[{"Id":1379,"Year":2026,"BEYear":183,"LanguageId":90,"Title":null,"Text":"
አሁን የዘጠኝ ዓመቱ ዕቅድ ሁለተኛውና የላቀው ምዕራፍ ተጀምሯል። ዓለም አቀፉ የባሃኢ ማኅበረሰብ በነደፈው አቅጣጫ ላይ ባለው ተገቢ የሆነ መተማመን፣ በአንድነት ወደፊት ሲገሰግስ እንመለከተዋለን። የአላማው ግልጽነትና ጽኑ እምነቱ የማያወላዳ ነው። በዓለማችን ግዝፈት እየነሳ ባለው ቀውስ ሳይበገር፣ ትኩረቱን በተቀደሰ ተልዕኮው ላይ አድርጓል። በተለይም ደግሞ፣ አዳዲሶቹ ጽናትን የተላበሱ አማኞች ከቀደምት ፅኑ ምዕመናን ጋር ጎን ለጎን በአገልግሎትና በተግባር መስክ ተሰልፈው ስናይ ታላቅ ደስታ ይሰማናል። የሦስተኛው ምዕራፍ ስብስቦች የዳበሩ ተሞክሮዎች የሚቀሰሙባቸውና የሚሰራጩባቸው ለም መስኮች መሆናቸውን እያስመሰከሩ ነው። እንዲሁም፣ ባለፈው ታኅሣሥ ወር እዚህ ለተሰበሰቡት አማካሪዎች ያስተላለፍነውን መልእክት፤ ወዳጆች በሁሉም ቦታ በማሰላሰል፣ ለዕቅዳቸውና ለተግባራቸው መመሪያ እያደረጉት መሆኑን በማየታችን ተደስተናል።
\n
ይህ ዓላማ ያለው መንፈስ፣ በተለይ በዓለም ዙሪያ በተካሄዱት የተቋማት ስብሰባዎች ላይ በግልጽ ታይቷል። የእነዚህ ስብሰባዎች መግለጫዎች ደጋግመው አንድ ዓይነት ክስተትን ዘግበዋል፤ ይኸውም፣ በግምቶች ወይም በንድፈ-ሐሳቦች ላይ ሳይሆን፣ ሕይወታማ ማኅበረሰቦችን በመገንባት ሂደት ውስጥ በተገኘ ቀጥተኛ ተሞክሮ ላይ የተመሠረተ ጥልቅና በማስተዋል የተመላ ጭውውት እንደነበረ ነው። ይህ ጭውውት በእያንዳንዱ ቦታ በሚካሄደው ቀጣይነት ያለው የመማር ሂደት ተጋግሏል። ጭውውቱም ስለባሃኢ ማኅበረሰብ ጥረቶች እና ጥረቶቹም አቅጣጫ ለሚሻውና በችግር ለተናወጠው ዓለም ያላቸውን ፋይዳ በጥልቀት በመገንዘብ የታጀበ ነው። የኃላፊነትና ቁርጠኝነት ስሜት በሰፊው የሚታይ ሲሆን፣ በእጃችን ላይ ያለው ተግባር ምን ያህል ሰፊ እንደሆነም ጥልቅ ግንዛቤ አለ። ይህ ጭውውት ብዙ ጊዜ ለሌላ ተጨማሪና ምልዓት ለሚሰጥ አመለካከት በር ይከፍታል፤ ይህም የማኅበረሰቦችና የግለሰቦች ጥረቶች አንደ የምንከታተላቸው ፕሮግራሞች ወይም ፕሮጀክቶች ብቻ አቅልሎ ማየት ሳይሆን፣ ነገር ግን በመለኮታዊ ትምህርቶች ላይ የተመሠረተ የተግባር፣ የግንኙነትና የእሾትን ቅርጽ የማስያዝ የሕይወት ዘይቤን ማዳበርን ከግንዛቤ የወሰደ ነው፡፡
\n
