Return to BahaiPrayers.net   Facebook

Thanksgiving

አምላኬ ሆይ፣ የክብርና የግርማ፣ የታላቅነትና የክቡርነት፣ የሉዓላዊነትና የገዢነት፣ የልዕልናና የፀጋ የመከበርና የስልጣን ሁሉ ምንጭ ለሆንከው ለአንተ ብቻ ምስጋና ሁሉ ይድረስህ፡፡ አንተ የምትፈቅደውን ሁሉ ወደ እጅግ በጣም ታላቁ ውቅያኖስ እንዲቀርብ ታደርገዋለህ፤ የመትወደውንም ሁሉ ዘለዓለማዊ ስምህን የማወቅን ክብር ታጎናጽፈዋለህ፡፡ በሰማያትና በምድር ካሉት ሁሉ የከፍተኛ ፈቃድህን ፍፃሜ ሊያስቀር የሚችል ከቶ አይገኝም፡፡ ከእምቅድመ ዓለም ጀምረህ ፍጥረትን ሁሉ ገዝተሃል፣ እስከ ዘለዓለምም በፍጡራን ሁሉ ላይ ገዥነትህ ከቶ አያቋርጥም፡፡ ከአንተ ከፍጹም ኃያሉ፣ ከሁሉም በላይ ከተከበረው፣ ፍጹም ኃይል ከተመላው ከፍጹም ጠቢቡ በስተቀርሌላ አምላክ የለም፡፡

ጌታ አምላኬ ሆይ፣ አገልጋዮችህ አንተን ለማየት ይችሉ ዘንድ ፎቶቻቸውን አብራላቸው፣ ወደ መንግስተ ሰማያዊ ችሮታዎችህ መንበር እንዲዞሩ፣ እርሱን የአንተ የራስህ ክስተትና የህላዌህ ጎሕ የሆነውን እንዲያውቁ ልቦቻቸውን አንፃ፡፡ በእውነቱ አንተ የዓለማት ሁሉ ጌታ ነህና ከአንተ ጨቋኝ ከሌለበትና ሁሉን ድል ከሚነሣው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

የተመሰገንክና የተወደስክ ነህ፣ ጌታ አምላኬ ሆይ! ምንም ያህል ጥበቡ የጠለቀ አንደበት ስምህን በተገቢ ሁኔታ ለማወደስ እንደማይችል፣ የሰው ልብ ወፍም፣ ምንም ያህል ታላቅ ናፍቆትና ፍላጎት ቢኖረውም፣ ወደ ግርማህና ወደ ዕውቀትህ ሰማይ ሊያደርግ እንደማይችል እያወቅሁ፣ እንዴት ስምህን ላነሳ እችላለሁ፡፡

አምላኬ ሆይ! ሁሉን የሚያስተውል ብዬ ብገልጽህ፣ እነዚያ ፍጹም ከፍተኞቹ የማስተዋል ክስተቶች በአንተ ትዕዛዝ መፈጠራቸውን እንድቀበል እገደዳለሁ፡፡ ፍጹም ጠቢቡ ብዬ ባወድስህም፣ እንደገና የጥበብ ምንጮች የሆኑት ራሳቸው በአንተ ፈቃድ መፍለቃቸውን እንዳውቅ እገደዳለሁ፡፡ ተወዳደሪ የሌለው ብዬ ብገልጽህም ፣ እነዚያ የአንድነት ውስጣዊ ህልውና የሆኑት በአንተ ወደዚህ የተላኩና የአንተ የእጅ ጥበብ ማረጋገጫዎች መሆናቸውን ወዲያውኑ እረዳለሁ፡፡ ሁሉን ነገሮች አዋቂው ብዬ ብጠራህም፣ እነዚያ የዕውቀት የመጨረሻ ከፍተኛ ህልውና የሆኑት የዓላማህ ፍጥረቶችና መሣሪያዎች መሆናቸውን ማመን አለብኝ፡፡

የሟች ሰው ፍጥረት ምስጢርህን ለመፍታት ክብርህን ለመግለጽ የህላዌህን ባህርይ እንኳ ለመጠቆም ከሚችለው በላይ የተከበርክ፣ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ፤ እነዚህ ጥረቶች በትዕዛዝህ የተንቀሳቀሱና የአንተ ፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ፣ እንዲህ ያሉት ጥረቶች ምንም አይነት ውጤት ቢያስገኙም ለፍጡራንም ከወሰንከው ገደብ የማለፍ ተስፋ ሊኖራቸው ከቶ አይችሉም፡፡ እጅግ በጣም ብፁዕ የሆኑት ቅዱሳን አንተን ለማወደስ የሚያቀርቡት ከፍተኛ ስሜት፣ እጅግ በጣም የተማሩት ሰዎች የአንተን ባህርይ ለመረዳት በመሞከር ሊናገሩት የሚችሉት እጅግ በጣም ጥልቅ ጥበብ፣ በዚያ በአንተ ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ በሚገዛው፣ የአንተን ውበት በሚያስጌጠው፣ በአንተ ብዕር ኃይል በሚንቀሳቀሰው ማዕከል ዙሪያ ይሽከረከራሉ፤

