Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Naw-Ruz
ናውሩዝ መጋቢት 12 ቀን የባሃኢ ዓመት የመጀመሪያ ቀን እንዲሁም የደስታና የመስተንግዶ ዕለት ነው፡፡
አምላኬ ሆይ ለአንተ ፍቅር ሲሉ አንተን ከሚያስከፉ ነገሮች ሁሉ ተጠብቀው ለጾሙት የናውሩዝን ክብረ በዓል ስለሰየምክላቸው ምስጋና ለአንተ ይሁን፡፡ ጌታዬ ሆይ የአንተ ፍቅር እሳትና አንተ ባዘዝከው ፆም የተፈጠረው ግለት በእምነትህ እንዲነዱ፣ አንተንም በማመስገንና በማስታወስ የተወሰኑ እንዲሆኑ እንዲያደርጋቸው ፈቃድህ ይሁን፤
ጌታዬ ሆይ፣ አንተ ባዘዝከው ፆም ጌጥ እንዳስጌጥካቸው ሁሉ በፀጋህና ልግስና በተመላበት ደግነትህ የተቀባይነትህንም ጌጥ አጎናጽፋቸው፤ የሰዎች ሥራ ሁሉ ዋጋ የሚኖረው በአንተ መልካም ፈቃድ ሲደገፍ፤ በትዕዛዝህም ላይ ሲመሠረት ነውና አንተ ፆሙን ያላከበረውን እንደፆመ ብትቆጥረው አንዲህ ያለው ሰው ከእነዚያ ከእምቅድመ ዓለም ጀምረው ፆሙን ከአከበሩት ጋር ይቆጠራል፡፡ ፆሙን ያከበረውን እንዳልጾመ ብትመለከተው ያ ሰው የግልፀትህን ካባ በአቧራ እንዲቆሽሽ ከአደረጉትና ከዚህ ህያው ምንጭ የጠራ ውሃ እንዲወገዱ ከተደረጉት ጋር ይቆጠራል፡፡
አንተ፣ በእርሱ ፣ በስራዎቸህ ሁሉ ምስጉን ነህ የሚለው ዓርማ ከፍ የተደረገው ፤ ትዕዛዝህ ሁሉ የሚከበር ነህ ፤ የሚለውም ሰንደቅ በእርሱ አማካይነት የተዘረጋው ነህ፤ የሁሉም ነገር ልቀት በትዕዛዝህና በቃልህ ላይ ሲመሠረት ብቻ መሆኑን የእያንዳንዱም ተግባር ዋጋ በአንተ ፈቃድና በፍላጎትህ መልካም ፈቃድ እንደሚወሰን እንዲገነዘቡ፣ የሰዎችም ስራዎች ሁሉ ልጓም በአንተ ፈቃድና በትዕዛዝህ መዳፍ ውስጥ መሆኑን እንዲያውቁ፣ ይህን ደረጃህን ለአገልጋዮችህ ግለጽላቸው፣ ክርስቶስ አንተ የመንፈሱ (የየሡስ) አባት ሆይ፣ ስልጣን ሁሉ ያንተ ነው፤ በማለት በሚያወድስባቸው ፤ ወዳጅህም (መሐመድ) አንተ ከሁሉም በላይ ተወዳጅ የሆንከው ሆይ፣ ውበትህን ስለገለጽህ ከእነዚያ ከአንተ በቀር ከሌላው ሁሉ ከተላቀቁት ራሳቸውንም ወደ እርሱ አንተን ራስህን ገላጭና የባህርያትህ ክስተት ወደሆነው ካዞሩት በስተቀር ሌሎች ሰዎች ሁሉ እንዲያዝኑ ወደ ተደረጉበትወደ ታላቁ ስምህ ግልፀት ዙፋን ለመድረስ የሚያስችላቸውን ለተወዳጆችህ ስለፃፍክላቸው ክብር ላንተ ይሁን. በማለት በሚጮህባቸው በእነዚህ ቀናት ምንም ነገር ከውበትህ እንዳይጋርዳቸው ይህን እንዲያውቁ አድርጋቸው፤
ጌታዬ ሆይ፣ እርሱ የአንተ ቅርንጫፍ የሆነውና አጃቢዎችህ በሙሉ አንተን ለማስደሰት ባላቸው ጉጉት በመንበርህ ክልል ውስጥ ሆነው ፆማቸውን ከፆሙ በኋላ ዛሬ ፈስከዋል፡፡ ለእርሱም ለእነርሱም በእነዚያ ቀናት ወደ ቅርበትህ መድረክ ለገቡትም ሁሉ በመጽሐፍህ ውስጥ የወሰንከውን መልካም ነገር ሁሉ እዘዝ እዘዝላቸው፤ እንግዲህ በዚህም ህይወት በወዲያኛውም ህይወት የሚጠቅማቸውን አድላቸው፡፡
አንተ በእውነቱ ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህና፡፡
- Bahá'u'lláh