Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Protection
ጌታ አምላኬ ሆይ፣ስምህ የተወደሰ ይሁን! ወደ አንተ ተመልሰው የአንተን እምነት ለረዱት አገልጋዮችህ ልቦቻቸውን የሚያስደስተውን ከምሕረትህ መንግስተ ሰማይና ፍቅር ከተመላበት የአንተ የርኅራኄ ደመናዎች እንድታዘንብላቸው፣ ሰዓቱ በደረሰበት፣ ትንሳኤውም በተፈፀመበት፣ ፍርሐትና መንቀጥቀጥም በእነዚያ በሰማይ በሚገኙት ሁሉ፣ በምድር ላይ በሚገኙትም ሁሉ ላይ በወረደበት ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡
ጌታ ሆይ፣ ወንድ አገልጋዮችህንና ሴት አገልጋዮችህን ከእውነት የራቁ እምነቶችና የከንቱ አስተሳሰቦች ጦሮች ሊያደርሱባቸው ከሚችሉት አደጋዎች እንድትጠብቃቸው፣ ከፀጋህም እጆች በለዘብታ የሚወርዱትን የዕውቀትህን ውሃዎች መጠጥ እንድትሰጣቸው እለምንሃለሁ፡፡
አንተ በእውነቱ ፍጹም ኃያሉ፣ ከሁሉ በላይ የተከበረው ፣ ዘላለም ይቅር ባዩ፣ ከሁሉም በላይ ለጋሱ ነህና፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የፍቅርህን ገመድ አጥብቄ በመያዝ፣ ራሴንም ሙሉ በሙሉ ለአንተ እንክብካቤና ለጥበቃህ በመስጠት ከቤቴ ወጥቻለሁ፡፡ ተወዳጆችህን ከእነዚያ ከትክክለኛው መንገድ ከራቁትና ከጠማማዎቹ፣ ከእያንዳንዱም አመፀኛ ጨቋኝ፤‹ ከእያንዳንዱም ከአንተ የራቀ ክፉ አድራጊ በጠበቅህበት ኃይልህ፣ እኔንም በቸርነትህና በፀጋህ ከማንኛውም አደጋ እንድትጠብቀኝ እማፀንሃለሁ፡፡ በስልጣንህና በኃያልነትህም በደህና ወደቤቴ ለመመለስ አስችለኝ፡፡
በእርግጥ አንተ ፍጹም ኃያሉ፣ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ፣ በገዛ ራሱም ነዋሪው ነህና፡፡
አምላኬ ሆይ! ማናቸውንም ፈቃዴን ሁሉ አንተ በቅዱስ ጽላትህ ላይ በፃፍከው መሠረት እንድወስን፣ በገዥነትህ ስልጣን ካዘዝከው ውጭ የሆነውን ምኞት ሁሉ እንዳልመኝ፣ በፈቃድህም ካዘዝክልኝ ዕድል በስተቀር የሌላ ፍላጎት ከቶ እንዳያድርብኝ፣ ግርማው ሰማይንና ምድርን በከበበው ስምህ እለምንሃለሁ፡፡
በል እግዚአብሔር ሁሉን ነገሮች ከሁሉም በላይ ያረካል፣ በሰማይና በምድር ከእግዚአብሐየር በስተቀር የሚያረካ የለም፣ በእውነቱ እርሱ በራሱ አዋቂው ህይወት ሰጪው ምንም የማይሳነው ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ! የሁሉን ነገሮች አስቀድሞ የታዘዘ በእጅህ መዳፍ ውስጥ ይዘሃልና፣ ለእኔና ለእነዚያ ለሚያምኑብህ፣ ያንን በእናንተ መጽሐፍ ውስጥ እንደሠፈረው በአንተ ግመት ይበልጥ፤እንደሚጠቅመን ያሰብከውን እዘዝልን፡፡ ነልካም ሥጦታዎችህ በእነዚያ ፍቅርህን በሚወዱት ላይ ያለማቋረጥ ይዘንባሉ፣ የመንግስተ ሰማያዊ በረከቶችህም ድንቅ ምልክቶች፣ ለእነዚያ መለኮታ አንድነትህን ለተቀበሉት በበቂ መጠን ይሰጣሉ፡፡ ለእኛ ያዘጋጀሀልንን ማንኛውንም ነገር ለጥበቃ ለአንተ እንሰጣለን፣ እውቀትህ የሚያቅፈውንም መልካም ነገረ ለጥበቃ ለአንተ እንሰጣለን፤ ዕውቀትህ የሚያቅፈውንም መልካም ነገር ሁሉ እንድትሰጠኝ እንማፀናለሁ፡፡
ጌታ ሆይ ፣ ሁሉን አዋቂነት ከሚያየው ክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን ኃይላና ብርታት በአንተ እንጂ በሌላ የለምና፣ ድል አድራጊነትም ከአንተ ዘንድ በቀር ከሌላ አይመጣምና፣ ማዘዙም የአንተ ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር የፈቀደው ማንኛውም ነገር ሆኗል፤ እርሱ ያልፈቀደውም አይሆንም፡፡
ከሁሉም በላይ በተከበረው፣ በፍጹም ኃያሉ አምላክ በቀር በሌላ ኃይልም ብርታትም የለም፡፡ አምላክ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን! አንተ ከሁሉ ነገሮች በፊት የነበርክ፣ ከሁሉ ነገሮች በኋላ የምትኖርና ከሁሉም ነገሮች በኋላም አልፈህ የምትቆይ አምላክ ነህ፡፡ አንተ ሁሉን ነገሮች የሚያውቀው፣ በሁሉ ነገሮችም ላይ የላቀ የበላይ የሆነው አምላክ ነህ፡፡ አንተ ሁሉን ነገሮች በምሕረት የምትዳሰሰው፣ በሁሉ ነገሮችም መካከል የሚፈርደው፣ የማየት ኃይሉም ሁሉን ነገሮች የሚያቅፈው አምላክ ነህ፤ አንተ አምላክ ጌታዬ ነህ፣ አንተ ስለሁኔታዬ ታውቃለህ፡፡ አንተ ውስጣዊውንና ውጫዊውን ህያውነቴን ታያለህ፡፡
ለእኔና ለጥሪህ መልስ ለሰጡት አማኞች ይቅር ባይነትህን ስጠን፣ ኃዘን ሊያደርስብኝ ከሚፈልግ ወይም ክፉ ከሚመኝልኝ ከማንኛውም ሰው ጉዳት የሚከላከልልኝ አርኪ ረዳቴ ሁን፡፡ በእውነቱ አንተ የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ጌታ ነህ፡፡ አንተ እያንዳንዱን ሰው ታረካለህ፤ ነገር ግን ማንም ያለ አንተ እርዳታ ራሱን የሚችል ለመሆን አይችልም፡፡
በስመ እግዚአብሔር በሚያርበደብደው ግርማ ጌታ በሁሉን አስገዳጁ!
የገዢነት ምንጭ በእጁ ውስጥ ያለው ጌታ የተቀደሰ ይሁን፡፡ እርሱ “ሁን” ሲል በሚሆነው የትዕዛዝ ቃሉ የፈቀደውን ማንኛውንም ነገር ይፈጥራል የሥልጣን ኃይል ከዚህ በፊት የእርሱ ነበር፣ ለወደፊቱም የእርሱ መሆኑን ይቀጥላል፡፡ እርሱ የፈለገውን ማንኛውንም ሰው በትዕዛዙ ፍጹም ኃይል ድል አድራጊ ያደርገዋል፡፡ እርሱ በእውነቱ ኃይል የተመላው ፣ ፍጹም ኃይሉ ነው፡፡ በግልፀትና በፍጥረት ዓለማት በመካከላቸውም በሚገኘው በማንኛውም ውስጥ ክብርና ግርማ ሁሉ የእርሱ ናቸው፡፡ በእውነቱ እርሱ ምንም የማይሳነው፣ ንዑዱ ነው፤ ከእምቅድመ ዓለም ጀምሮ እርሱ የማይበገር ሃይል ምንጭ ነበር፡፡ በዚህም ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ እርሱ በእርግጥ ኃያልነትና