አምላኬ ሆይ! በተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ህልውናና በግልፀትህ ብዕር መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለ የግድ የሚያመለክቱትን አይነት ቃላት ስለመናገሬ ይቅር በለኝ፡፡ እነዚያ ከአንተ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ከዚህ አይነቱ የማዛመድ ሐሳብ በላይ በጣም በጣም ከፍ ያሉ ናቸው፡፡ ማንኛውም ማወዳደርና ማመሳሰል ለግልጸትህ ዛፍ ተገቢ አይደለም፡፡ የአንተን ክስተትና የውበትህን ጎሕ የመረዳት መንገድ ሁሉ ተዘግቷል፡፡

ሟች ሰው ስለ አንተ ሊናገር ወይም አንተን ሊገልጽበት የሚችለው ባህርይ ወይም አንተን ሊያወድበት የሚችለው ምስጋና ከአንተ ክብር በጣም የራቀ ይሁን! አገልጋዮችህን ያዘዝካቸው፣ የተቻላቸውን ያህል ግርማህንና ክብርህን የማወደስ ማንኛውም ምግባር፣ ለራሳቸው እጅግ ጥልቅ ሕያውነት ወደ ተሰጠው ደረጃ፣ ራሳቸውን ወደ ማወቅ ደረጃ ለመድረስ የሚያስችላቸው የእነተ ፀጋ ምልክት ብቻ ነው፡፡

በምንም ጊዜ፣ ከአንተ በስተቀር የአንተን ምስጢር ጠልቆ ለማወቅ፣ ወይም የአንተን ታቅነት በሚገባ ለማወደስ የቻለ የለም፡፡ አንተ በምርምር የማትገኝ፣ ከሰዎችም ምስጋና በላይ ሆነህ ዘለዓለም ትኖራለህ፣ የማይደረስብህ፣ ምንም የማይሳንህ፣ ሁሉን አዋቂ የቅዱሳን ቅዱስ ከሆንከው ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡

አምላኬ ሆይ የክብሮች ክብርና ከሁሉ በላይ አንፀባራቂው ብርሃን በአንተ ላይ ይረፍ፡፡ ግርማህ በጣም የመጠቀ በመሆኑ ምንም የሰው ሃሳብ ሊደርስበት አይችልም፤ ፍጹም ኃይልህም በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የሰዎች ልቦችና አዕምሮዎች አእዋፋት ከፍታዎቹ ላይ ለመድረስ ከቶ አይችሉም፡፡ ሕያዋን ሁሉ ለደረጃህ እንደሚገባ ሊያወድሱህ ኃይል አልባነታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ፡፡ አንተ በራስህ እንዳለህ የምታውቀው ራስህ ብቻ ስለሆንክ ህያውነትህን ሊያሞግስ፣ ወይም ከሁሉም በላይ ጥልቀ በሆነው ውስጣዊ ህልውናህ በሚገኘው ሁኔታ የበረከትህን ማስረጃዎች ጠልቆ ለመረዳት የሚችል ማንም የለም፡፡

ጌታ አምላካችን ሆይ፣ የፍጥረትንና የፈጠረን ዓለም ወደ መኖር ለጠራህበት በረከት፣ ከአንተ በቀር ሌላ ምንም በሚገባ ሊገምተው በማይችለው፣ በማነቃቂያህ ኃይል በድምቀቀት በሚያበራው ምስጋና ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ከዚህም በላይ፣ ለዚህ ቅዱስ ቡራኬ፣ ለዚህ በግልፀትና በፍጥረት መንግስቶችህ ለተገለፀው ድንቅ ምልክት ለአስፈሪ ቅርበትህና ለአሸናፊው ግርማህ ክብር እንደሚገባው አወድስሃለሁ፣ ምስጋናም አቀርብልሃለሁ፡፡

ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን፡፡ ያ ለአንተ የሚገባው ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበረ ነው፡፡ በእውነቱ የደረጃህን ምጥቀት ማንም በቂ በሆነ ሁኔታ ተረድቶት፣ ወይም ከአንተ በቀር ሌላ ማንም ለአንተ እንደሚገባ አውቆህ አያውቅም፡፡ ከአንተ በቀር ሌላ የግልፀትህን ፍተኝነት ለመገመት የሚችል የሌለ ሲሆን፣ አንተ በሰፊ በረከትህ ጎርፎች አማካይነት ትገለፃለህ፡፡

ስምህ የተወደሰ ይሁን፣ ከአንተ በቀር ሌላ ማንም የባህርይህን ፍንጭ እንኳ ለመናገር ይችል ዘንድ ነፃ ህልውና አለውን. ከአንተም በቀር ሌላው አንተን ላውቅበት የምችልበት የአምሳል ምልክት አለውን. የታወቀ ሁሉ መታወቁን የሚያገኘው፣ ከሁሉም በላይ ግልጹ ከሚለው ስምህ ውበት ነው፤ እያንዳንዱ ነገር ከማይሸነፈው ፈቃድህ በሚፈልቀው አርገብጋቢ ኃይል ከሥረ መሠረቱ ተንቀሳቅሷል፡፡ አንተ ከሁሉም ነገሮች ይበልጥ ለሁሉ ነገሮች ቅርብ ነህ፡፡

