Return to BahaiPrayers.net
Facebook
Fasting Prayers
ምስጋና ላንተ ይሁን፣ ጌታ አምላኬ ሆይ! ለእኔና አብረውኝ ላሉት ሁሉ፣ ከሁሉ በላይ ወደሆነው ክብርህ ሰማየ ሰማያት ለመምጠቅ የሚያስችለንንና ተጠራጣሪዎችን ወደ አንድነትህ መቅደስ ከመግባት ካገዱአቸው የጥርጣሬ ጉድፎች የሚያነፃንን እንድትልክልን፣ ጨለማውን ወደ ብርሃን በተለወጠበት፣ የሚዘወተረው መቅደስ በተገነባበት፣ ጽሁፍ መልእክት በተገለፀበትና የተዘረጋው ብራና ሽፋኑ በተነሳበት በዚህ ግልፀት እማጠንሃለሁ፡፡
ጌታዬ ሆይ እኔ ያ የአፍቃሪ ደግነትህን ገመድ አጥብቄ የያዝኩ፣ በምሕረትህና በለጋስነትህ ጠርዝ ላይ የተንጠላጠልኩ ነኝ፡፡ ለእኔና ለተወዳጆቼ የዚህኛውንና የመጪውን ዓለም መልካም ነገሮች ሁሉ አዘዝልን፤ እንግዲህ ከፍጡሮችህ መካከል እጅግ በጣም ምርጥ ለሆኑት ካዘዝክላቸው ሕቡዕ ሥጦታዎች አድላቸው፤
ጌታዬ ሆይ ፣ እነዚህ ቀናት አገልጋችህ ፆም እንዲፆሙባቸው ያዘዝካቸው ናቸው፡፡ ከአንተ በስተቀር ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ራሱን አግልሎ ለአንተ ብቻ ሲል የፆመ የተባረከ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ አንተን እንድንታዘዝና ሕግጋትህን እንድናከብር እርዳኝ፣ እነርሱንም እርዳቸው፣ አንተ በእውነቱ የመረጥከውን ለማድረግ ኃይል አለህና፡፡
ከአንተ ከሁሉን አዋቂው፣ ከፍጹም ጠቢቡ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ የዓለማት ሁሉ ጌታ ለሆነው የእግዚአብሔር ምስጋና ሁሉ ይሁን፤
በፆም ጊዜ የማለዳ
አምላኬ ሆይ፣ ከቅርበትህ ከተማ በር አርቀህ እንዳትጥለኝና በፍጡሮችህ መካከል በፀጋህ ክስተቶች ላይ ያደረግሁአቸውን ተስፋዎች እንዳትቀጭብኝ፤ በኃያሉ ምልትህና በሰዎች መካከል በፀጋህ መገለጽ እማጠንሃለሁ፤ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ጠንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ ሁልጊዜ ይበልጥ ወደ በርህ ደጀሰላም እንድታቀርበኝ፣ ከምህረትህ ጥላና ከቸርነትህ አጎበር እንድርቅ እንዳታደርገኝ በፍጹም ጣፋጩ ደምጽህና ፍጹም በተከበረው ቃልህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፤ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ በመጎናፀፊያህ መዓዛ እንድትስበኝና የቃልህን ምርጥ የወይን ጠጅ እንድጠጣ እንድታደርገኝ፣ በአንፀባራቂው የግምባርህ ውበትና ከፍጹም ከፍተኛው አድማስ በሚያበራው የገጽህ ብርሃን ብሩህነት እማጠንሃለሁ፡፡
አምላኬ ሆይ ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላትዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ ወደ ኋላ ሳላፈገፍግ ወይም እነዚያ በምልክቶችህ ያፌዙትና ከፊትህም የዞሩት በሚያቀርቡአቸው ሃሳቦች ሳልደናቀፍ እምነትህን እንዲገለግል በጣም እንድታነሳሳኝ፣ ልክ ፍጹም የተከበረው ብዕርህ በፍጥረትህ መንግስት ላይ የስውር ትርጉሞች ልዩ መዓዛ እያፈሰሰ በጽላቶችህ ገጾች ላይ እንደሚንቀሳቀስ ሁሉ በፊትህ ላይ በሚንቀሳቀሰው ፀጉርህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹመ ቅዱሱን ፍፁም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ በውበትህ የቀኑ ኮከብ ላይ ለማተኮር እንድታስችለኝና የልሳንህንም የወይን ጠጅ እንድታድለኝ፣ የስሞች ንጉስ በአደረግኽው በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በተመሰጡበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር እንድታርቀኝና እርሱ የአንተ ምልክቶች ጎሕ የሆነው ወደ አበራበት ደረጃ እንድታቀርበኝ፣ በመለኮታዊው ሎጥ ዛፍ መንኮሻኮሽና በስሞችህ መንግስት ውስጥ የልሳንህ ልዝብ ነፋሾች ድምጽ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውን ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር እንድታርቀኝና እርሱ የአንተ ምልክቶች ጎሕ የሆነው ወደ አበራበት ደረጃ እንድታቀርበኝ፣ በመለኮታዊው ሎጥ ዛፍ መንኮሻኮሽና በስሞችህ መንግስት ውስጥ የልሳንህ ልዝብ ነፋሾች ድምጽ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን፣ ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ በዕውቀትህ ማከማቻዎች ውስጥ የተደበቁትንና በጥበብህ ማስቀመጫዎች ውስጥ የተሸሸጉትን እንድትገልጥልኝ፣ በዚያ ከፈቃድህ አንደበት ከመውጣቱ ውቅያኖሶች እንዲተምሙ ነፋሶችም እንዲነፍሱ ፣ ፍሬዎችም እንዲገለጡ ዛፎችም እንዲበቅሉ፣ ያለፉት ደብዛዎች ሁሉ እንዲጠፉ ፣ ግርዶሾችም ሁሉ እንዲተረተሩ ፣ ለአንተም ያደሩት ወደማይጨቆነው የእነርሱ ጌታ ገጽታ ብርሃን እንዲለግሱ ባደረገው ፊደል እማጠንሃለሁ፣ አምላኬ ሆይ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛውም ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፤
አምላኬ ሆይ በመጽሐፍህ ውስጥ አንተ ላወረድከውና በፈቃድህም ለተከሰተው ከበቁት ጋር እንድትቆጥረኝ፣ እንቅልፍን ከሕሩያንህና ከተወዳጆችህ አይኖች ባባረረው የፍቅርህ እሳት፣ ጎህ በሚቀድበትም ሰዓት በእነርሱ አንተን ማስታወስና ማወደስ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን፣ ፍጹም ኃያሉን፣ ፍጹም ታላቁን፣ ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ ፣ ለታማኖችህና ለሕሩያንህ የፃፍከውን ለኔም ፍጹም በተከበረው ብዕርህ እንድትጽፍልኝ ለአንተ የቀረቡት በትዕዛዝህ ጦሮች መወጋትን እንዲቀበሉ፣ ለአንተ ያደሩትም የጠላቶችህን ሰይፎች በመነግድህ እንዲጋፈጡ ባደረጋቸው በገጽህ ብርሃን እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር ተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ ለተመለሰው ለእያንዳንዱ ሰው፣ አንተ የያዝከውንም ፆም ላከበረው፣ በአንተ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ለማናገሩትና ያላቸውንም ሁሉ በአንተ መንገድና ለአንተ ፍቅር ሲሉ ለሰውት ያዘዝከውን ካሳ እንድትጽፍለት፣ ያፍቃሪዎችህን ጥሪ፣ የእነዚያን አንተን የሚናፍቀቱትንም የኃዘን ድምጽ እነዚያ ወደ ቅርበትህ ለመግባት የታደሉት የሚያሰሙትንም ጩኽት እነዚያ ላንተ ያደሩት የሚያሰሙትንም ማቃሰት ባዳመጥህበትና በፀጋህና በቸርነትህ፣ የእነዚያን ተስፋቸውን በአንተ ላይ ያደረጉትን ሰዎች ምኞቶች በአሟላህበትና ፍላጎቶቻቸውንም በፈቀድክበት ስምህ፤ የይቅር ባይነትም ውቅያኖስ በፊትህ በተመመበትና የቸርነትህ ደመናዎች በአገልጋዮችህ ላይ በዘነቡበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡
ጌታዬ ሆይ፣ እነዚያ ህግጋትህን አጥብቀው የያዙትና በመጽሐፍህ ውስጥ የደነገግህላቸውን ያከበሩት የፈፀሙትን በደል ትሰርዝላቸው ዘንድ በአንተው በራስህ በምልክቶችህ በግልጽ መታወቂያዎችህ በሚያበራው የውበትህ የቀኑ ኮከብ ብርሃንና በቅንጫፎችህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፤
- Bahá'u'lláh