉዓላዊነት ያንተ ነው፤ የፍጥረትና የግልፀት ዓለማት በእጅህ ናቸው፤ በቀኝ እጅህ የተፈጠሩትን ነገሮች ሁሉ ይዘሃል፣ የይቅር ባይነትህ የተመደቡ መጠኖች በመዳፍህ ውስጥ ናቸው፡፡ ከአገልጋዮችህ መካከል ለፈለግኽው ለማንኛውም ይቅር ትለዋለህ፡፡ በእውነቱ አንተ ዘለዓለም ይቅር ባዩ ሁሉን አፍቃሪው ነህ፡፡ ምንም ነገር ማንኛውም ቢሆን ከዕውቀትህ አያመልጥም፣ ከአንተ የተሰወረ ምንም ነገር የለም፡፡
እግዚአብሔር ጌታችን ሆይ! በኃያልነትህ ኃይል ተብቀን፣ በመትመም ላይ ወዳለው ድንቅ ውቅያኖስህ ለመግባት አስችለን፣ ከአንተ መፈቀዱ ተገቢ የሆነውን ፍቀድልን ፡፡
አንተ የላቀው ገዢ ኃያሉ አድራጊ፣ የተከበረው ሁሉን አፍቃሪው ነህና፤
ጌታ ሆይ! ምስኪኖች ነንና ችሮታህን ስጠን፡፡ ድሆች ነንና ከሀብትህ ውቅያኖስ አጋራን፣ ችግረኞች ነንና አጥግበን፣ የተዋረድን ነንና ክብርህን አጎናጽፈን፣ የሰማይ ዐዕዋፋትና የየብስ እንሰሶች ሁሉ ምግባቸውን በየቀኑ ከአንተ ያገኛሉ፤ ሕያዋንም ሁሉ ከአንተ ጠባቂነትና ፍቅራዊ ደግነት ይካፈላሉ፤
ይህን ደካማ ፍጡር ግሩም ፀጋህን አትንሣው በኃያልነትህም ለዚህ ምስኪን ነፍስ ቸርነትህን ስጠው፡፡ የዕለት እንጀራችንን ስጠን፣ የአንተ እንጂ የሌላ ጥገኞች እንዳንሆን ከአንተም ጋር በፍጹም እንድንቋረብ፣ በአንተም መንገድ አንድንመላለስና ምስጢርህን ለመግለጽ እንድንችል ለሕይወት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ መጠን አብዛ፡፡ አንተ ፍጹም ኃያሉ፣ አፍቃሪና ለሰው ዘር ሁሉ አስፈላጊውን ሰጪው ነህና፡፡
ጌታ ሆይ! ደካሞች ነንና አበርታን፡፡ አምላክ ሆይ! ዕውቀት ቢስ ነንና አዋቂዎች አድርገን፡፡ ጌታ ሆይ! ድሆች ነንና ባለፀጋዎች አድርገን፡፡ አምላክ ሆይ! የሞትን ነንና የህይወት እስትንፋስ ዝራብን፡፡ ጌታ ሆይ! ውርደት ራሷን ነንና በመንግስትህ ውስጥ ክብርን አጎናጽፈን፡፡ ጌታ ሆይ አንተ ከረዳኽን እንደሚያበሩት ከዋክብት እንሆናለን፡፡ አንተ ካልረዳኽን ግን ከአፈር በታች እንሆናለን፡፡ ጌታ ሆይ አበርታን፡፡ አምላክ ሆይ! ድል አጎናጽፈን፡፡ አምላክ ሆይ! እኔነትን ለማሸነፍና ከከንቱ ምኞት በላይ ለመሆን አስችለን፡፡ ጌታ ሆይ! ከዓለማዊ ቁራኛነት አድነን፤ ጌታ ሆይ! አንተን ለማገልገል እንድንነሣሣ፣ ለአንተ መስገድ ተግባራችን በመንግስትህም ውስጥ ተሳትፎአችን በሙሉ ልብ እንዲሆን በቅዱስ መንፈስ እስትንፋስ አንቃን፡፡ ጌታ ሆይ! አንተ ኃይል የተመላው ነህ1 አምላክ ሆይ፤ አንተ ይቅር-ባዩ ነህ! ጌታ ሆይ ፣ አንተ ሩኅሩኁ ነህ!
- Bahá'u'lláh