Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Tablet of the Holy Mariner
እውነቱን ታውቁ ዘንድ የቅዱሳን መርከበኛ መልዕክት አጥኑ የተባረከው ውበት በመጪው ጊዜ የሚፈፀሙት ድርጊቶች ሙሉ በሙሉ እንደተነበዬ አስተውሉ ፡፡
እነዚያ የሚያስተውሉት ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
እርሱ ፀጋ የተሞላው በጣም ተወዳጅ ነው ቅዱስ መርከበኛ ሆይ የዘለአለም መርከብህን በሰማይ ሰራዊት ፊት እንድትታይ እዘዛት፤ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን፤ በእርሱ ከሁሉም በላይ ድንቅ በሆነው ስም በጥንቱ ባህር ላይ አንሳፍፋት፡፡ ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን ፍጹም ከፍተኛ በሆነ አምላክ ስም መልአካዊዎቹ መናፍስት እንዲሳፈሩአት አድርጋቸው፡፡
ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን፤ ከዚያም ምናልባት በውስጧ የሚኖሩበት በዘላለማዊው ግዛት ወደደ ሚገኘው ወደ ቅርበት መጠለያ ይደርሱ ዘንድ
ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን በክቡር ውቅያኖስ ላይ እንድትጓዝ ከታሰበችበት እንድትለቀቅ አድርጋት፡፡ ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
ቀይማ ባህሮች ዳርቻ ወደ ሆነው ወደ ተቀደሰው ባህር ዳርቻ ከደረሰች በኋላ ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን፡፡ በውስጡ ጌታ በሞት አልባ ዛፍ ውስጥ በሁለቱ ነበልባል ወደታዬበት ማዕከል ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን በውስጡ የእርሱ እምነት መገለጫዎች እራሳቸውን ከራስ ወዳድነትና ከምድራዊ ብርቱ ስሜት ወዳነፁበት ፤
ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን በዙሪያው የሙሴ ክብር ዘላለም ከሚኖረው ሰራዊት ጋር ወደሚዞረው ንዑድ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን ከውስጡ የእግዚአብሔር ልጅ ከታላቅነቱ ጉያ ወደ ተዘረጋበት ፤ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! ለነዋሪዎቹ ሁሉም መለኮታዊ ባሕርያት የተነገሩላቸው ቢሆንም፣ በውስጡ የእምነቱ መርከብ እንቅስቃሴ አልባ ሆና ወዳለችበት ማዕከል፤
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
ከመርከቧ እንዲወርዱና ወደዚህ ወደማይታየው መንግስተ-ሰማያዊ ማዕከል እንዲገቡ እዘዛቸው፤
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! መርከበኛው ሆይ! ለእነዚያ በመርከቧ ውስጥ ለሚገኙት፤
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
ምናልባት እንደበረዶ ነጭ በሆነው በተቀደሰው ሥፍራ እንዳይዘገዩ፤ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! ይልቁንም ጌታ በዝቅተኞቹ ዓለማት ከመጠቀስ ሁሉ በላይ ወዳከበረው ማዕከል በመንፈስ ክንፎች ይበሩ ዘንድ፤ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! ልክ በዘላለማዊ የእንደገና መሰባሰብ ግዛት እንደሚገኙት የተመረጡ አዕዋፋት በህዋ ውስጥ ይከንፉ ዘንድ ፤
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
በብርሃን ባሕሮች ውስጥ የተደበቁትን ምሥጢራት ያውቁ ዘንድ፣ በምሥጢራዊው መጋረጃ በስተኋላ እያለህ ያስተማርንህን አስተምራቸው፡፡ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
እነርሱ የምድራዊ ውስንነቶችን ደረጃዎች አልፈው የመለኮታዊ መርሖ ማዕከል ወደሆነው ወደ መለኮታዊ አንድነቱ ደረጃ ደረሱ፡፡
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! እነርሱ ወደዚያ ጌታ ከእነርሱ ደረጃ በላይ እንዲሆን ወዳዘዘው ክብር ለመውጣት ተመኙ፡፡ ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን! በዚያን ጊዜ የሚንበለበለው በራሪ ኮከብ ከእነዚያ በእርሱ ቅርበት መንግስት ከሚኖሩት ውስጥ አውጥቶ ጣላቸው፡፡
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
እነርሱ በክብር ከፍታ ላይ ከሚገኘው ከማይታየው አዳራሽ በስተኋላ የታላቁ ድምጽ እንደሚከተለው ሲናገር ሰሙ፤
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን1
“ እናንት ሞግዚት መላእክት ሆይ”
ንዑዱ ጌታዬ የተወደሰ ይሁን!
“ የእነዚያ ለመረዳት ሚችሉት አዕምሮወወች ሊገነዘቡት የማይችሉት ከእውነት የራቀ እምነት መርከብ እንቅስቃሴ አልባ ሆና ወደቆመችበት አካባቢ፤
- Bahá'u'lláh