የተመሰገነንክና የተከበርክ ነህ፡፡ ምጥቀትህ እነዚያ የመረዳት ኃይልን የተለገሱት ሰዎች እጆች ወደ አንተ ለመዘርጋት ከሚችሉበት ከፍታ የላቀ ነው፤ መጨረሻ የሌለውም ጥልቀትህ የሰዎች አዕምሮዎችና የመገንዘብ ችሎታዎች ወንዞች ከዚያ ለመጉረፍ ከሚችሉበት ይበልጥ ጥልቅ ነው፡፡

አቤቱ አንተ ሩኅሩኅ ጌታ ሆይ! አንተ ለጋሱና መሐሪው ሆይ! እኛ የደጀሰላምህ አገልጋዮች ነን፤ በከለላ ሰጪውም የመለኮታዊ አንድነትህ ጥላ ስር ተሰብስበናል፡፡ የምህረትህ ፀሐይ በሁሉም ላይ ያበራል፤ የበረከትህም ደመናዎች በሁሉም ላይ ያዘንባሉ፤ ስጦታዎችህ ሁሉንም ይከባሉ፤ ፍቅራዊ አምላካዊ ጥበቃህ ሁሉን በህይወት ያኖራል፡፡ የአንተ ጥበቃ ሁሉን ይከልላል፤ የችሮታህ እይታዎችም በሁሉም ላይ ያርፋሉ፤ ጌታ ሆይ! የማያልቁትን ስጦታዎችህን ስጠን፣ የመርሖህም ብርሃን እንዲያበራ ፈቃድህ ይሁን፡፡ አይኖችን አብራ፣ ልቦችን በማያቋርጥ ሐሴት አስደስት፤ በሁሉም ሰዎች ላይ አዲስ መንፈስ ዝራ፣ ዘላለማዊ ሕይወትንም አጎናጽፋቸው፡፡ እውነተኛ ማስተዋልንም በሮች ክፈት፣ የእምነትም ብርሃን በድምቀት እንዲያበራ ፈቃድህ ይሁን፤ ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ፀሐይ ጨረሮች እንደ አንድ ውቅያኖስ ማዕበሎች፣ እንደ አንድ ዛፍም ፍሬዎች ይሆኑ ዘንድ፣ በቸርነትህ ጥላ ሥር ስብሰባቸው፤ እንዲስማሙና አንድ እንዲሆኑም አድርጋቸው፤ ከአንድ ምንጭ እንዲጠጡ ይሁን፤ በአንድ ልዝብ ነፋስም እንዲነቃቁ ፈቃድህ ይሁን፡፡ ከአንድ የብርሃን ምንጭም ብርሃን ይቀበሉ፡፡ አንተ ሰጪው መሐሪው ምንም የማይሳነው ነህና፡፡

 


English  
ភាសាខ្មែរ  
አማርኛ.  
Afrikaans  
Alaska Native  
American Indian  
Azərbaycan  
Bahasa Indonesia  
Bahasa Malaysia  
Bidayuh  
Bosanski  
Canadian Indigenous  
Català  
Cebuano  
Česky  
Chamorro  
Chichewa  
Corsica  
Cymraeg  
Daga  
Dansk  
Deutsch  
Dzongkha  
Eesti  
Español  
Esperanto  
Euskara  
Fiji  
Filipino  
Føroyar  
Français  
Frysk  
Hausa  
Hawaiian  
Hiri Motu  
Hrvatski  
Irish  
Íslenska  
Italiano  
Kabyle  
Kalaallisut  
Kiribati  
Kiswahili  
Kreyol Ayisyen  
Kuanua  
Kube  
Latviešu  
Lëtzebuergesch  
Lietuvių  
Luganda  
Magyar  
Malagasy  
Malti  
Māori  
Marshallese  
Melpa  
Montenegrin  
Nalik  
Namibia  
Nederlands  
Norsk  
Papiamentu  
Polski  
Português (BR)  
România  
Sámi  
Samoan  
Sarawak  
Sesotho  
Shqip  
Slovenščina  
Slovensky  
Sranan Tongo  
Srpski српски  
Suomi  
Svenska  
Tetum  
Tiếng Việt  
Tok Pisin  
Tongan  
Türkçe  
Türkmençe  
Tuvalu  
Vanuatu  
ελληνικά  
Беларускі  
български  
Кыргыз  
Монгол хэл  
Русский  
Тоҷикӣ  
Україна  
հայերեն  
اُردُو  
العربية  
فارسی  
नेपाली  
मराठी  
हिंदी  
বাংলা  
ગુજરાતી  
ଓଡ଼ିଆ  
தமிழ்  
తెలుగు  
ಕನ್ನಡ  
മലയാളം  
ภาษาไทย  
ພາສາລາວ  
한국어  
日本語  
简体中文  
繁體中文  
Windows / Mac