Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Steadfastness
ስምህ የተከበረ ይሁን አምላኬ ሆይ! ለአንተ ባለን ፍቅርና ለፈቃድህ በታዛዥነታችን ለመጽናት እታዎቻችንን በአንተ ፊት ላይ ለማተኮርና ክብርህን ለማወደስ እንድታስችለን፤ የተፈጠሩትን ነገሮች ሁሉ በከበበው ሥልጣንህ ከመላው ፍጥረት ልቆ በሚገኘው ሉዓላዊነትህ፣ በጥበብህ ውስጥ በተደበቀውና ምድርህንና ሰማይህን በፈጠርክበት ቃልህ እማጠንሃለሁ፡፡አምላኬ ሆይ የአንተን ምልክቶች በፍጡራንህ መካከል በሰፊው ለማሰራጨት፣ በመንግስትህም ውስጥ እምነትህን ለመጠበቅ፤ የሚያስችለንን ኃይል ስጠን፤ ከፍጡራንህ መካከል ማንኛውም ስምህን ሳያነሣ ራስህን ችለህ ዘለዓለም ኖረሃል፡፡ከእምቅድመ ዓለም ጀምረህ በነበርክበት ሁኔታ ዘለዓለም ትኖራለህ፡፡
ፍፁም እምነቴን በአንተ አኑሬአለሁ፡፡ ፊቴንም ወደ አንተ መልሼአለሁ፡፡ በፍቅራዊ ጥበቃህ ገመድ ላይ ተንጠላጥያለሁ፣ ወደ ምሕረትህም ጥላ ገስግሼአለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ተስፋው እንደተቀጨበት ሰው ከደጅህ አውጥተህ አትጣለኝ፤ አንተን ብቻ ስለምሻ ፀጋህን አትንሳኝ፤ ከአንተ ከዘለዓለም ይቅር ባዩ- ከሁሉም በላይ ለጋሱ በስተቀር ሌላ አምላክየለምና፡፡
አቤቱ ላወቁህ ሁሉ ተወዳጅ የሆንከው ሆይ ለአንተ ምስጋና ይድረስህ!
የፀጋና የምህረት ጌታ የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ በትዕዛዝ ቃሉ መላው ፍጥረት ወደመኖር የተጠራበት ንጉስ ነህ፤ የአገልጋዮቹ ተግባሮች ፀጋውን ከመለገስ ያልገቱት የቸርነቱንም መገለፅ ሊያስቀሩ ያልቻሉት ፍጹም ቸር ጌታ ነህ፤
ይህ አገልጋይህ በአለሞችህ እያንዳንዱ ዓለም የደህንነቱ ምክንያት የሆነውን እንዲያገኝ ታደርገው ዘንድ እማፀንሃለሁ፡፡ አንተ በእውነቱ ፍፁም ኃያሉ ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህና፡፡ ከሁሉም በላይ ተወዳጄ የሆንክ ጌታ ሆይ፣ ምስጋና ለአንተ ይሁን! በእምነትህ ጽኑ አድርገኝ፣ ከእነዚያ ቃል- ኪዳንህን ካልጠሱት፣የራሳቸውን ከእውነት የራቁ ከንቱ እምነቶችና ጣኦቶች ካልተከተሉትም ጋር እንድቆጠር ፈቃድህ ይሁን በአንተ ዘንድ የእውነት መቀመጫ ለማግኘት አስችለኝ፣ የምህረትህንም ምልክት አጎናጽፈኝ፣ ከእነዚያም ምንም ፍርሐት ከማይኖርባቸው፣ በኃዘንም ላይ ከማይጣሉት አገልጋዮችህ ጋር እንድቀላቀል አድርገኝ፣ ጌታዬ ሆይ ለራሴ አትተወኝ፣ እርሱን የአንተ የራስህ ክስተት የሆነውን ከማወቅ አትንፈገኝ፣ ከእነዚያ ከአንተ ቅዱስ መንበር ፊቶቻቸውን ከአዞሩትም ጋር አትቁጠረኝ፡፡ አምላኬ ሆይ ፣ ከእነዚያ ውበትህን አትኩረው ለማየት ከታደሱት፣ በዚያም ትልቅ ደስታን የሚደሰቱ በመሆናቸው፣ የዚያችን ትንሷን ጊዜ እንኳ በሰማያትና በምድር መንግስታት ግዛት ወይም በመላው ፍጥረት ዓለም ከማይለውጡት ጋር ቁጠረኝ ጌታ ሆይ የምድሩን ህዝቦች በአሳዛኝ ሁኔታ በተሳሳቱባቸው በእነዚህ ቀናት በእኔ ላይ ምሕረት ይኑርህ፡፡ አምላኬ ሆይ ስለዚህ ያንን በአንተ አስተሳሰብ ተገቢ የሆነውን ለግሰኘ፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ኃይል የተሞላው ፀጋ የተሞላው በረከት የተመላው፣ዘለዓለም ይቅር ባይ ነህና፡፡ አምላኬ ሆይ ከእነዚህ ጆሮዎቻቸው ከደነቆሩት፣ አይኖቻቸው ከታወሩት፣ አንደበታቸው ንግግር አልባ ከሆኑት ልቦቻቸው መገንዘብ ከተሳናቸው ጋር እንዳልቆጠር ፍቃድህ ይሁን፡፡
ጌታ ሆይ ከድንቁርናና ከራስ ወዳድነት ፍላጎት እሳት አድነን ወደ ላቀው ምህረትህም ክልል እንድገባ አድርገኝ፡፡ ያንን ለሕሩያንን ያዘዝከውንም በላዬ አውርድልኝ፡፡ የፈለግኽውን ለማድረግ ችሎታዬ ያለህ ነህና፡፡ በእውነቱ አንተ በአደጋ ጊዜ እረዳቱ በገዛ ራሱ ነዋሪው ነህ፡፡ አቤቱ አምላኬ ሆይ የተመሰገንክና የተወደስክ ነህ ወደ ቅዱስ ቅርበትህ የመድረስ መቀደጃው ቀን በፍጥነት እንዲቃረብ ፈቃድህ ይሁን፡፡ በፍቅርህና በመልካም ደስታ ኃይል ልቦቻችንን አስደስትልን ለፍላጎትህና ለትዕዛዝህም በፈቃደኝነት እንድገዛ ጽኑመትን አጎናጽፈን፡፡ በእውነቱ እውቀትን የፈጠርካቸውንና የምትፈጥራቸውን ነገሮች ሁሉ ያቅፋል፡፡ የመንግስተ ሰማይ የሆነው ሃያልነትህን ወደ መኖር ከጠራኽንና ከምትጠራው ከማንኛውም ነገር ይልቃል፡፡ ከአንተ በቀር የሚሰገድለት ማንም የለም፡፡ ከአንተ በቀር የሚፈለግ ማንም የለም፣ካንተ በቀር የሚመለክ ማንም የለም፡፡ በበጎ ፈቃድህም ፈቃድህም በቀር ምንም የሚወደድ የለም፡፡ በእውነቱ አንተ ከሁሉ በላይ ከፍተኛው ገዥ የላቀ እውነት በአደጋ ጊዜ እረዳቱ በገዛ ራሱ ነዋሪው ነህና፡፡ ጌታ ሆይ አምላኬ ሆይ! ተወዳጆችህ በእምነትህ እንዲጠነክሩ፣ በመንገድህ እንዲራመዱ፣ በሃይማኖትህ እንዲፀኑ እርዳቸው ፡፡ እኔነትንና የብርቱ ስሜት ውርጂብኝ ወረራን ለመቋቋምና የመለኮታዊ መርሖን ብርሃን ለመከተል የሚያስችላቸውን ጸጋህን ስጣቸው፡፡ አንተ ኃይል የተመላው ፣ፀጋ የተመላው በገዛ ራሱ ነዋው ለጋሱ፣ሩኅሩኁ፣ ፍጹም ኃያሉ፣ፍጹም በረከት የተመላው ነህና፡፡
- Bahá'u'lláh