ይህ ለመማር ያለን ቁርጠኝነት የሚንጸባረቅበት ልባዊ ጭውውት፣ በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ እንዲሁም እስከ መንደርና ሰፈር ድረስ በመላው ማኅበረሰብ ውስጥ እየተስፋፋ ይገኛል፤ ይህም በተቋማት በሚዘጋጁ ስብሰባዎችና አዲስ እየተፈጠሩ ባሉ ሌሎች መድረኮችም ጭምር እየተከናወነ ነው። በእርግጥም ይህ ሁኔታ በብሔራዊ ጉባኤዎች ላይም አንዱ ገፅታ የሚሆን ነው። ይህ ጭውውት እየሰፋ ሲሄድ፣ የግለሰብም ሆነ የጋራ ተግባራት ይበልጥ እየተጠናከሩና እየተስፋፉ ሲሄዱ ለማየት እንጓጓለን። እንደወትሮው ሁሉ፣ ይህ ጭውውት የሰው ልጅ አንድነትን መሠረት በማድረግ መንፈሳዊና ቁሳዊ እድገትን ለማምጣት በሚደረጉ ጥረቶች በሚስማሙ የወዳጆች፣ ጎረቤቶች እና ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው የሌሎች ሰዎች እየሰፉ በሚሄድ ክበባት ውስጥ መስፋፋት ይገባዋል። ድንገተኛም ወይም ቀድመው የታቀዱ ይሁኑ፣ ይህንን ጭውውት ለማስፋት የሚፈጠሩት መድረኮች ከማኅበረሰቡ ጋር ያለን ግንኙነት እየጠነከረ የመምጣቱ ምልክቶች ናቸው፤ እነዚህም መድረኮች ይበልጥ እየተለመዱ እንደሚሄዱ ተስፋ እናደርጋለን።
\n
በሰፊው ማኅበረሰብ ውስጥ ባሃኢዎች ከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍል ጋር የሚያከናውኑት እንቅስቃሴ የገጠሟቸው ብዙ ሰዎች እንቅስቃሴው በሚያሳየው ልዩ መገለጫዎች ይደነቃሉ:- እንቅስቃሴው ለሁሉም ደኅንነት ከልብ ከማሰብ ይመነጫል፣ ትኩረቱን በአንድነትና በአገልግሎት ላይ ያደርጋል፣ እንዲሁም ግልጽ የሆኑ መመሪያዎችን የሚከተል ቢሆንም ለሁሉም ችግሮች ፈጣን መልስ አለኝ ብሎ አይኩራራም ። ባሃኢዎች በጋራ ጥረት መንፈስ ከሌሎች ጋር ለመተባበርና አብሮ ለመማር ይጥራሉ፤ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታ ካላቸው አካላት ጋር በሚመሠርቱት ግንኙነትም ቅንና አስተዋይ ናቸው። ያለ ምንም ፖለቲካዊ ፍላጎት ወይም የግል ጥቅም ማኅበራዊ ለውጥን ያራምዳሉ፤ እንዲሁም ሃይማኖቱ እየጎላ ሲሄድ፣ ስለእውነተኛ ባህሪውና ዓላማው ተገቢው ግንዛቤ መኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ይገነዘባሉ። በብዙ ቦታዎች፣ የማኅበረሰቡ ከሰፊው ሕብረተሰብ ጋር ያለው መስተጋብር ጥልቀት እየጨመረ መምጣት የሚያሳየው፣ አዳዲስ የሚታሰሱ ሁኔታዎችና መልስ የሚፈልጉ አዳዲስ ጥያቄዎች መኖራቸውን፣ እንዲሁም ማኅበረሰቡ የራሱን አቅም ይበልጥ እንዲያሳድግ ማስገደዱ አይቀሬ መሆኑን ነው።
\n
