Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Education
ጌታ አምላኬ ሆይ፤ ምስጋና ለአንተ ይሁን! ማንም ሰው በሚገባ ባላወቀው፣ ታላቅነቱንም ማንም ነፍስ ባልተረዳው ስምህ እማፀናሀለሁ፤ ልቤን የፍቅርህና የትውስታህ ማኅደር እንድታደርግልኝ፣ በእርሱ የግልፀትህ ምንጭና የምልክቶችህ ጎሕ በሆነው እማፀንሃለሁ፡፡ እንዲሁም ከዚህ ከልቤ የጥበብህ የህይወት ውሃዎች፣ የውዳሴህና የምስጋናህ ንጹህ ጅረቶች ይወርዱ ዘንድ ከታላቁ ውቅያኖስህ ጋር አገናኘው፡፡
የአካሌ መለያልዮች ስለአንድነትህ ይመሠክራሉ፤ የእራሴ ፀጉርም ስለሉዓላዊትህና ስለታላቅነትህ ኃይል ያውጃል፡፡ ራሴን ፍጹም ዝቅ በማድረግና ሙሉ በሙሉ በመርሳት በፀጋህ በር ላይ ቆሜአለሁ፣ በቸርነትህም ካባ ጠርዝ ላይ ተጠንላጥያለሁ፤ የዓይኖቼንም እይታ ወደ ስጦታዎችህ አድማስ መልሼአለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ ለግርማህ ታላቅነት የሚገባውን ዕድል ወስንልኝ ሙታንም ከመቃብሮቻቸው በፍጥነት በመውጣትና እምነታቸውን ሙሉ በሙሉ በአንተ ላይ በመጣል፣ የእይታቸውንም ትኩረት ወደ እምነትህ አቅጣጫና ወደ ግልፀትህ የንጋት ሥፍራ በመመለስ ወደ አንተ በፍጥነት እንዲለግሱ እምነትህን እንዳስተምር፣ በሚያጠናክረው ፀጋህ እርዳኝ፤
አንተ በእውነቱ ፍጹም ÷ ኃይል የተመላው÷ ፍጹም ከፍተኛው ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህና፤
አምላክ ሆይ! የአገልጋዮችህ ጉዳይ ሁሉ እንዲሰምር ከተሞችህም እንዲያብቡ ለማድረግ እንድንችል ትረዳኝ ዘንድ፣ከሁሉም በላይ በተከበረው ስምህ እለምንሃለሁ፡፡ አንተ በአውነቱ በሁሉም ነገሮች ላይ ስልጣን ያለህ ነህና፡፡ አቤቱ አንተ እጅግ ተዋጄ ሆይ! በሕግ ተላላፊዎች ከባድ ወረራም ሆነ በከሃዲዎች ቁጣ በማናውላውልበት ሁኔታ ስምህን ከፍ ከፍ ለማድረግ መልዕክትህን ለማስተላለፍና እምነትህን ለማወጅ እንድንችል እኔንም አገልጋዮችህንም በፀጋህ እንድትረዳን ÷ ሰላም ማጣትን ወደ እርጋታ፣ ፍርሐትን ወደ ልበ ሙሉነት÷ ድክመትን ወደ ብርታት÷ ውርደትንም ወደ ክብር በምትለውጥበት ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡
