Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Spiritual Qualities
በል፣ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ራሴን በፍትሕ ዘውድ፣ አካሌንም በትክክለኝነት ጌጥ አጎናጽፈው፣ አንተ በእውነቱ የስጦታዎችና የበረከቶች ባለቤት ነህና፤
አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ውበትህ ህብስቴ የአንተ ቅርበት ብርሃንም ጽዋዬ የአንተም ፍላጎት ተስፋዬ አንተን ማወደስም ሥራዬ አንተን ማስታወስም ባልደረባዬ፣ የአንተ ሉዓላዊነትም እርዳታዬ የአንተ መኖሪያ ስፍራም መኖሪያ ቦታዬ ልክ በግርዶሽ እንደተከለሉ ከአንተ ከተዘጉት ሰዎች ገደቦች በላይ ከፍ ያደረግኽው መኖሪያ ሥፍራም መኖሪያ ቤቴ እንዲሆንልኝ ፈቃድህ ይሁን፡፡ በአውነቱ አንተ የስልጣን፣ የብርታትና የክብር አምላክ ነህና፤
አምላኬ ሆይ፣ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፣ አለኝታዬ ሆይ፣ የተረጋጋ ኅሊናዬንም በውስጤ አድስ! ከሁሉም በላይ ተወዳጄ ሆይ በኃይል መንፈስ ከእምነትህ ጋር አቆራኘኝ፤ የልቤ ዓላማ ሆይ፣ በክብርህም ብርሃን መንገድህን ግለጽልኝ፡፡ የሕይወቴ ምንጭ ሆይ ፍጹም በላቀው ኃያልነትህ ስልጣን ወደ ቅድስናህ ሰማይ ከፍ አድርገኝ፡፡ አንተ አምላኬ የሆንክ ሆይ፤ በዘለዓለማዊነትህም ልዝብ ነፋስ ሐሴትን ስጠኝ! ባልደረባዬ ሆይ ፣ ዘለዓለማዊ የዜማህ ቃናዎች ሰላምን ያውርዱልኝ፤ ጌታዬ ሆይ፣ የጥንታዊ ገጽህ በረከቶችም ከአንተ በስተቀር ከሌላው ነገር ሁሉ ይጠብቁኝ፤ አቤቱ አንተ የግልጽ ፍጹም ግልጽ፣ የስውር ፍጹም ሥውር የሆንክ ሆይ፣ የማይበላሸው የመለኮታዊ ሕላዌህ ግልፀት የምስራች ሐሴትን ያምጣልኝ፡፡
አምላክ ሆይ፣ ለሰው ዘር ላሳየኽው ፍቅር ክብር ላንተ ይሁን! አቤቱ አንተ ህይወታችንና ብርሃናችን የሆንክ ሆይ፤ አገልጋዮችህን በመንገድህ ምራቸው በአንተም እንድንበለፅግ አድርገን፣ ከአንተም በስተቀር ከሌለው ነገር ሁሉ አንፃን፡፡
አምላክ ሆይ፣ አንተን እንጂ ሌላውን ነገር እንዳናይ ስለአንድነትህ አስተምረን፤ ስለ አንድነትህም ግንዛቤን ስጠን፡፡ አንተ መሐሪውና ፀጋ ሰጪው ነህና፡፡ አምላክ ሆይ፣ የአንተን በስተቀር የእያንዳንዱን ሌላ ነገር ሀሳብ እንዲያጋይ በተወዳጆችህ ልቦች የፍቅርህን እሳት አቀጣጥል፡፡ አምላክ ሆይ፣ ከእምቅድመ ዓለም የነበርክ እስከ ዘለዓለምም የምትኖር መሆንህና ከአንተም በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እንገነዘብ ዘንድ የተከበረ ዘለዓለማዊነትህን ግለጽልን፤ በእውነት በአንተ ምቾትንና ጥንካሬን እናገኛለን፡፡
እነዚያን ከትክክለኛ መንገድ ወደ ስሕተት መንገድ የተመሩትን ትክክለኞችና የማያዳሉ እንዲሆኑ፣ ደንታቢስ የሆኑበትን እንዲገነዘቡ በፀጋው እንዲረዳቸው እግዚአብሄርን እንለምነዋለን፡፡ እርሱ በእውነቱ ፍጹም ፀጋ የተመላው ከሁሉም በላይ ለጋሱ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ ፣አገልጋዮችህን ከፀጋህ በር አትከልክላቸው፣ ከቅርበትህም መንበር አታርቃቸው፡፡ የአጉል እምነትን ጭጋግ እንዲያስወግዱ፣ የከንቱ አስተሳሰብንና የከንቱ ምኖትን ግርዶሽ ቀዳደው እንዲጥሉ በፀጋህ እርዳቸው፡፡ አንተ በእውነቱ ሁሉ ነገር ያለው፣ ከሁሉ በላይ ከፍተኛው ነህ፤ ከአንተ ከፍጹም ኃያሉ፣ ፀጋ ከተመላው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡
- Bahá'u'lláh