Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Spiritual Qualities
(በሴት የሚደረግ)
አቤቱ ጌታዬ ሆይ! እኔ አከንተ ሴት አገልጋዮች መካከል አንዷ ነኝ፡፡ ፊቴን ፀጋ ወደተመላበት ችሮታዎችህ ክልልና ወደሚመለከተው የክብርህ መቅደስ መልሼአለሁ፡፡ ውበትህን በማሰላሰል እንድደሰት ከፍጡሮችህ መካከል ከማንኛውም ጋር በአጉል ቁራኛነት ከመጣበቅ ሁሉ እንድላቀቅ፤ በእያንዳንዷም ቅጽበት “ የዓለማት ጌታ የሆነው አምላክ የተወደሰ ይሁን” በማለት እንዳውጅ፣ የአንተ ካልሆነው ነገር ሁሉ አንፃኝ፣ አንተንም እንዳፈቅርና ፍላጎትህን ለማሟላት እንድችል አበርታኝ፡፡
አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ውበትህ ህብስቴ፣ የአንተ ቅርበት ብርሃንም ጽዋዬ፤ የአንተም ፍላጎት ተስፋዬ አንተን ማወደስም ስራዬ፣ አንተን ማስታወስም ባልደረባዬ፣ የአንተ ሉዓላዊነትም እርዳታዬ፣ የአንተ መኖሪያ ሥፍራም መኖሪያ ቦታዬ ልክ በግርዶሽ እንደተከለሉ ከአንተ ከተዘጉት ሰዎች ገደቦች በላይ ከፍ ያደረግኽው መኖሪያ ሥፍራም መኖሪያ ቤቴ እንዲሆልንኝ ፈቃድህ ይሁን፡፡
በእውነቱ አንተ የስልጣን÷ የብርታትና የክብር አምላክ ነህና፡፡
አቤቱ አንተ የአገሮች ፈጣሪና የዘለዓለም ንጉሥ የሆንከው ሆይ÷ ሴት አገልጋዮችህን በአንተ የክብረ ንጽህና መቅደስ ውስጥ እንድትጠብቃቸው÷ እነዚያን ለቀናትህ ብቁ ያልሆኑትን አይነት አድራጎታቸውንም ይቅር እንድታለቸው እማፀናለሁ፡፡ አማልኬ ሆጥ ጥርጣሬዎችንና ከንቱ አስተሳሰቦችን ከእነሱ አንፃ፡፡ አቤቱ አንተ የስሞች ሁሉ ጌታና የንግግር ምንጭ ተገቢ ካልሆኑት ከማናቸውም ነገሮች ቀድሳቸው፡፡ አንተ የመላው ፍጥረት ግዛት በመዳፍህ ውስጥ ያለው ነህና፡፡ ከአንተ ከፍጹም ኃይሉ ከሁሉም በላይ ከተከበረው ከንዑድ በገዛ ራሱ ከሚኖረው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አምላክ ሆይ! መንፈሴን አድስልኝ፣ አስደስትልኝም ልቤን አንፃልኝ፡፡ አዕምሮዬን አብራልኝ፡፡ ጉዳዮቼን ሁሉ በአንተ ላይ ጥዬአለሁ፡፡ አንተ መሪዬና መሸሻዬ ነህ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ የተከፋሁና ኃዘንተኛ አልሆንም፣ ደስተኛና በሐሴት የተመላሁ እሆናለሁ፡፡ አምላክ ሆይ፤ ከእንግዲህ ወዲያ በሥጋት ውስጥ አልዋኝም፣ ችግርም እንዲያስጨንቀኝ መንገድ አልሰጥም፤ ደስ በማያሰኝ የህይወት ነገር ውስጥ አልኖርም፡፡ አምላክ ሆይ! አንተ ከራሴ ይልቅ ለኔ ትራራልኛለህ፡፡ ጌታ ሆይ፣ ራሴን ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁ፡፡
አቤቱ አንተ ሩኅሩህ አምላክ ሆይ፣ አንተ ከራሴ ይልቅ ትራራልኛለህ፡፡ ፍቅርህም በጣም ከፍተኛና እምቅድመ ዓለማዊ ነው፡፡ የአንተን በረከት ባስታወስኩ ጊዜ ደስተኛና ባለተስፋ ነኝ፡፡ በምበሳጭበት ጊዜ የልብና የነፍስ ዕረፍት አገኛለሁ፡፡ በምታመምበት ጊዜ ዘለዓለማዊ ጤንነት ይኖረኛል፡፡ እምነቴን በማጓድልበት ጊዜ ታማኝ እሆናለሁ፡፡ ተስፋ ቢስ በምሆንበት ጊዜ ተስፋ ይኖረኛል፡፡
አቤቱ አንተ የመንግስቱ ጌታ ሆይ! ልቤን ደስ አሰኝልኝ፡፡ ደካማ መንፈሴን በአርታልኝ፡፡ የቆረቆዙ ጅማቶቼንም አጠንክርልኝ፣ አይኖቼንም አብራልኝ፣የመንግስትህን ዜማ እንድሰማና ዘለዓለማዊ ተድላና ደስታ እንዳገኝ ጆሮዎቼን አንቃልኝ፡፡ በእውነቱ፣ አንተ ቸሩ ሰጪውና ሩኅሩኁ ነህና፡፡
አቤቱ የተከበርክ ጌታዬ ሆይ! አንተን ለማገልገልና ቃልህንም ለማስተማር እበቃ ዘንድ፣ ከማንኛውም ህገወጥ ዝንባሌ እንድታቀብ፣ ማንኛውንም አመፀኛ ስሜት እንዳሸንፍ፣ የምግባሬንም ዓላማ እንዳነፃ፣ ምንም ትንኮሳ በማይረብሸው ትሑትነት፣ ምንም ስቃይ በማይበግረው ትዕግስት ምንም ራስ ወዳድነት በማያናውጠው ሐቀኛነት እንድኖር እርዳኝ፡፡
አቤቱ አንተ ሩኅሩኁ አምላክ ሆይ! እንደ መስታወት በፍቅርህ ብርሃን የሚያንፀባርቅ ልብ ፍጠርልኝ፡፡ ይህን ዓለም በመነፍሳዊ የፀጋ ጎርፎች አማካይነት ወደ ጽጌረዳ አትክልት ሥፍራ ለመለወጥ የሚያስችሉኝን አስተሳሰቦች ለግሰኝ፡፡ አንተ ሩኅሩኁ ፣መሐሪው ነህና! አንተ ታላቁ ቸር አምላክ ነህና፡፡
- Bahá'u'lláh