ጌታዬ ሆይ! እኔ ወደ አንተ ጥሪ ያዳመጥኩ÷ ወደ አንተም ለመቅረብ የፈጠርኩ÷ ከራሴም በመሸሽ ልቤን በአንተ ላይ ያሳረፍኩ ሴት አገልጋይህ ነኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ÷ ከእነዚያ በአንተ ባላመኑትና የአንተን እውነት በአስተባበሉት ሰዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ከሚሰነዝረው ሃሳብ እንድትመክተኝ÷ ከውስጡ የምድር ሀብቶች ሁሉ እንዲመጡ በተደረጉበት ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡ አንተ የሚያስደስትህን ለማድረግ ኃይል የተመላው ነህ፡፡ አንተ በእውነቱ ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህ፡፡
ተወዳዳሪ ሌለህ አምላክ ሆይ! አቤቱ አንተ የመንግስቱ ጌታ! እነዚህ ነፍሶች መንግስተ ሰማያዊ ሠራዊትህ ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው እንደ አንድ ጦር ኃይል በመሆን በእግዚአብሔር ፍቅርና በመለኮታዊ ትምህርት ውጋገን እነዚህን ሀገሮች ያስገብሩ ዘንድ በከፍተኛው የሰማይ ሠራዊት ቡድኖች እርዳቸው፡፡
አምላክ ሆይ! ድጋፍና እርዳታ ሁንላቸው በመንግስትህ ኃይልና በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ድምፃቸውን ያሰሙ ዘንድ በምድረ በዳ፣ በተራራ፣ በሸለቆ፣ በጥሻ፣ በሜዳና በባህር አለኝታ ሁናቸወው፡፡
በእውነቱ አንተ፣ ኃይል የተመላው፣ ኃያሉና ምንም የማይሳነው ነህና፣ እንዲሁም አንተ ጠቢቡ ሁሉን ሰሚውና የሚያየው ነህና፡፡ አምላኬ ሆይ! አምላክ ሆይ ! ይሀ ከንፈ ሰባራ ወፍነው በረራውም በጣም ዝግተኛ ነው፣ ወደ ብልጽግናና ወደ መዳን ከፍታ ጫፍ ለመብረር እንዲችል፣ በከፍተኛ ሐሴትና ደስታ ወሰን በሌለው ሕዋ ስፋት ውስጥ እንዲከንፍ፣ በላቀው ስምህ በሁሉም አካባቢዎች ዜማውን እንዲያሰማ፣ በዚህም ጥሪ ጆሮዎችን እንዲያስደስት፣ አይኖችም የመርሖን ምልክቶች በማየት እንዲበሩ እንዲያደግ እርዳው!
ጌታ ሆይ! እኔ ረዳት የሌለኝ፣ ብቸኛና ዝቅተኛ ነኝ፡፡ ለእኔ ከአንተ በስተቀር ሌላ ደጋፊ፣ ከአንተ በስተቀር ሌላ ደጋፊ፣ ከአንተ በስተቀር ሌላ ረዳት፣ ከአንተም ሌላ የሚያኖረኝ የለም፡፡ ለአገልግሎትህ አጠናክረኝ፣ በመላእክትህ ሠራዊት እርዳኝ፣ ቃልህን በማሰራጨት ተግባሬ ድልን አጎናጽፈኝ፣ በፍጡራንም መካከል የአንተን ጥበብ እንድለፍፍ አድርገኝ፡፡ በእውነቱ፣ አንተ ለደካሞች ረዳቱ፣ በዝቅተኞችም ተከላካዩ ነህና፣ በእውነቱም አንተ ኃይል የተመላው፣ ኃያሉና የማይገታው ነህና!
