Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Contributions
የእግዚአብሔር ወዳጆች ሁሉ፣ የሚሰጡት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም እንኳ፣ የሚችሉትን ያህል ማዋጣት አለባቸው፣ እግዚአብሔር ማንኛዋንም ነፍስ ከአቅሟ በላይ አይፈልግባትም፡፡ እንዲህ ያለው መዋጮ ከሁሉም ማዕከሎችና ከሁሉም ምዕመናን መምጣት አለበት፤ የእግዚአብሔር ወዳጆች ሆይ ለእነዚህ ለምታዋጡአቸው መዋቾዎች አፀፋ፣ እርሻዎቻችሁ ኢንዱስትሪዎቻችሁና ንግዶቻችሁ በብዙ እጥፍ ጭማሪዎች፣ በመልካም ስጦታዎችና ገፀበረከቶች እንደሚባረኩ እርገጠኞች ሁኑ፣ አንድ መልካም ሥራ የሚሠራ አሥራ እጥፍ ዋጋ ይቀበላል፡፡ ለእነዚያ ሀብታቸውን በእርሱ መንገድ ሥራ ላይ ለሚያውሉት ሕያው ጌታ በተትረፈረፈ ሁኔታ ማረጋገጫ እንደሚሰጣቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
- Bahá'u'lláh