የስልጣን ጌታ ነው፡፡ በሰማይና በምድር በመካከላቸውም የሚገኙት ዓለማት ሁሉ የአምላክ ናቸው፡፡ ስልጣኑም በሁሉም ነገሮች ላይ የላቀ የበላይ ነው፡፡ የምድርና የሰማይ ሀብት ሁሉ፣ በመካከላቸውም የሚገኙት ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው፡፡ ጥበቃውም በሁሉም ነገሮች ላይ ተዘርግቶ ይገኛል፡፡ እርሱ የሰማያጥና የምድር፣ በመካከላቸውም የሚገኝ የማንኛውም ነገር ፈጣሪ ነው፡፡ በእውነቱ እርሱ በሁሉ ነገሮች ላይ ምስክር ነው፡፡ እር በሰማያትና በምድር የሚኖሩትን፣ እንዲሁም በመካከላቸው የሚያገኙትን ሁሉ ስለሥራቸው የሚጠይቅ ጌታ ነው፤ በእውነቱ እግዚአብሔር ስለተሠሩት ስራዎች ለመጠየቅ ፈጣን ነው፡፡ እርሱ በሰማያትና በምድር በመካከላቸውም ለሚገኘው ሁሉ የተመደበውን ድርሻ መጠን ይወስናል፡፡ በእውነቱ እርሱ የላቀው ጠባቂ ነው፡፡ እርሱ የሰማይንና የምድርን በመካከላቸውም የሚገኘውን ነገር ሁሉ ቁልፎች በመዳፉ ውስጥ ይይዛል፡፡ እርሱ በገዛ ራሱ ፍላጎት፣ በራሱ ትዕዛዝ ስጦታዎችን ይሰጣል፡፡ በእርግጥ ፀጋው ሁሉን ያቅፋል፣ እንዲሁም እርሱ ሁሉን አዋቂው ነው፡፡
በል፤ እግዚአብሔር ለእኔ አርኪዬ ነው፣ እርሱ የሁሉንም ነገሮች ዓለም በመዳፉ ውስጥ የያዘው ነው፡፡ በሰማያትና በምድር በመካከላቸውም በሚገኙት የእርሱ ሠራዊት ኃይል፣ ከአገልጋዮቹ መካከል የፈለገውን ማንኛውንም ሰው ይጠብቃል፡፡ በእውነቱ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች ይጠብቃል፡፡ ጌታ ሆይ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ! በፊት ለፊታችንና ከበስተኋላችን፣ ከእራሶቻችን በላይ፣ ከበስተቀኛችን ከበስተግራችን ከእግሮቻችን በታችና በተጋለጥንበት በእያንዳንዱ ሌላ ጎን በኩል ከሚገኘው ከማንኛውም ነገር ጠብቀን፤ በእውነቱ አንተ ጥበቃ ከሁሉም ነገሮች ላይ አይቋረጥም፡፡
ጌታዬ ሆይ ህዝቦች ሁሉ በጭንቅና በመከራ፣ በልፋትና በችግር የተከበቡ መሆናቸውን አንተ ታውቃለህ፡፡ እያንዳንዱን ሰው ልዩ ልዩ ፈተና ይገጥመዋል፣ የእባብ ንክሻን የመሰለ አደገኛ ችግርም ይደርስበታል፣ ተከላካይነትና ጠባቂነት ከተመላው ከአንተ ክንፍ በስተቀር ሰው ሌላ መጠጊያና መሸሻ የለውም፡፡
አቤቱ አንተ መሐሪው አምላክ ሆይ ጌታዬ ሆይ ጠባቂነትህን የብረት ልብሴ፣ ክብካቤህን ጋሻዬ በአንተ አነድነት ደጅ ላይ ትህትና ማሳየቴን ጠባቂዬ፣ ተከላካይነትህንና መከታተነትህን ምሽጌና መኖሪያዬ አድርግልኝ፡፡ ለራሴና ለምኞቴ ቅድሚያ ከመስጠት ጠብቀኝ፤ ከማንኛውም ሕመም፣ ፈተና ችግርና ጭንቀት አድነኝ፡፡ በእውነቱ አንተ ጠባቂው ሞግዚቱ፣ በህይወት የሚያቆየው፣ አርኪው ነህና በእርግጥም አንተ ከሁሉ በላይ መሐሪዎች ከሆኑት ሁሉ በላይ ፈጹም መሐሪው ነህና፡፡
- Bahá'u'lláh