እግዚአብሔር ምላኬ ሆይ! ድቅድቅ ጨለማ አካባቢዎችን ሁሉ መክበቡን፣ ሀገሮችም ሁሉ በሀሳብ ቅራኔ ሰደድ እሳት እየጋዩ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በምድር ምስራቆችና በምዕራቦችዋ ሁሉ እንዴት የጦርነትና የእልቂት እሳት እንደተቀጣጠለ አንተ ታያለህ፡፡ ደሙ እጎረፈ ነው፤ አስከሬኖችም በመሬት ላይ ተዘርረዋል፣ የተቀሉ ጭንቅላቶችም በጦራ ሜዳ አቧራ ላይ ተጥለዋል፡፡
ጌታ ሆይ! በእነዚህ ደናቁርት ላይ ኃዘኔታ ይኑርህ፣ በምህረትና በይቅርታ አይንም ተመልከታቸው እነዚህ አድማሱን የሸፈኑት ጥልቅ ደመናዎች ይበተኑ ዘነድ፣ የእውነት ፀሐይ በዕርቅ ጨረሮች ይበራ ዘንድ፣ ይህ ጥልቅ ጨለማ ይወገድ ዘንድ፣ የሰላም ደማቅ ብርሃንም ጮራውን በሁሉም አገሮች ላይ ይፈነጥቅ ዘንድ ይህን እሳት አጥፋው፡፡
ጌታ ሆይ! ህዝቦችን ከጥላቻና ከጠላትነት ውቅያኖስ አዘቅት አውጣቸው፣ ከዚያም ከማይበገረው ጨለማ አድናቸው፡፡ ልቦቻቸውን አስተሳሰር፣ አይኖቻቸውንም በሰላምና በእርቅ ብርሃን አብራ፤ ከጦርነትና ከደም መፍሰስ አዘቅት አድናቸው፣ ከስህተት ጨለማም ነፃ አውጣቸው፣ ግርዶሹን ከዓይኖቻቸው ግለጥላቸው፣ ልቦቻቸውንም በመርሖ ብርሃን አብራ፤ በአዛኝ ምህረትህና ርኅራሄህ ያዛቸው እንጂ፣ የኃያሎቹን ቅልጥሞች እንኳ በሚያንቀጠቅጠው በአንተ ፍትህና በቁጣህ አትፍረድባቸው፤
ጌታ ሆይ! ጦርነቶች ተራዝመዋል፡፡ ጭንቀትና ሥጋት ተባብሰዋል፤ እንዳንዱም ለምለም አካባቢ ወደ ጠፍነት ተለውጧል፡፡ ጌታ ሆይ! ልቦች አዝነዋል፣ ነፍሶችም ተጨንቀዋል፡፡ በእነዚህ ምስኪኖች ነፍሶች ላይ ምሕረት ይኑርህ እንጂ ራሳቸው ለሚመኙት ከመጠን ያለፈ ፍላጎት አትተዋቸው፡፡
ጌታ ሆይ! ፎቶቻቸው በመርሐ ጨረር የበሩ፣ ከዓለም የተላቀቁ፣ስምህን የሚያወድሱ፣ የአንተን ምስጋና የሚናገሩ፣ በሰውም ዘር መካከል የቅዱስነትህን መዓዛ የሚያሰራጩ ትሑታንና ታዛዦች ነፍሶችን በአገሮችህ ሁሉ ውስጥ አስነሣ፡፡
ጌታ ሆይ! ጀርባዎቻቸውን አጠንክር፣ሽንጦቻቸውን ደግፍ፤ ከሁሉም በላይ ታላቅ በሆኑት በፍቅርህ ምልክቶችም ልቦቻቸውን አስደስት፡፡
ጌታ ሆይ! በእውነቱ እነርሱ ደካሞች ናቸው፤ አንተ ግን ብርቱውና ኃያሉ ነህ፣ እነርሱ አቅመቢሶች ናቸው፤ አንተ ግን ረዳቱና መሐሪው ነህ፤ ጌታ ሆይ! የአመጽ ውቅያኖስ እየሞገደ ነው፤ ሁሉንም አካባቢዎች ባቀፈው ወሰን በሌላው ፀጋህ በስተቀር እነዚህ ኃይለኛ ነፋሶች አይረጉም፤
ጌታ ሆይ ! በእውነቱ ህዝቦች በከፍተኛ መድራዊ ምኖት አዘቅት ውስጥ ናቸው፤ ወሰን ከሌለው ልግስናህም በስተቀር ምንም ነገር ሊያድናቸው አይችልም፡፡
ጌታ ሆይ! የእነዚህን የእርኩስ ምኞቶች ጨለማ አስወግድ፣ ሀገሮችም ሁሉ በቅርብ ጊዜ በሚበሩበት በፍቅርህ ፋኖስ ልቦችን አብራ፡፡ እነዚያን፣ ለውበትህ ፍቅር ሲሉ፣ አገሮቻቸውን ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን ጥለው፣ መዓዛዎችህን ለማሰራጨትና ትምህርቶችህን ለማስፋፋት ፣ ወደ ውጭ አገሮች የሚጓዙትን ተወዳዶችህን አጠንክራቸው፤ በብቸኝነት ጊዜአቸው ጓደኛ፣ በባዕድ አገር ረዳታቸው፣ የኀዘናቸው አስወጋጅ፣ በመከራ ጊዜ አጽናኝ፤ ሁንላቸው፤ ለጥማታቸው የሚያረካ መጠጥ፣ ለበሽታቸው ፈዋሽ መድኃኒት፣ የልቦቻቸው ስሜት ነበልባል አብራጅ ቅባት ሁን፤
በእውነቱ፣ አንተ ከሁሉም በላይ ለጋሱ፣ ወሰን የሌለው ፀጋ ባለቤት ነህ፣ እንዲሁም አንተ ሩኅሩኁና መሐሪው ነህና፡፡ አቤቱ አንተ ቸር ጌታ ሆይ ! የመርሖን አውራ ጎዳና ስለአሳየኽን፣ የመንግስትህን በሮች ስለከፈትክልንና ራስህንም በእውነት ፀሐይ አማካይነት ስለከሰትክልን ምስጋና ለአንተ ይሁን፤ ለዕውራን ማየትን ሰጥተሃል፣ ለደንቆሮዎች መስማትን አድለሃል፤ ሙታንን አስነስተሃል፣ ድሆችን አበልጽገሃል፣ መንገድ የሳትቱን መንገዱን አሳይተሃቸዋል፣ እነዚያን ከንፈሮቻቸው ደቁትን ወደ መርሐ ምንጭ መርተሃቸዋል፣ የተጠቀሙትንም ዓሶች ወደ እውነት ውቅያኖስ እንደደርሱ አድርገሃል፣ የሚንከራተቱትንም ወፎች ወደ ፀጋ የጽጌረዳ አትክልት ሥፍራ ጋብዘሃል፡፡
አቤቱ አንተ ፍጹም ኃያል ሆይ! እኛ ባሮችህና ምስኪኖችህ ነን፤ እሩቅ ነንና የአንተን ቅርበት እንሻለን፣ ለምንጭህም ውሃ እንጠማለን፣ ሕሙማን ነንና ፈውስህን እንናፍቃለን፡፡ በመንገድህ እንጓዛለን፣ ነፍሶች ሁሉ አምላክ ሆይ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራን የሚለውን ጩኽት ያሰሙ ዘንድ፣ መዓዛህን ከማሰራጨት በስተቀር ሌላ ዓላማና ተስፋ የለንም፡፡ ብርሃኑን ለማየት አይኖቻቸው እንዲከፈቱ፣ ከድንቁርና ጨለማ ነፃ እንዲወጡ፣ በመሪነትህም ፋኖስ ዙሪያ እንዲሰባሰቡ፣ ቁራሽ ቢሾች ድርሻቸውን እንዲቀበሉ፣ የተገለሉትም ሁሉ የምሥጢሮችህ ተካፋዮች እንዲሆኑ ፈቃህ ይሁን፡፡
ፍጹም ኃያል ሆይ! በምሕረትህ አስተያየት ተመልክተን፤ መንግስተ ሰማያዊ ማረጋገጫን አድለን፡፡ ለአገልግሎትህ እንዲረዳንና እንደ አንፀባራቂ ከዋክብት የምሖህን ብርሃን በእነዚህ ክፍለ ሀገሮች እንድናበራ የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ አጎናጽፈን፤ አንተ በእርግጥም ብርቱው፣ ኃያሉ ጠቢቡና የሚያየው ነህና፤
- Bahá'u'lláh