በቅርቡ ለአማካሪዎች ጉባኤ በላክነው መልእክት ላይ እንደገለጽነው፣ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የታየው ጉልህ እድገት ማኅበረሰቡ የዕቅዱ ይበልጥ ጎልቶ የሚታይ ዋና ተዋናይ ሆኖ መውጣቱ ነው፤ ማኅበረሰቡ የተወሰኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና በተለዩ የጥረት መስኮች ለመራመድ፣ በጋራ የትብብር ቅንጅቶች አማካኝነት እርስ በእርስ ለመደጋገፍ፣ እንዲሁም እየተሻሻለ በሚሄድ የድርጊት ማዕቀፍ ውስጥ ውጤታማነቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመጨመር ራሱን እያደራጀ ይገኛል። ለዚህ አንዱ አስደናቂ ምሳሌ በአንድ አካባቢ አብረው የሚሰሩ እና የእኩዮቻቸውን ተሳትፎ የሚያበረታቱ የወጣቶች ቡድን ነው። ወጣቶቹ የሚያደርጉት ጥረት በተቋማቱ ፍቅራዊ ማበረታቻና አመራር በእጅጉ መደገፉ ተፈጥሯዊ ሆኖ ሳለ፤ ወጣቶቹ ተነሳሽነትን የመውሰድ እና ፍሬያማ የሆኑ የአገልግሎት መንገዶችን የመለየት ችሎታቸውን አሳይተዋል። አብዛኛውን ጊዜ ጥረቶቻቸው የሚከናወኑት፥ ግጭትና ሁከት፣ ኢኮኖሚያዊ ኢ-ፍትሃዊነት እና ጥልቅ ማኅበራዊ መከፋፈል የሞላበትን ሁኔታ በመጋፈጥ ነው። ወጣቶች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንገነዘባለን፤ እንዲሁም የመተቸት እና የመኮነን ስሜትን በመቋቋም፣ ይልቁንም እነዚህን ከባድ እንቅፋቶች አልፎ ለመሄድ እና በመጨረሻም ድል ለመንሳት የሚያስችሏቸውን ገንቢ መንገዶችን በመፈለጋቸው እናደንቃቸዋለን።
\n
የተወደዳችሁ ወዳጆች፤ ጊዜው ምንም ያህል በነውጥ የተሞላ ቢሆንም፣ ስጋት እንዳይሰማችሁ ወይም ተስፋ እንዳትቆርጡ እናሳስባችኋለን። አብዱል-ባሃ ሁላችንም በአምላክ ችሮታዎች እንድንታመን፣ እንዲሁም \"ሁሌም ተስፋ የምናደርግ\"፣ በተስፋችንም \"የምንጸና\" እና \"ተስፋ ለቆረጠች ነፍስ የተስፋ ምክንያት\" እንድንሆን ይመክረናል። የዓለም አድማስ ሲጨልም፣ ተስፋ ብርቅ እና ውድ ሀብት ይሆናል፣ ነገር ግን የእጅግ ታላቁ ስም ማኅበረሰብ ስለ ሰው ልጅ የወደፊት ሁኔታ አስመልክቶ ባለው ጽኑ እምነት እና ከራሱ ልምድ በወሰደው ትምህርት የተነሳ በዚህ ረገድ አብዝቶ ተባርኳል። እጅግ ብዙ ሰዎች እናንተ ወደ ልባቸው ልታመጡላቸው የምትችሉትን ተስፋ ይናፍቃሉ።
\n
ለረጅም ጊዜ የተስፋን ነበልባል ጠብቆ በማኖር ወርቃማ ተምሳሌት የሆነን ማኅበረሰብ ስናስብ፣
\n
በደል የደረሰባቸውን ሆኖም ሁሌም ታጋሽ፣ ሁሌም ጽኑ እና ሁሌም የማይበገሩ የሆኑትን በእርሱ ሃይማኖት መፍለቂያ ምድር ውስጥ ወደሚገኙት፣ የባሃኡላህ ተከታዮች እንመለከታለን። በአስርት ዓመታት ውስጥ በዘለቀው በማያቋርጥ ጭቆና ውስጥ እንዴት ተግተው እንደቆዩ፣ ለመርህ ያላቸው ቁርጠኝነት ምን ያህል እንደሆነ፣ እንዲሁም በሌሎች አገሮች የሚገኙ የእምነት ባልንጀሮቻቸው ካደረጓቸው እድገቶች ለመማር ምን ያህል እንደቆረጡ፣ በአገራቸው ውስጥ የሚኖሩ ወገኖቻቸውን ለማገልገልና እነርሱን ለማጽናናት እንዴት እንደተነሱ ተመልከቱ። ለብዙዎቹ የአገራቸው ዜጎች የተስፋ ብርሃን፣ የርህራሄና የጥልቅ እይታ ምንጭ፣ እንዲሁም በአገልግሎት ጎዳና ላይ የታመኑ አጋሮች ሆነዋል፤ አሁንም መሆናቸውን ቀጥለዋል። ባለፉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ፣ እጅግ የምንወዳቸው እነዚህ ወዳጆች ዘወትር በሀሳባችን ውስጥ ነበሩ፣ ዘለዓለም አፍቃሪ የሆነው ጌታ በፍቅራዊ ጥበቃው እቅፍ ውስጥ እንዲይዛቸው በመለመን ደጋግመንም በጸሎታችን አስበናቸዋል፤ እናንተም እንዲሁ እንደምታደርጉ እርግጠኞች ነን።
\n
በተለይም አሁን፣ በዘጠኝ ዓመቱ ዕቅድ አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ፣ የአምላክን ዓላማ ለማስፋፋት የምታደርጉት የእናንተ ጥረትም ቢሆን፣ በቅዱሱ ደፍ ላይ የምናቀርበው ተማፅኖ ትኩረት ነው። ወደ ቅዱሳን መካነ-መቃብሮች በምንሄድበት ጊዜ ሁሉ፣ ለጥረቶታችሁ መለኮታዊ ዕርዳታንና ድጋፍን እንለምናለን፤ ለሥራችሁም ጽናትንና ጥንካሬን እንማጸናለን። ለተግባር የፈጠናችሁ፣ ለመማርም የጓጓችሁ ትሆኑ ዘንድ፤ የሰማያዊው መንግሥት በረከቶች ሁሉ የእናንተ ይሆኑ ዘንድ እንመኛለን።
"},{"Id":940,"Year":2020,"BEYear":177,"LanguageId":90,"Title":null,"Text":"
ሁለት ብቅ እያሉ ያሉ እውነታዎች እነዚህን ቃላቶች ለእናንተ እንድናካፍል ገፋፍተውናል፡፡ የመጀመሪያው እውነታ
\n
እያንዣበበ ስላለውና አሰቃቂ ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አደጋዎች በዓለም ዙሪያ እያደገ የመጣው ንቃተ-ህሊና ነው። በብዙ አገሮች ውስጥ እልቂትን ለመታደግ ጀግንነት የመላቸውና ቆራጥ እርምጃዎች በጋራ ቢወስዱም ፣ በቤተሰቦች እና በግለሰቦች ላይ ሃዘን በመፍጠር እንዲሁም መላ ማህበረሰቦችን ቀውስ ውስጥ በመክተት ሁኔታው እነሆ ከባድ ሆኗል፡፡ የመከራ እና የሃዘን ማዕበሎች ከቦታ ወደ ቦታ እየተከሰቱ ነው ፤ እናም ይህ በተለያዩ ወቅቶች፣ በተለያዩ መንገዶች የተለያዩ ሀገሮችን ያዳክማል፡፡
\n
ሁለተኛውና በየዕለቱ ይበልጥ ገሃድ እየሆነ ያለው እውነታ፣ የባሃኢ ዓለም ሊታወስ ከሚቻል ግዜ ወዲህ አይቶት
\n
የማያውቀውን ተግዳሮት የመቋቋም ብቃት እና ያልተደቆሰ ሕያውነቱ ነው፡፡ የሰጣችሁት ምላሽ ድንቅ ነው፡፡ ከአንድ ወር በፊት በናውሩዝ ክብረ-በዓል ወቅት ወደ እናንተ ስንጽፍ፤ እነኛ ተለምዷዊ የእንቅስቃሴ ዘይቤያቸው የተስተጓጎለባቸው ማህበረሰቦች ያሳዩዋቸው አስደማሚ ባህሪያትን አፅንዖት ለመስጠት ሞክረን ነበር፡፡ ወዳጆች ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እየሆኑ የመጡ ገደቦችን እንዲያከብሩ በተጣለባቸው ከዛን ወዲህ ባሉ ሳምንታት ውስጥ በሆነው ሁሉ የአድናቆት ስሜታችን ይበልጥ ጨምሯል። አንዳንድ ማህበረሰቦች በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካገኙት ተሞክሮ በመማር፣ ደህንነታቸው አስተማማኝ የሆኑ እና ፈጠራ የተመላቸው በሕዝቦች ውስጥ ያሉትን የህዝብ ጤና ፍላጎቶች ግንዛቤ ማሳደጊያ መንገዶችን አግኝተዋል፡፡ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑት እና ከመስፋፋቱ ጋር ተያይዞ ለኢኮኖሚያዊ ችግር ለሚዳረጉት ልዩ ትኩረት እየተሰጣቸው ነው፤ ይህን አስመልክቶ በባሃኢ የዓለም የዜና አገልግሎት (Baha'i World News Service) ላይ የሚወጡት ዘገባዎች እየተከናወኑ ካሉቱ ቁጥር ስፍር ከሌላቸው እንቅስቃሴዎች አኳያ እፍኝ አይሞሉም፡፡ እነኚህም፥ በጣም ተፈላጊ የሆኑ መንፈሣዊ ባህሪያትን ለመመርመር ፣ ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ በሚደረጉ ጥረቶች ይበልጥ እየታገዙ ይገኛሉ። እንደዚህ ያሉ በርካታ ጥረቶች በቤተሰብ ወይም በግል ደረጃ መደረጋቸው እንዳለ ሆኖ፣ ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን ወይም የመገናኛ መሳሪያዎች በሚያስችሉበት ግዜ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን በሚጋሩ ነፍሳት መካከል ልዩ የሆነ የትብብር ስሜት ሆን ተብሎ እየተጠናከረ ይገኛል ፡፡ ለጋራ እድገት በጣም አስፈላጊ የሆነው የህብረተሰብ ኑሮ መስተጋብር አይንበረከክም።
\n
የብርሃን ሠራዊት የማይታክቱ ፊታውራሪዎች የሆኑት ብሔራዊ መንፈሣዊ ጉባዔዎች እንዴት ማኅበረሰቦቻቸውን
\n
በብቃት እንደመሩና እና ለተፈጠረው ቀውስ የሚሰጠውን ምላሸ ቅረጽ እንዳስያዙ በማየታችን መንፈሣችን ከፍ ከፍ ብሏል፡፡ እንደ ሁልጊዜም ሁሉ ፍቅር የተመላበት የአገልግሎት ዓርማን በጀግንነት ካነገቡ አማካሪዎች እና ረዳቶቻቸው ጠንካራ ድጋፍን አግኝተዋል። መንፈሣዊ ጉባዔዎች በየአገሮቻቸው በፍጥነት ተለዋዋጭ ስለሆኑት ሁኔታዎች ወቅታዊ መረጃ ይኖራቸው ዘንድ በሚገባ እየተከታተሉ ሣለም የዕምነቱን ጉዳዮች ለማስተዳደር፤ በተለይም ምርጫን ማካሄድ በሚቻልባቸው ቦታዎች ይህን ለመከወን አስፈላጊውን ዝግጅቶች አድርገዋል። ተቋማት እና ኤጀንሲዎችም በመደበኛ መልዕክት አማካኝነት ጥበብ ያዘሉ ምክሮች፣ የሚያረጋጉ ማጽናኛዎችን እና ቀጣይ ማበረታቻን ሰጥተዋል፡፡ በብዙ አጋጣሚዎችም፣ በማህበረሰባቸው ውስጥ ከሚነሱ የውይይት መድረኮች የሚመነጩ ገንቢ ጭብጦችን መለየት ጀምረዋል፡፡ በናው-ሩዝ መልዕክታችን ውስጥ ይህ የሰው  ልጅ ጽናቱን እየተፈታተነ ያለው ፈተና ታላቅ ማስተዋልን እንደሚለግሰው እንደምንጠብቅ የገለጽነው ተስፋ እነሆ ዕውን መሆን ጀምሯል፡፡ መሪዎች፣ ታዋቂ ምሁራን እና ተንታኞች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከሕዝባዊ የመወያያ ርዕስነት ርቀው የነበሩ መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና ድፍረት የተመሉ ተስፋዎችን መዳሰስ ጀምረዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ በአሁኑ ጊዜ ገና የመጀመሪያ ጭላንጭሎች ቢሆኑም የጋራ የንቃተ-ህሊና ወቅት ይመጣ ዘንድ እድል እንዳለ ማሳያ ናቸው፡፡
\n
የባሃኢ ዓለም አይበገሬነት በተግባር ሲገለጥ ከማየት የሚሰማን እፎይታ፣ ወረርሽኙ በሰው ልጆች ላይ በሚያስከትለው
\n
መዘዝ በሚሰማን ሃዘን ለዝቧል። በቃ እንግዲህ፣ ምእመናን እና አጋሮቻቸውም የዚህ ሥቃይ ተካፋይ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ አሁን በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ሰዎች ህዝባዊ የደህንነት መስፈርቶችን ከማክበር አኳያ የሚተገብሩት ከወዳጆች እና አዝማዶች ጋር የመራራቅ ሁኔታ፣ ለአንዳንዶች እስከወዲያኛው ላለመገናኘትም መንገዶችን ይከፍታል፡፡ በእያንዳንዱ ንጋት ላይ፣ ፀሐይ ከመጥለቋ አስቀድሞ ተጨማሪ ሥቃዮችን መቋቋም ግድ የሚል ይመስላል፡፡ በዘለአለማዊ ግዛቶች ውስጥ እንደገና የመገናኘት ተስፋ የሚወዷቸውን በሞት ለሚያጡ መፅናኛ ይሁንላቸው። እነኛ ትምህርታቸው፣ ኑሮአቸው፣ ቤታቸው ብሎም መተዳደሪያቸው ራሱ እንኳ ለአደጋ የሚያጋለጡት ልባቸው እፎይታ እንዲያገኝ እና የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲከባቸው እንጸልያለን። ስለእናንተ እና ስለምትወዷቸው እንዲሁም ስለወገኖቻችሁ ሁሉ ባሃኦላህን እንማጸናለን እንዲሁም በረከቱና ሞገሱን እንለምናለን፡፡
\n
ከፊት የሚጠብቀው መንገድ የቱንም ያህል ረዥም እና አድካሚ ቢሆን ፣ ጉዞውን ለመጨረስ ባላችሁ ጽናትና
\n
ቁርጠኝነት እጅግ ሙሉ እምነት አለን፡፡ የሌሎችን ፍላጎት ከራሳችሁ በማስቀደም፣ ያጡትን መንፈሣዊ ምግብ እንዲመገቡ ለማስቻል፣ እነዛ መልስ ለማግኘት ጥማታቸው የሚበረታውን እርካታ እንዲያገኙ ለማድረግ እንዲሁም እነዛ ዓለም ትሻሻል ዘንድ ለመሥራት የናፈቁት አስፈላጊው እንዲመቻችላቸው ለማድረግ ከተስፋ፥ ዕምነትና እና የልዕልና ማከማቻዎች ትወስዳላችሁ። እንዴት ለተባረከው ፍጹምነት ከተሠጡ ታማኝ ተከታዮች ከዚህ ያነሰ ልንጠብቅ እንችላለን?