Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Long Healing
እርሱ ፈዋሹ፣ አርኪው ረዳቱ ፍጹም መሐሪው ነው፡፡ አንተን እጠራለሁ አቤቱ የተከበረው ሆይ፣ ታማኙ ሆይ፣ክብር የተመላው ሆይ! አንተ አርኪው፣ አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው ፤ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ወደር የሌለው ዘለዓለማዊው ሆይ፣ አንድዬው ሆይ! አንተ አርኪው፣ አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ከሁሉም በላይ የተወደሰው ሆይ፣ ቅዱስ ሆይ አጋዡ ሆይ፣ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ፣ አንተን እጠራለሁ አቤቱ ወደር የሌለው ሆይ፣ ዘለዓለማዊው ሆይ፣ አንድዬው ሆይ! አንተ አርኪው፣ አንተ ፈዋሹ፣ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ከሁሉም በላይ የተወደሰው ሆይ ቅዱሱ ሆይ፣ አጋዡ ሆይ ፣ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ሁሉን አዋቂው ሆይ ፍጹም ጠቢቡ ሆይ፣ ከሁሉም በላይ ታላቁ ሆይ፤ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነወሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ! አቤቱ ሉዓላዊው ሆይ፣ ከፍ አድራጊው ሆይ ፈራጁ ሆይ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ፣ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ወደር የሌለው ሆይ፣ ዘለዓለማዊው ሆይ ፣ አንድዬው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ ፣ አንተ ነዋሪው ፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ከሁሉም በላይ የተወደሰው ሆይ፣ ቅዱስ ሆይ አጋዡ ሆይ፣ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ፣ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ተወዳጁ ሆይ፣ ክቡሩ ሆይ፤ ከሁሉም በላይ ደስተኛው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ከሁሉም በላይ ኃያሉ ሆይ፣ አነዋሪው ሆይ ምንም የማይሳነው ሆይ! አንተ አርኪው ፣ አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ገዥው ሆይ፣ በገዛ ራሱ ነዋው ሆይ፣ ሁሉን አዋቂው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ መንፈስ ሆይ፣ ብርሃን ሆይ፣ ከሁሉ በላይ ግልጹ ሆይ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ በሁሉ የምትዘወትረው ሆይ፣ አንተ በሁሉም የምትታወቀው ሆይ አንተ ከሁሉም ስውር የሆንከው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ፣ አንተ ነዋሪው ፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ድብቁ ሆይ፣ ድል አድራጊው ሆይ፣ ለጋሱ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ፍጹም ኃያሉ ሆይ፣ ረዳቱ ሆይ ሰዋሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ሰሪው ሆይ አርኪው ሆ፣ ነቃዬ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አስነሺው ሆይ ሰብሳቢው ሆይ፣ ከፍ አድራጊው ሆይ አንተ አርኪው፣ አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ፍጹም የምታደርገው ሆይ፣ የማይገታው ሆይ፣ ፀጋ ተመላው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ቸሩ ሆይ ከልካዩ ሆይ፣ ፈጣሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ትክክለኛው ሆይ ፣ ፀጋ የተመላው ሆይ፣ ለጋሱ ሆይ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋወው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ሁሉን አስገዳጁ ሆይ ዘላለም ነዋሪው ሆይ ከሁሉም በላይ አዋቂው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ እጹብ ድንቁ ሆይ! ቀናት ቀደምቱ ሆይ ቸሩ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ የማደፈረው ሆይ የሐሴት ጌታ ሆይ፣ ተናፋቂው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋው አቤቱ አንተ ነዋው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ለሁሉ ደጉ ሆይ፣ ለሁ ሩኅሩኁ ሆይ ከሁሉም በላ በጎ አድራጊው ሆይ! አንተ አርኪው፣ አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ለሁሉ አለኝታ ሆይ፤ ለሁሉ መጠለያ ሆይ ሁሉን ጠብቆ አኑዋሪው ሆይ! አንተ አርኪው፣ አንተን እጠራለሁ አቤቱ ለሁሉ አለኝታ ሆይ፣ ለሁሉ መጠለያ ሆይ፣ ሁሉን ጠብቆ አኑዋሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ የሁሉ ረዳት ሆይ አንተ በሁሉም ተለማኜ ሆይ ህይወት ሰጪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱአንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ገላጩ ሆይ፣ አፈራራሹ ሆይ ከሁሉን በላይ መሐሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተነዋው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ የሁሉ ረዳት ሆይ፣ አንተ በሁሉም ተለማኜ ሆይ፣ ህይወት ሰጪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ገላጩ ሆይ፣ አፈራራሹ ሆይ ከሁሉም በላይ መሐሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ነፍሴ ሆይ፤ አንተን የኔ ተወዳጅ ሆይ፣ አንተ እምነቴ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ ፣ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ ጥማትን አርኪው ሆይ፣ ከሁሉም የላቀው ጌታ ሆይ፣ ከሁሉ በላይ ብርቁ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ ፣ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ከሁሉ በላይ ታላቁ ትውስታ ሆይ፣ ከሁሉ በላይ ቅዱሱ ስም ሆይ ከሁሉ በላይ ጥንታዊው መንገድ ሆይ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ ከሁሉም በላ የተወደሰው ሆይ፣ ከሁሉም በላይ ቅዱሱ ሆይ! ብሩኩ ሆይ አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ለኳሹ ሆይ፣ ብሩህ አድራጊው ሆይ፣ ደስታ እምጪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው ፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ! አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ የበረከት ጌታ ሆ! ከሁሉ በላይ ሩኅሩኁ ሆይ ከሁሉም በላይ መሀሪው ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ የማይለወጠው ሆይ ህይወት ሰጪው ሆይ፣ የሕያው ሁሉ ምንጭ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ሁሉን ነገሮች ጠልቀህ የምታውቀው ሆይ፣ ሁሉን የምታየው አምላክ ሆይ፣ የልሳን ጌታ ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ ግልጽ ሆኖም ስውር የማይታየው ሆኖም ተዋቂው ሆይ፣ በሁሉም የሚፈለገው ተመልካች ሆይ! አንተ አርኪው አንተ ፈዋሹ አንተ ነዋሪው፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተ አፍቃሪዎችን የምትሰዋው ሆይ፤ ለክፉዎች የፀጋ አምላክ ሆይ!
አርኪው ሆይ፣ እጠራሃለሁ አርኪው ሆይ!
ፈዋሹ ሆይ፣ እጠራለሁ ፈዋሹ ሆይ!
ነዋሪው ሆይ፣ እጠራሃለሁ ነዋሪው ሆይ!
አንተ ዘለዓለም ነዋሪው፣ አቤቱ አንተ ነዋሪው ሆይ!
አምላኬ ሆይ ፣ አንተ የተቀደስክ ነህ1 የልግስናህና የፀጋህ በሮች በሰፊው በተከፈቱበትና የቅድስናህ መቅደስ በዘለዓለም ዙፋን ላይ በተተከለበት ቸርነትህ፤ የተፈጠሩትን ነገሮች ሁሉ ወደ አንተ ልግስናዎችና ስጦታዎች ገበታ በጠራህበት ምሕረትህ፣ ሉዓላዊነትህና ታላቅነትህም ተገልፆ በቆመበት ሰዓትና የግዛትህ ኃያልነት እንዲገለጽ በተደረገባት የንጋት ጊዜ አዎን በሚለው ቃልህ በሰማይና በምድር በሚገኙት ሁሉ ፈንታ በገዛ ራስህ መልስ በሰጠህበት ፀጋህ እማጠንሃለሁ፡፡ እንደገናም ይህን የተባረከውን መልዕክት የያዘውን የሚደግመውን፣ መልዕክቱ ጋ የሚደርሰውንም መልዕክቱ በሚገኝበት ቤት አካባቢ የሚያልፈውንም ሁሉ እንድትጠብቅ፣ በእነዚህ ከሁሉም በላይ ውብ በሆኑት ስሞች፣ በእነዚህ ከሁሉም በላይ የተከበሩ እና ከሁሉም በላይ የላቁ ባህሪያት ከሁሉ በላይ በተከበረው ትውስታህ በንጹህና ምንም ጉድፍ በማይገኝበት ውበትህ ከሁሉም በላይ ህቡዕ በሆነው አዳራሽህ ውስጥ በተደበቀው ብርሃንና በእያንዳንዱ ንጋትና ምሽት የመከራን ካባ ባጠለቀው ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡ እንግዲህ በዚህ መልዕክት አማካኝነት እያንዳንዱን ህመምተኛ በሽተኛውንና ምስኪኑን ከእያንዳንዱ መከራና ጭንቀት ከእያንዳንዱ አስከፊ ስቃይና ሀዘን አንፃው በዚሁም መልዕክት ወደ መመሪያ መንገዶች ወደ ይቅርባይነትህና ወደ ፀጋህም ጎዳናዎች ለመግባት የሚሻውን ማንኛውም ሰው ምራው፡፡
አንተ በእውነቱ አያል የተመላው ፍጹም አርኪው ፈዋሹ፣ ጠባቂው ፣ሰጪው፣ሩህሩህ ፍጹም ለጋሽ፣ ፍጹም መሐሪ ነህና ፤
- Bahá'u'lláh